❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ታኅሣሥ ፲፫ (13) ቀን።
❤ እንኳን #ለታላቁ_አባት_ቆቅ ሲመገብ ለነበሩት #ለአባ_መቃርስ ወደ ብሔረ ሕያዋን ለገባበት በዓል፣ በስላሞች ዘመን በሰማዕትነት ለዐረፈ #ለአባ_በጽንፍርዮስና ከላይኛው ግብጽ ለሆነ #ለቅዱስ_አባት_ለአባ_አብራኮስ ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦#ቅድስት_ሐና እመቤታችንን ቅድስት ድንግል ማርያም ጸነሰቻት የሚሉ አሉ፣ በደብረ ቀልሞን ከሚኖር ከገዳማዊ #ከአባ_ሚካኤል ዕረፍት፣ #ከሰማዕት_ቅዱስ_አብራቂስ_ከሐርስፎስ፣ #ከመኰንኑ_ቆርኔሌዎስ_ከወርቅጥጶስና_ከአፍሬ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #ቆቅ_ሲመገብ_የነበረው_አባ_መቃርስ፦ ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ ጀምሮ ሕያው እግዚአብሔርን መከተል ፈልገ የቤተ ክርስቲያንንም ትምህርት መጻሕፍትንም ተማረ የዚህንም ዓለም ኃላፊነቱን ለጻድቃንም በጎ ዋጋ ለኃጥአን ቅጣት እንዳለም አስተዋለ ስለዚህም ዓለምን ትቶ በአንድ ገዳም ውስጥ መነኰሰ ከዚያም ወጥቶ የዐሥር ቀን ጎዳና ተጓዘና በውስጡ ኲዕንትና ቆቆች ውኃም ካለበት ተራራ ደረሰ። አስቦ እንዲህ አለ "ኵዕንት ወደመልቀም ብሰማራ የስግደቴና የጸሎቴ ሥራ ይቋረጣል ሰብስቦ የሚያስገባልኝ ረዳት የለኝም ብቸኛ ነኝኛ ሥጋ አትብላ ያለውስ የባልንጀራችንን ሥጋ በሐሜት የምንበላውን አይደለምን ሌላ ምግብም እንደሌለኝ ፈጣሪዬ ያውቃል" ብሎ ከዚያችም ዕለት ወዲህ ቆቆችን የሚያጠምድ ሁኖ በየቀኑ አንዳንድ የሚያዙለት ሆነ። እርሳቸውንም እየተመገበ ከዚያ ውኃም እየጠጣ በማመስገን ኖረ በቀንና በሌሊትም በጸሎትና በስግደት በመትጋት ወደ እግዚአብሔርም እየለመነ ብዙ ዘመናት ኖረ የሰውንም ጽምፅ አይሰማም የሰውንም ፊት አያይም ሐሜትንም ሆነ ስድብን በማንም ላይ አብሮ አይነጋገርም ከሰው ጋር ከልሆነ በቀር ሰይጣን አይመጣም ይባላልና።
❤ ከዚህም በኋላ ከቊስጥንጥንያ ከተማ አንድ መነኵሴ ዋሻ እየፈለገ አባ መቃርስ ከአለበት ደርሶ ቆቅን ሲያጠምድ አየው ያን ጊዜ አልታገሠም ግን ወንድሙን በሐሜት እስከሚገድለው ቸኰለ ወደ የቊስጥንጥንያ ከተማ ወደ ሊቀ ጳሳሳቱ ተመልሶ እንዲህ ብሎ ነገረው "እኔ ዋሻ እየፈለግሁ ወደ በረሀ ሔድሁ በዚያም ሥጋ ሊበላ ቆቅን ሲያጠምድ መነኵሴውን አየሁት የሚሠራውን ሲያዩ በአሕዛብ ዘንድ ሊያስነቅፈን ነው" አለው።
❤ ሊቀ ጳጳሳቱም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ነገሩ እውነት እንደሆነ ያውቅ ይረዳ ዘንድ ከዚያ ከነገረው መነኰሴ ጋር ሌላ መነኵሴ ላከ። እነርሱም በጒዞ ላይ በጐዳና ሳሉ ገና ሳይደርሱ አባ መቃርስ እንደልማዱ ወደ ወጥመዱ ሔደ በአንዲት ወጥመድ የተያዙ ሦስት ቆቆችን አገኘ እንዲህም ብሎ አሰበ "ጌታዬ እሊህን የሰጠኝ እኔን ሊፈትነኝ ነውን። ወይስ ከዚች ዕለት በፊት ሆዴ ያልጠገበች ኑራለችን ወይስ ለሌላ ነው እንዳልል በዚህ በረሀ ውስጥ ከሰው ወገን ያየሁት የለም"። እንዲህም እያሰበ ሳለ ከሊቀ ጳጳሳቱ የተላኩት እሊህ መነኰሳት ደረሱ በአያቸው ጊዜ ደስ አለው "ችግረኞነቴን አውቀህ ለአገልጋዩችህ ቅዱሳን ምግባቸውን የሰጠኸኝ አቤቱ አመሰግንሃለሁ" ብሎ ሰገደ። እነርሱ ግን ማዕድ ሠርቶ አዘጋጅቶ እስከአቀረበላቸው ድረስ ይጠቃቀሱበት ነበር።
❤ ከዚህም በኋላ አቅርቦላቸው "ንሱ አባቶቼ ባርኩና ተመገቡ" አላቸው እርሱም የራሱን ድርሻ ይዞ እስከጨርስ ያለ መነጋገር በጸጥታ ተመገበ። ከዚህም በኋላ ዓይኖቹን ቀና ቢያደርግ እንዳልበሉ አየ "አባቶቼ እንዴት አልበላችሁም" አላቸው "እኛ መንኰሳት ስለሆን ሥጋ አንበላም ትኅርምትም አለን" አሉት እርሱም ተዋቸው አላስገደዳቸውም እነዚያን ያበሰላቸውን ቆቆች አንሥቶ ሦስት ጊዜ እፍ አለባቸው ያን ጊዜም ድነው በረሩ ወደ ቦታቸውም ሔዱ እነዚያ መነኰሳትም ይህን ተአምር አይተው ደነገጡ "የእግዚአብሔር ቅዱስ ሆይ በደላችንን ይቅር በለን ብለው" ሰገዱለት እርሱም "የሁላችንንም በደል እግዚአብሔር ይቅር ይበለን" አላቸው።
❤ ከዚህም በኋላ ወደ አገራቸው ተመልሰው ያዩትን ይህን ድንቅ ተአምር ለሊቀ ጳጳሳቱ ነገሩት እርሱም ሰምቶ አደነቀ ወደ ንጉሡም እንዲህ ብሎ ላከ "በዘመናችን ጻድቅ ሰው መነኰስ ተገኝቷልና አንተም ና ሒደን በረከቱን እንድንቀበል" አለው። ወዲያውኑ ንጉሥ ከሠራዊቱ ጋር ተነሣ ሊቀ ጳጳሳቱም ከካህናቱ ጋር አባ መቃርስ ወዳለበት እነዚያ መነኰሳት እየመሩአቸው ሔዱ ወደርሱም ሲቀርቡ ወደ ብሔረ ሕያዋን ያደርሰው ዘንድ መልአክ አንሥቶ በክንፎቹ ተሽክመው ሲያርግም በአዩ ጊዜ "የእግዚአብሔር ቅዱስ ሆይ ባርከን የምንድንበትን አንዲት ቃል ንገረን" ብለው ጮኹ። እርሱም "ከሐሜትና ከነገር ሥራ አንደበታችሁ ይከልከል። ካህን ብዙ ባይማር ትዕቢትና መታጀር ባልመጣበት ነበር መነኵሴም ትኅርምት ባያበዛ ባልተመካም ነበር ርስበርሳችሁ ተፋቀሩ እግዚአብሔርም አድሮባችሁ ይኑር" አላቸው። ይህንንም ብሎ ዐረገ ከዐይናቸውም ተሠወረ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ መቃርስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #አባ_በጽንፍርዮስ፦ ይህም የከበረ መነኰስ በምስር አገር በወንዝ ዳር በአለች በሊቀ መላእክት በቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ መንኵሶ ታላቅ ተጋድሎን ሲጋደል ኖረ ስቀናች ሃይማኖትም ከእስላሞች መሳፍንት ጋር ተከራከረ የጌታችን ክርስቶስንም መለኮቱን ገለጠላቸው አምላክነቱንም አስረዳቸው ስለዚህም እስላሞች በአፈሩ ጊዜ ተቆጡ ጽኑዕ ሥቃይንም አሠቃዩት ራሱንም በሰይፍ ቆረጡ የሰማዕትነት አክሊልን በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም አባ በጽንፍርዮስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #አባ_አብራኮስ፦ ይህም ቅዱስ አባት ከላይኛው ግብጽ ነው። ዕድሜው ሃያ ዓመት ሲሆን መንኵሶ መልካም የሆነ ታላቅ ተጋድሎን ተጋደለ። ሰይጣንም ከእርሱ ጋር በመጣላት በተሸነፈና በደከመ ጊዜ በእርሱም ላይ ምንም ምን ማድረግ ባልተቻለው ጊዜ ፊት ለፊት ተገልጦ መጥቶ "እነሆ ከዚህ ዕድሜህ ሌላ ኀምሳ ዓመት ቀረህ" አለው። በዚህም ወደ ስንፍና ሊጥለው ወዶ ነው ሽማግሌውም እንዲህ ብሎ መለሰለት "አሳዘንከኝ እኔ ሌላ መቶ ዓመት እኖር ዘንድ ስለአሰብኩ ቸለል ብያለሁ አንተ እንዳልከው ከሆነ ከቀድሞው እጅግ አብዝቼ እጋደል ዘንድ ይገባኛል"። ከዚህም በኋላ ተጋድሎውንና በገድል መጸመድ አበዛ ሰባ ዓመታትም ከተጋደለ በኋላ በዚያች ዓመት ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ አብራኮስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የታኅሣሥ13 ስንክሳር።
✝ ✝ ✝
❤ "#ሰላም_ለመቃርዮስ_ዘተመሥጠ_መልዕልተ። በቅድመ ጉቡአን ይንብብ ዘይብል ቃላተ። እምኢያእመሩ ትዕቢተ ወዘይመስሎ ትምክህተ። እመ ኢያፈድፈደ ካህን ትምህርተ። ወእመ ኢያብዝኀ ካዕበ መነኰስ ትኅርምተ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የታኅሣሥ_13።
@sigewe
https://t.me/joinchat/AAAAAFGQ22bI0Ij80hYpFA
https://www.facebook.com/profile.php?id=61552828743736&mibextid=ZbWKwL