ዳንኤል ክብረት ዋሹ
ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በማህበራዊ ሚድያቸዉ ላይ ያሰራጩት መረጃ የተሳሳተ ነው - ኢትዮጵያ ቼክ
ትናንት ምሽት አንድ የጦር ሜዳ መገናኛ ሬዲዮን የሚያሳዩ ሁለት የስክሪን ቅጂዎች (screenshots) በማህበራዊ ሚዲያ በስፋት ሲዘዋወሩ ነበር።
አንደኛው የስክሪን ቅጂ 'Tigray Press’ የሚል ስም ካለው የፌስቡክ አካውንት እንደተወሰደ ተደርጎ የቀረበ ሲሆን የጦር ሜዳ ሬዲዮው እአአ ታህሳስ 23/2020 ዓ.ም በአካውንቱ እንደተጋራ ያሳያል።
በአንጻሩ ሁለተኛው የስክሪን ቅጂ 'አስረስ ማረ ዳምጤ' የሚል ስም ባለው የፌስቡክ አካውንት ከደቂቃዎች በፊት እንደተወሰደ ያስነብባል።
እነዚህ የስክሪን ቅጅዎች በስፋት ማህበራዊ ሚድያ ላይ ሲጋሩ ተመልክተናል። ምስሎቹን ካጋሯቸው ሰዎች መካከልም የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ይገኙበታል።
ኢትዮጵያ ቼክ ሁለቱ ስክሪን ቅጂዎች ተወሰዱ የተባሉባቸውን የፌስቡክ ገጾች በተመለከተ ማጣራት አድርጓል።
'Tigray Press' የተባለው የፌስቡክ ገጽ እአአ ታህሳስ 23/2020 ዓ.ም የወታደራዊ ሬዲዮ የሚያሳይ ይዘት አጋርቶ እንዳልነበር ተመልክተናል። ለዚህም ‘ሁ ፖስትድ ዋት’ (Who Posted What) የተባለውን የቆዩ ፖስቶችን መፈለጊያ መገልግያ ተጠቅመናል።
በተጨማሪም ምናልባት በዛኑ ቀን የተጋራና ኤዲት የተደረገ ይዘት ይኖር ይሆን በማለት ምልከታ ያደረግን ቢሆንም ትግራይ ፕሬስ በተጠቀሰው ቀን ያጋራው ምንም ነገር አልነበረም ማለቱን ዳጉ ጆርናል ከዘገባው ተመልክቷል።
በተጨማሪም የሪቨርስ ኤሜጅ ሰርች (Reverse Image Search) መተግበሪያዎችን በመጠቀም ለማሰስ የሞከርን ሲሆን ምስሉ በተጠቀሰው ወቅት የትም ቦታ ተጋርቶ ማግኘት አልቻልንም።
በተጨማሪም የወታደራዊ ሬዲዮው ምስል በትግራይ ፕሬስ ተጋርቶ ነበር ብለው የሚከራከሩ ወገኖች ወደ ይዘቱ የሚያደርስ ምንም አይነት ማስፈንጠሪያ አላያያዙም።
በአንጻሩ ሁለተኛውን የስክሪን ቅጅ ተጋራበት በተባለው አካውንት አሁንም ይታያል። ብሎም ምስሉ ትክክለኛ መሆኑን የሚያጠናክሩ ተጨማሪ ምስሎችና ቪድዮን ወደ አካውንቱ በመሄድ መመልከት ይቻላል።
ይህም የመጀመሪያውን ስክሪ ቅጅ ትክክለኛነት ጥያቄ ውስጥ የሚከት ብቻ ሳይሆን የተሳሳተ መሆኑን ያሳያል።
በአሁኑ ጊዜ እንዲህ ያሉ የስክሪን ቅጂዎችን ለመፈብረክ ቀላል ሲሆን ሀሠተኛ ስክሪን ቅጂዎችን ወደሚፈበርኩ መተግበሪያዎች በመሄድ ማምረት እየተለመደ መጥቷል።
ስለሆነም በማህበራዊ ሚዲያ ገጾች የምንመለከታቸውን ስክሪን ቅጅዎች ከማመናችን እና ከማጋራታችን በፊት ትክክለኛ መሆናቸውን እንመርምር ሲል የመረጃ አጣሪዉ ኢትዮጵያ ቼክ መልዕክት አስተላልፏል።
Credit - ኢትዮጵያ ቼክ
@sheger_press