Репост из: AI-IKHILAS
ልቦና በህይወትና በሞት ደረጃ ከሆነ ልቦችን በሶስት ከፍለን መመልከት አንችላለን፡-
1. ሰላማዊ የሆነች ቀልብ፡ በማንኛውም መልኩ ሰላማዊ የሆነችና ሽርክ የሌለባት
ቀልብ ነች፡፡ ይልቁንም በመውደድ፣ በፍላጎት፣ በመመካት፣ ተጸጽታ በመመለስ፣
በመዋደቅ ፣ በመፍራት እና በተስፋ አላህን ጥርት አድርጋ ታመልካለች ፡፡
ከወደደች ለአላህ ብላ ትወዳለች ፤ ከጠላች ደግሞ ለአላህ ብላ ትጠላለች ፤
ከሰጠች ለኣላህ ብላ ትሰጣለች ፤ ከከለከለች ደግሞ ለአላህ ብላ ትከለክላለች ፤
በማንኛውም ነገሯ ዳኛዋ በረሡል صلى الله عليه وسلم ላይ የወረደው ህግ ነው ፤ በዓቂዳም
በንግግርም በተግባርም ከአላህ ህግ ውጭ ሌላን አታስቀድምም፡፡
2. የሞተች ቀልብ፡ ምንም ህይወት የሌላት ነች ፤ ጌታዋን አታውቅም፣ አትገዛም ፣
ትእዛዙን አታከብርም፣ አላህ የሚወደውን አትሰራም፤ ይልቁንም የአላህ ቁጣ
እና ጥላቻ ቢኖርበት እንኳ ከስሜቷ ጋር ነው የምትንቀሳቀሰው ፤ ፍርሃቷም፣
ተስፋዋም፣ ውዴታዋም ጥላቻዋም፣ ማላቋም ማዋረዷም ከአላህ ውጭ ነው፡፡
ስትወድም ስትጠላም ስትሰጥም ስትከለክልም ለስሜቷ ነው፡፡ ስሜትና የዱንያ
ፍላጎቷ ኢማሟ (መሪዋ) ፤ ማህይምነት ሹፌሯ ፤ ዝንጋቴ መርከቧ ነው፡፡
3. ህይወትና በሽታ የተቀላቀለባት ቀልብ፡ ይህች ቀልብ ሁለት ገጽታዎች ያሏት ሲሆን
አንዳንድ ጊዜ አንድኛው ገጽታ በሌላ ጊዜ ደግሞ ሌላኛው ገጽታ ያሸንፋታል፡፡
እርሷ ከሁለቱ ወዳሸነፈው ትሆናለች ፡፡ በውስጧ የአላህ ውዴታ፣ ኢማን፣ ኢኽላስ እና ተወኩል አላት፡፡ ይህ የህይወት ገጽታዋ ነው ፤ ስሜት፣ ምቀኝነት፣ ኩራት፣ በራስ መደነቅ እና የበላይነትን መፈለግ የጥፋትና የክስረት ገጽታዋ ነው፡፡
https://t.me/AlIkhilasmedresa