#Ethiopia
“ላለፉት ስድስት ዓመታት፤ ብታምኑም ባታምኑም አንድ ሰው ኢትዮጵያ ውስጥ torture አይደረግም። በዚህ እኛ እንኮራለን” - ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ያሉ ግጭቶች ጠንሳሾች፤ “ትላንትና ፖለቲካ ሲያንቦራጭቁ የነበሩ ሰዎች ናቸው” አሉ።
በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ግጭቶች “ጠንሳሽ” እና “ጨማቂዎች”፤ “ትላንትና ፖለቲካ ሲያንቦራጭቁ የነበሩ ሰዎች ናቸው” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ (ዶ/ር) ወነጀሉ።
አቢይ በሚመሩት ብልጽግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ መክፈቻ ላይ ዛሬ ባደረጉት ንግግር፤ ባለፉት ስድስት ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ “ሰው torture አይደረግም” ሲሉ ተደምጠዋል።
ገዢው ፓርቲ እስከ መጪው እሁድ ጥር 25፤ 2017 ዓ/ም የሚቆየውን ሁለተኛ ጠቅላላ ጉባኤ እያካሄደ ያለው፤ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የመሰብሰቢያ አዳራሽ ነው።
የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዝዳንት የሆኑት አቢይ፤ ፓርቲው ቃል ከገባቸው ጉዳዮች መካከል “በኢትዮጵያ ቶርቸር ይቁም” የሚለው አንዱ እንደነበር አስታውሰዋል።
ብልጽግና ፓርቲ “ባለፉት ጥቂት ዓመታት” በተጓዘበት “የመጀመሪያ ምዕራፍ” ካሳካቸው ጉዳዮች አንዱ፤ ይኸው እንደሆነም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለጉባኤው ታዳሚያን ተናግረዋል።
“ላለፉት ስድስት ዓመታት፤ ብታምኑም ባታምኑም አንድ ሰው ኢትዮጵያ ውስጥ torture አይደረግም። በዚህ እኛ እንኮራለን” ብለዋል አቢይ።
በዚህ ንግግራቸው “ፖለቲካን በቅጡ አልተለማመዱም” ያሏቸውን “አባቶች” ወርፈዋቸዋል። “አባቶቻችን ሀገርኛ ሀሳብ አላፈለቁም። በተዋሱት ሃሳብ ሲጨቃጨቁ፣ ሲጋደሉ የኖሩ ስለሆነ፤ አሁንም ያንን ማስቀጠል ይፈልጋሉ” ብለዋል። #EthiopianInsider
@ThiqahEth