ተጠናቀቀቀ😍😍
ሁለት መልክ የነበረውን ዩናይትድ ባየንበት ምሽት በኦልድትራፎርድ ዩናይትድ ከመመራት በኋላ አሸንፏል በመጀመሪያው አጋማሽ በተጨዋቾች ድክመት ፍርሃት እንዲሁም በአሰልጣኙ የተጨዋቾች ምርጫ ቡድኑ በጣም ደካማ ነበር... ዶርጉን በቀኝ ዊንግባክ መጠቀሙ ጥያቄ ያስነሳል የግራግር የቀኝ ዋንግባክ ወደ አማካዮች እየገባ መንቀሳቀስ ይችላል እንጂ መስመሩን ታኮ ለማጥቃት ሚቸገርባቸው ሁኔታዎች ብዙ ናቸው.. ልጁግን እንደ መጀመሪያ ጌሙ እንቅስቃሴው መጥፎ አልነበረም በአንፃሩ በግራ እየተጫወተ ያለው ዳሎ በመጀመሪያው አጋማሽ ለማየት ይቀፍ ነበር
በመጀመሪያው አጋማሽ ቡድኑ ፕሮግረስ እያደረገ ወደፊት ለመጠጋት ከብዶት ብዙ ባክፓስ ሲጫወቱ ነበር...
በሁለተኛው አጋማሽግን በጣም የተሻለውን ዩናይትድ አይተናል በተለይ ጋርናቾ መግባቱ የቡድኑን እንቅስቃሴ አፍጥኖታል በሚገባ ጋርና ጫና የፈጠረ በመሆኑ በሁለቱም መስመሮች ቡድኑ ተመጣጣኝ አቅም ነበረው ይህደሞ ለሌስተሮች ነገሮችን ከባድ አድርጎባቸዋል... የጋርናቾ ከፊትጫና መፍጠር ለዳሎም የተመቸው ይመስል ነበር በእርግጥ ዳሎ በሁለተኛው አጋማሽ ወደ አማካዮች እየተጠጋ ስለሚቆይ ወደላይ ከፍብሎ ሚገኝ የነበረው ዮሮነበር ይህ ድንቅልጅ ኳስተልተሎ ወደፊት ስለሚልክና የሌስተሮችን እንቅስቃሴ ይገታው ስለነበር ጋርናቾን የበለጠ ጫና ፈጣሪ አድርገውታል...
ለኔግን ምርጡ የአሞሪም ውሳኔ ዚርክዚን ወደሜዳ ሲልክ ሆይሉንድን አለማስወጣቱነው ሆይሉንድ የራሱ ድክመቶች አሉት ነገርግን ሁሌም የተጋጣሚውን ተከላካይ መስመር ለመረበሽ አይሰንፍም ሆይሉንድ ከፊት ስለቆየ ከሱ ጀርባ ዚርክዚ ያደርግ የነበረው እንቅስቃሴ በጣም ምርጥ ነበር ሁሉንም ነገር የቀየረው እሱልጅነው እያንዳንዱ ንክኪው ስኬታማ ውጤታማ ነበሩ... አማድ የቀኝ ሙሉ ኮሪደሩን ስለያዘለት ዚርክዚ አማካይና አጥቂውን ሚያገናኝ ድልድይ ፈጥሮ ጫና መፍጠር እንዲችሉ ረድቷል
አሳማኝ አደለም ግን ተደሰቱ ለጊዜው 😂👍
#
@the_red_forever_mv