#ሰበር_ዜና! የነበልባሎ ክፍለጦር አዛዥ የነበረው ሻለቃ ጌታሁን መኮነን የሰሜን አቸፈር ወረዳ መቀመጫ የሆነችውን ሊበን ከተማን ተቆጣጠረ። ሻለቃ ጌታሁን በሁመራ ግምባር፣ ሸረሪና ላይ የነበልባሉን ክፍለጦር እየመራ ከሕወሓት ጋር ሲዋጋ እንደነበር ይታወቃል። ቆስሎ ህክምና ላይ ቢሆንም ከሥርዓቱ ጋር አልተባበርም በማለት ዛሬ ማለዳ የሰሜን አቸፈር ወረዳን ከተማ ተቆጣጥሯል። ሻለቃ ጌታሁን የሚመራው ፋኖ በጀግናው አርበኛ አያሌው መኮነን ስም "አያሌው ብርጌድ" የሚል ስም ተሰጥቶታል። በአሁኑ ሰዓት በሊበን ከተማ ከህዝቡ ጋር በመወያየት የፋኖ ኮማንድ ፖስት ተቋቁሟል።
ማንኛውንም ሀሳብና አስተያየት በዚህ ሊንክ መላክ ይችላሉ @Tadeletibebut
ማንኛውንም ሀሳብና አስተያየት በዚህ ሊንክ መላክ ይችላሉ @Tadeletibebut