طالبات العلم "ጧሊበተል ዒልም"


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


ጧሊባቱል ኢልም የቂርአት እና የቲሞችን መርጃ ማእከል
https://t.me/joinchat/AAAAAEiNUs3gAKq0F39w0g
@Talibatul1ilm_bot
ይህ 👆 የአስተያየት መስጫ ነው ያሎትን አስተያየት ያካፍሉን

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


اللهم اجعلنا
مفاتيح للـخير
مغالـيق للـشر
نساعد و ننصح
من نعرف ومن لا نعرف
ونعوذ بك من آفة الغرور
ونسألك التواضع وحسن الخاتمة


ከአላህ የራቅክ እንኳን ብትሆን ስለርሱ ለሰዎች ተናገር፣ፃፍ ምናልባት ንግግርህ አስተጋብቶ በውስጥህ ሲመላለስ ይመልስህ ይሆናል…


√ እድል አለ !

«እድል በየትኛዉ ቀዳዳ በኩል እንደሚመጣ አታዉቂም ስለዚህ አትዘናጊ ባገኘሽው አጋጣሚ ሁሉ ተጠቀሚ ወደኃላ አትበይ ! ወደ ፊት ሂጂ !ʔ




"የነገ ሟች የዛሬን ሟች ይቀብራል።"
ሀሰን አል-በስሪይ


የሹዐይብ ጥሪ!
~
((وَيَا قَوْمِ أَوْفُوا الْمِكْيَالَ وَالْمِيزَانَ بِالْقِسْطِ ۖ وَلَا تَبْخَسُوا النَّاسَ أَشْيَاءَهُمْ وَلَا تَعْثَوْا فِي الْأَرْضِ مُفْسِدِينَ * بَقِيَّتُ اللَّهِ خَيْرٌ لَكُمْ إِنْ كُنْتُمْ مُؤْمِنِينَ ۚ وَمَا أَنَا عَلَيْكُمْ بِحَفِيظٍ)
«ሕዝቦቼም ሆይ! ስፍርንና ሚዛንን በትክክል ሙሉ፡፡ ሰዎችንም ምንም ነገራቸውን አታጉድሉባቸው፡፡ በምድርም ውስጥ አጥፊዎች ሆናችሁ አታበላሹ፡፡ አላህ ያስቀረላችሁ ለእናንተ የተሻለ ነው፡፡ ምእመናን እንደሆናችሁ (አላህ በሰጣችሁ ውደዱ)፡፡ እኔም (መካሪ እንጅ) በናንተ ላይ ተጠባባቂ አይደለሁም፡፡» [ሁድ: 85–86]


https://chat.whatsapp.com/LPxsxAjSnS7JXGaKEkulXZ


ይህ በጧሊባት ኢልም በየአመቱ የቲሞች እና ሚስኪኖች የረመዳን አስቤዛ (መጋዲ) የምናዘጋጅበት ግሩፕ ነው ያለው ለሌለው ሽፍን ሁኖ የአላህን ወዴታ በማሰብ የቻልነውን በመዘርጋት ሚስኪኖችት እና የቲሞችን በማስፈጠር አጅር ለምፈልጉ የቻላችሁትን ያክል ለማዋጣት በዚህ ሊንክ ተቀላቀሉ በማለት ጧቷሊባቱል ኢልም ጥሪ ያቀርባል




✎የቀልብ ሂወት ቁልፉ፦

~ቁርአንን በማስተንተን መቅራት
~ሌሊቱ መጨረሻ አካባቢ ወደ አላህ መተናነስ
~ወንጀልን መተዉ።


https://chat.whatsapp.com/LPxsxAjSnS7JXGaKEkulXZ


ይህ በጧሊባት ኢልም በየአመቱ የቲሞች እና ሚስኪኖች የረመዳን አስቤዛ (መጋዲ) የምናዘጋጅበት ግሩፕ ነው ያለው ለሌለው ሽፍን ሁኖ የአላህን ወዴታ በማሰብ የቻልነውን በመዘርጋት ሚስኪኖችት እና የቲሞችን በማስፈጠር አጅር ለምፈልጉ የቻላችሁትን ያክል ለማዋጣት በዚህ ሊንክ ተቀላቀሉ በማለት ጧቷሊባቱል ኢልም ጥሪ ያቀርባል


በዚህ ዑማ ህዝብ ላይ
የምፈራለት ነገር ቢኖር የምላስ
አሊምነት የልብ ጃሂልነትን ነው!!
   "
  "   ዑመር አል ፋሩቅ"


~የጀመራችሁት በጎ ሥራ ካለ ጨርሱ፤
ያቋረጣችሁት ጥሩ ነገር ካለ ቀጥሉ፤
ያልጀመራትሁት መልካም ነገር ካለ ጀምሩ፤
የያዛችሁትን ከዳር አድርሱ እንደገና ጀምሩ ቀጥሉ ጨርሱ ሕይወት መጀመር፣ መቀጠል፣ መጨረስ ናት ዕድሜ ማለት መወለድ፣ መኖር፣ መሞት ነውና።


ሪዝቅን የሚያመጡ  አራት ነገሮች

~የለሊት ሶላት
~ እስቲግፋር
~ዚክር እና
~ ሶደቃ ናቸው።


~አንዳንድ ንግግሮች አሉ ከአላህ ዘንድ አጅር የማናገኝባቸው፤ ለስኬትም የማንበቃባቸው፡፡ አንዳንድ ወሬዎች አሉ ለዱንያችን የማይጠቅሙን ፣ለአኺራችንም የማይፈይዱን፡፡ አንዳንድ ወጎችም አሉ ወደ ጀነት የማይመሩን ከእሣትም የማያድኑን፡፡ ወይ ዚክር ሆነው አላህን አላወሳንባቸው ወይ ደግሞ ሹክር አይደሉ አምላካችንን አላመሰገንባቸው፡፡

የዚህ ዓይነቶቹ ወሬዎችና ንግግሮች«ማላ የዕኒ» ይላቸዋል እስልምና፡፡ የማይመለከቱን ጉዳዮች፣ ዝባዝንኬዎች፣ አሉባልታዎች፣ እንቶፈንቶዎች፣ እርባና ቢስ ጉዳዮች ልትሏቸው ትችላላችሁ፡፡ ወዳጆቼ … በዚህ ዓይነቱ ማዕድ ላይ ድንገት ከገባችሁ እንኳን ብዙ አትቆዩ፤ ቁም-ነገር ካጣችሁና ጥቅሙ ካልታያችሁ ቶሎ ዉጡ፡፡ ጊዜያችሁ ይቃጠላልና፡፡ ትልቁን ሀብታችንን ጊዜን አቃጠልን ማለት ትልቅ ኪሣራ ላይ ወደቅን ማለት ነው፡፡

ወደዚህ ዓለም የመጣነው ለቁምነገር ነውና እኛን የሚመለከቱን ጉዳዮች «ቁምነገሮች» ናቸው፡፡ ነፍሣችንን የምንጠቅምባቸው፣ ሌሎችን የምንፈይድባቸው፣ ዓላማችንን የምናሳካባቸው፣ ኻቲማችንን የምናሳምርባቸው፡፡

የሆነ ጊዜ ላይ ከሆነ ሰው ጋር ረጅም ጊዜ ወሬ ልታወሩ ትችላላችሁ፡፡ ቀኑን ሙሉ ጊዜ ወስዳችሁ ወይም ሙሉ ሌሊቱን እንቅልፍ አጥታችሁ ፌስ ቡክ ላይ አፍጣችሁ ከአንድ ግሩፕም ገብታችሁ ሀሳብ ልትለዋወጡ ወይም እዚያው አካባቢ ፈንጠር ብላችሁ በመቆም ሀሳብ የሚለዋወጡትን ትታዘቡ ይሆናል፡፡ 

አንዳንድ ጊዜ ግን ቆም ብላችሁ የዕለት ቻታችሁንና የግሩፕ ዉሏችሁን ስትገመግሙና ፍሬውን መልቀም ስትሞክሩ ዉጤቱ ባዶ ይሆንባችኋል፡፡ ባዶ፡፡ ምሽት እቤቴ በር ላይ ስደርስ «ወይኔ ዛሬም ወድቄ ገባሁ!» ብዬ ከራሴ ጋር የማወራባቸው አጋጣሚዎች እጅግ ብዙ ናቸው፡፡ በጣም ብዙ!! መውደቅ በኃጢአት ብቻ አይደለም፤ በተጨመረ ዕድሜ ላይ ምንም መልካም ነገር ሳይጨምሩ መዋልም መዉደቅ ነው፡፡ ዕድሜ የተሠጠው ለዓላማ ነውና፡፡

ሳያጣሩ መረጃን ማሠራጨት፣ የሰሙትን ነገር ሁሉ ለማውራት መቸኮል፣ በማያገባ ነገር ገብቶ መፈትፈት፣ እዚህም እዚያም ሄዶ መከራከር፣ አዋቂ መስሎ ለማስረዳት መሞከርና … ሌላው የጊዜው ማላ የዕኒ ነው፡፡ ዛሬ ላይ ማንን መስማት እስኪያቅተን ድረስ ሁሉም ተንታኝ፣ ሁሉም መካሪ፣ ሆኗል፡፡ የሚችለውም የማይችለውም፣ የሚያገባውም፣ የማያገባውም ይናገራል፡፡ የዚህ ዓይነቱ ባህሪ የጥሩ ሙስሊም መገለጫ አይደለም፡፡ የአንድ ሰው እስልምና ማማርን ከሚያመለክቱ ነገሮች መካከል አንዱ የማይመለከተውን ነገር መተዉ ነው፡፡ አንዳንድ ዝምታና ከሰው መገለል ጥሩ ነው፡፡ ትኩረትህን ይሰበስብላህል፡፡ ጊዜህን ሙጥጥ አድርገህ ለዉጤታማ ሥራ እንድትጠቀምበት ያግዝሃል፡፡

እናም ወዳጆቼ … ለጊዜያችን በትልቁ እንጨነቅ፡፡ እያንዳንዷን ሰከንድ በምን ላይ እንዳዋልናት መለስ ብለን እንቃኝ፡፡ ምድር ላይ የምናሳልፋትን ይህችን አጭር የሀምሳ እና ስልሳ ዓመት ዕድሜ ከተራ ብዙ ነገሮች ይልቅ ጥቂት ቋሚና ጠቃሚ ቅርሦችን እንለፍ፡፡ መዝናናት መቀለዳችንም በልክ ይሁን፡፡ መልካም ሥራችን ይብዛ ይክበድም፡፡ የነገ ሥራችን ይመዘናል እንጂ አይቆጠርም፡፡ ከመልካም ሥራ በላይም ምንም ዋስትና የለንም፡፡

አምላኬ ሆይ ! አንተን በማውሳት፣ በማመስገንና አምልኮህን በማሳመሩ ላይ እርዳኝ፡፡

አምሹልኝ!


~አንዳንድ ሰዎች የመጀመሪያ የጁሙዓ አዛን ካለ ብኃላ እየተነሱ ሱና ሶላቶችን ይሰግዳሉ።ይህን ተግባር የሚደግፍ ምንም አይነት ሶሂህ ሐድስ የለም።

ስለዚህ ከጁሙዓ በፊት የሚሰገድ ምንም አይነት ሱና ሶላት የለም!


«አላማሽን ለሰዎች አትናገሪ  ይልቅ አላማሽ ደብቂ እና ዉጤትሽን አሳያቸዉ !»


Репост из: طالبات العلم "ጧሊበተል ዒልም"
➣ምርጡን ህይወት ያገኘነው
በትግስት ውስጥ ነው::
➤ዑመር አል ፋሩቅ


Репост из: طالبات العلم "ጧሊበተል ዒልም"
🍃اللهم لا تجعلنا من الخاسرين


~አንዳንድ ጊዜ በሥራችን የማናገኛቸው ነገርግን በንያችን የምናገኛቸው ትላልቅ ምንዳዎች ይኖራሉ። ካላማረ ሥራ ያማረ ንያ በእጅጉ ይበልጣልና።
ወዳጆቼ ለረመዷን ምን አሰብን?
 ብንደርስም ባንደርስም ከወዲሁ ለረመዷን የበጎ ሥራ ዕቅዶቻችንን እንንደፍ። ሞት እንኳን ቢቀድመን የሥራውን ምንዳ ብናጣ የንያችንን ምንዳ እናገኛለንና።
ታላቁን እንግዳ ልንቀበለው ከ 80 ቀን ያነስ ጊዜ ቀርቶናል። አላህ ከሚደርሱና ከሚፆሙት ያድርገን።


~በጎ ነገሮችን በሰፊው የምንዘራበት በረከተ- ብዙው ረመዷናችን እየመጣ ከ ሦስት ወር ያነሰ ነው የቀረው። ከወዲሁ ቀልባችንን አለስልሰን እንጠብቀው። ረመዷን ከመግባቱ በፊት ያለሰለሰ ቀልብ ቁርኣን ዘልቆት አይገባውም። ከረመዷንም ተጠቃሚ ሊሆን አይችልምና ከወድሁ ዚክርን፣ቁርኣንን፣ሱና ሶላቶችን፣ሱና ፆሞችን፣የለይል ሶላቶችን… እናለማምደው።

Показано 20 последних публикаций.