✔️ኬቨን ካርተር የሚባል ፎቶግራፈር። ትንሿ ልጅ በረሃብ ምክንያት ልትሞት አጎንብሳ ባለበት። በዛው ትይዩ ልጅቷ እስከምትሞት ድረስ ትዕግስት አጥቶ ሲጠብቅ የሚያሳይ አንድ አሞራ በአጋጣሚ አግኝቶ ፎቶ አንስቶ ነበር። በኋላም በዚህ ሥዕል የፑሊትዘር ሽልማት በ1984 ዓ.ም አሸነፈ። ነገር ግን ከዚያ በኋላ ጥቂት ወራት ብቻ ነው የኖረው። ምክንያቱም ለሞት የሚያበቃ ከባድ የመንፈስ ጭንቀት ውስጥ ሊወድቅ ችሏል።
ከመጽሔት እስከ መጽሔት፣ ከቴሌቭዥን እስከ ቴሌቪዥን፣ በዓለም ዙሪያ ባከናወነው ስኬት ተደስቷል። የመንፈስ ጭንቀት የጀመረው በአንድ የቴሌቭዥን ፕሮግራም ላይ ከአንድ ተመልካች ጋር የስልክ ቃለ ምልልስ ካደረገ በኋላ ነው። ሰውዬው በስልክ ደውሎ “ከፎቶው በኋላ ትንሿ ልጅ ምን ሆና ይሆን?” ሲል ጠየቀው።
እሱም መለሰ፡- ወደሃገሬ ለመመስ በረራ ስለነበረብኝ ቀጥሎ የሚሆነውን ለማወቅ አልጠበቅኩም።
ደዋዩ፡- “እነግርሃለሁ በዚያ ቀን ሁለት አሞራዎች ነበሩ። አንደኛው ፎቶውን ያነሳው ሰው ነበር!”
የዚህ እንግዳ ቃል በአእምሮው ውስጥ ደጋግሞ አቃጨለበት፤ ወደ ከፍተኛ ድብርት መራው እና.. በመጨረሻም እራሱን አጠፋ!።😢
#like እና ሼር አድ በማድረግ ቻናላችንን ለወዳጆ ይጋብዙ ❤
https://youtube.com/@jesus_smri?si=jH9uuYfHkdVq2zOK