~አንዳንድ ንግግሮች አሉ ከአላህ ዘንድ አጅር የማናገኝባቸው፤ ለስኬትም የማንበቃባቸው፡፡ አንዳንድ ወሬዎች አሉ ለዱንያችን የማይጠቅሙን ፣ለአኺራችንም የማይፈይዱን፡፡ አንዳንድ ወጎችም አሉ ወደ ጀነት የማይመሩን ከእሣትም የማያድኑን፡፡ ወይ ዚክር ሆነው አላህን አላወሳንባቸው ወይ ደግሞ ሹክር አይደሉ አምላካችንን አላመሰገንባቸው፡፡
የዚህ ዓይነቶቹ ወሬዎችና ንግግሮች«ማላ የዕኒ» ይላቸዋል እስልምና፡፡ የማይመለከቱን ጉዳዮች፣ ዝባዝንኬዎች፣ አሉባልታዎች፣ እንቶፈንቶዎች፣ እርባና ቢስ ጉዳዮች ልትሏቸው ትችላላችሁ፡፡ ወዳጆቼ … በዚህ ዓይነቱ ማዕድ ላይ ድንገት ከገባችሁ እንኳን ብዙ አትቆዩ፤ ቁም-ነገር ካጣችሁና ጥቅሙ ካልታያችሁ ቶሎ ዉጡ፡፡ ጊዜያችሁ ይቃጠላልና፡፡ ትልቁን ሀብታችንን ጊዜን አቃጠልን ማለት ትልቅ ኪሣራ ላይ ወደቅን ማለት ነው፡፡
ወደዚህ ዓለም የመጣነው ለቁምነገር ነውና እኛን የሚመለከቱን ጉዳዮች «ቁምነገሮች» ናቸው፡፡ ነፍሣችንን የምንጠቅምባቸው፣ ሌሎችን የምንፈይድባቸው፣ ዓላማችንን የምናሳካባቸው፣ ኻቲማችንን የምናሳምርባቸው፡፡
የሆነ ጊዜ ላይ ከሆነ ሰው ጋር ረጅም ጊዜ ወሬ ልታወሩ ትችላላችሁ፡፡ ቀኑን ሙሉ ጊዜ ወስዳችሁ ወይም ሙሉ ሌሊቱን እንቅልፍ አጥታችሁ ፌስ ቡክ ላይ አፍጣችሁ ከአንድ ግሩፕም ገብታችሁ ሀሳብ ልትለዋወጡ ወይም እዚያው አካባቢ ፈንጠር ብላችሁ በመቆም ሀሳብ የሚለዋወጡትን ትታዘቡ ይሆናል፡፡
አንዳንድ ጊዜ ግን ቆም ብላችሁ የዕለት ቻታችሁንና የግሩፕ ዉሏችሁን ስትገመግሙና ፍሬውን መልቀም ስትሞክሩ ዉጤቱ ባዶ ይሆንባችኋል፡፡ ባዶ፡፡ ምሽት እቤቴ በር ላይ ስደርስ «ወይኔ ዛሬም ወድቄ ገባሁ!» ብዬ ከራሴ ጋር የማወራባቸው አጋጣሚዎች እጅግ ብዙ ናቸው፡፡ በጣም ብዙ!! መውደቅ በኃጢአት ብቻ አይደለም፤ በተጨመረ ዕድሜ ላይ ምንም መልካም ነገር ሳይጨምሩ መዋልም መዉደቅ ነው፡፡ ዕድሜ የተሠጠው ለዓላማ ነውና፡፡
ሳያጣሩ መረጃን ማሠራጨት፣ የሰሙትን ነገር ሁሉ ለማውራት መቸኮል፣ በማያገባ ነገር ገብቶ መፈትፈት፣ እዚህም እዚያም ሄዶ መከራከር፣ አዋቂ መስሎ ለማስረዳት መሞከርና … ሌላው የጊዜው ማላ የዕኒ ነው፡፡ ዛሬ ላይ ማንን መስማት እስኪያቅተን ድረስ ሁሉም ተንታኝ፣ ሁሉም መካሪ፣ ሆኗል፡፡ የሚችለውም የማይችለውም፣ የሚያገባውም፣ የማያገባውም ይናገራል፡፡ የዚህ ዓይነቱ ባህሪ የጥሩ ሙስሊም መገለጫ አይደለም፡፡ የአንድ ሰው እስልምና ማማርን ከሚያመለክቱ ነገሮች መካከል አንዱ የማይመለከተውን ነገር መተዉ ነው፡፡ አንዳንድ ዝምታና ከሰው መገለል ጥሩ ነው፡፡ ትኩረትህን ይሰበስብላህል፡፡ ጊዜህን ሙጥጥ አድርገህ ለዉጤታማ ሥራ እንድትጠቀምበት ያግዝሃል፡፡
እናም ወዳጆቼ … ለጊዜያችን በትልቁ እንጨነቅ፡፡ እያንዳንዷን ሰከንድ በምን ላይ እንዳዋልናት መለስ ብለን እንቃኝ፡፡ ምድር ላይ የምናሳልፋትን ይህችን አጭር የሀምሳ እና ስልሳ ዓመት ዕድሜ ከተራ ብዙ ነገሮች ይልቅ ጥቂት ቋሚና ጠቃሚ ቅርሦችን እንለፍ፡፡ መዝናናት መቀለዳችንም በልክ ይሁን፡፡ መልካም ሥራችን ይብዛ ይክበድም፡፡ የነገ ሥራችን ይመዘናል እንጂ አይቆጠርም፡፡ ከመልካም ሥራ በላይም ምንም ዋስትና የለንም፡፡
አምላኬ ሆይ ! አንተን በማውሳት፣ በማመስገንና አምልኮህን በማሳመሩ ላይ እርዳኝ፡፡
አምሹልኝ!