TIKVAH-MAGAZINE


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ


ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን +251913134524

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций


በኢትዮ ጅቡቲ ባቡር መስመር ለመጓዝ ፋይዳ መታወቂያ ማቅረብ ግዴታ ሊሆን ነው።

የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር አክሲዮን ማህበር ከየካቲት 2017 አ.ም  ጀምሮ በኢትዮ ጅቡቲ ባቡር መስመር ለመጓዝ ተጓዦች ፋይዳ መታወቂያ ማቅረብ እንዳለባቸው አስታውቋል።

ዋና ስራ አስፈፃሚው ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከየካቲት 2017 ጀምሮ በኦንላይን ቦታ በማስያዝ የህዝብ መንገደኞች ትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ነው የገለጹት።

በዚህም ጥራት ያለዉና እና ቀልጣፋ የጉዞ አገልግሎት  ለመስጠት፣ ትክክለኛ የመንገደኛ መረጃን ለማረጋገጥ እና ከችግር የጸዳ ጉዞን ለማመቻቸት እንዲሁም የሀገር ውስጥ ተሳፋሪዎች ቦታ ለመያዝም ሆነ ለመጓዝ ብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) ማቅረብ በመስፈርትነት መቀመጡን ነው ያስታወቁት።

በኢትዮ ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት ባለፉት 6 ወራት 165 ሺህ 639 መንገደኞችንና 934 ሺህ ቶን ጭነት ማጓጓዝ መቻሉን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር መረጃ ያሳያል።

@tikvahethmagazine


በአዲስ አበባ የትምህርት ማስረጃ ማጣራት ሥራ በአፋጣኝ እንደሚጀመር ተገለጸ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ከአመራር እስከ ሰራተኛ ድረስ የትምህርት ማስረጃ ማጣራት ሥራ በአፋጣኝ እንደሚጀመር ገልጿል።

ቢሮው የትምህርት ማስረጃ የማጣራት ስራ ለማከናወን እና የተቀናጀ የመረጃ አያያዝ ስርዓት ኢስሚስ አተገባበር ላይ ከተቋማት ከተውጣጡ የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክተሮች ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡

በዚህ ወቅትም በከተማ አስተዳደሩ ከ90 ሺ በላይ የሚሆነው የመንግስት ሰራተኛ የመጀመሪያ ዲግሪና ከዛ በላይ የትምህርት ማስረጃ ያለው መሆኑን በቢሮው የሰው ሀብት ስራ አመራር ዘርፍ ኃላፊ አቶ መላኩ ታምሩ ገልጸዋል።

@tikvahethmagazine


ከ1ወር በፊት  በደረሰ ትራፊክ አደጋ 74 ሰዎች በሞቱበት ቦታ ላይ ተመሳሳይ አደጋ ደረሰ።

ሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ከ1ወር በፊት  በደረሰ ትራፊክ አደጋ 74 ሰዎች በሞቱበት ቦታ ላይ ተመሳሳይ አደጋ መድረሱን አስታወቀ።

በሲዳማ ክልል ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ቦና ወረዳ  ጥር 20 ቀን 2017 ዓ/ም ከምሽቱ  5፡30 ሰአት ገደማ  ሲኖትራክ መኪና ከሀዋሳ ወደ በንሳ ዳዬ በመጓዝ ላይ ሳለ መንገድ ስቶ  ገላና  ወንዝ ድልድይ  ገብቷል።

በአደጋው ሾፌሩና ረዳቱ ጉዳት  የደረሰባቸው   ሲሆን  በቦና ሆስፒታል ህክምና ላይ እየተደረገላቸው ይገኛል።

ከ1ወር በፊት በተመሳሳይ ሁኔታ በሲዳማ ክልል ቦና ዙሪያ ወረዳ በአይሱዙ የጭነት መኪና ተጭነው ከ75 በላይ ሰዎች ለሰርግ ሲሄዱ በደረሰ ሰቅጣጭ አደጋ 74 ሰዎች የሞቱ መሆኑ የሚታወስ ነው።

ከሟቾቹ ሰዎች ውስጥም ከ50 በላይ የሚሆኑት የአንድ ቤተሰብ አባላት እና ዘመዳሞች መሆናቸው መነገሩ ይታወሳል።

እንደ ፖሊስ ገለፃ ቦታው ጠመዝማዛና አደገኛ ቁልቁለትና ዳገታማ ቦታ በመሆኑ ዘላቂ መፍትሄ እስኪበጅ አሽከርካሪዎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል።

መረጃው የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ነው።

@tikvahethmagazine


#Update: በቴሌግራም የማጭበርበር ወንጀል ሲፈጽም የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ።

የግለሰቦችን የቴሌግራም አድራሻ በተለያዬ ዘዴ በመጥለፍ በስማቸው ሲያጭበረብር የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ከሰሞኑ የግለሰቦችን የቴሌግራም አካውንትን በመጠቀም የማጭበርበር ወንጀል ስለሚፈጽሙ ወንጀለኞች መበራከት ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ነበር።

በዚህም አንድ ወንጀለኛ የአንድ ግለሰብን የቴሌግራም አካውንት በመጥለፍ የተቸገረ በማስመሰል ገንዘብ ጠይቆ በማስላክ ለግል ጥቅሙ ሊያውል የነበረው ተጠርጣሪ በዛሬው ዕለት በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል።

የቢራሮ ክፍለ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር መሀመድ ይማም እንዳሉት ከሰሞኑ አንድ የግል ተበዳይ የቅርብ ቤተሰቡ የሆነች ልጅ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንዳለችና ገንዘብ እንደሚያስፈልጋት በቴሌግራም አድራሻዋ 340 ሽህ ጠየቀችው ያለውን 180 ሺህ ብር ከላከ በኋላ ሲያጣራ አድራሻዋ መጠለፉ ተረጋገጠ ብለዋል።

በዚህ መነሻነት ፖሊስ ተከታትሎ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ገልፀው አሁን አሁን በቴክኖሎጂ የተደገፈ የማጭበርበር ስራዎች እየጨመሩ መሆናቸውን አንስተዋል።

በመጨረሻም ወንጀል ፈፃሚዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ሂደት ማህበረሰቡ ላደረገላቸው ጥቆማ ያመሰገኑት ም/ኢንስፔክር መሀመድ ይማም  ወደ ፊትም ከፖሊስ ጎን እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።

መረጃው የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ነው።

@tikvahethmagazine


Addis Abeba's top and luxury apartment for sale
Bole - infront Bole Metemiya - (ቦሌ ማተሚያ)

👉 City View Luxury Apartments
👉 Built on Bole Main Road with Radisson Blu international hotel standard

We are offering more than 90% completed fully finished 2 bedroom and 3 bedroom apartments for sale.

📌 The apartment includes:

👉 Only 3/4 floor house (2 Buildings)
👉 Each apartments got digital carta
👉 4 modern elevators
👉 Standby electric generator
👉 Underground water is available and big capacity water tankers
👉 Modern garbage disposal on every floor
👉 24-hour security camera ...etc

For more information :

0920224609 | @Tsedalproperties


በኢትዮጵያ የሰብዓዊነት ትምህርት ቤት በቀይ መስቀል አማካኝነት ተቋቋመ።

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የሰላም፣ የግጭት-አልባ እና ሰብዓዊነት መርህዎች ላይ አተኩሮ ትምርት የሚሰጥ የሰብዓዊነት ትምህርት ቤት አቋቁሟል።

በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ለተመረጡ ሰልጣኞች ትምህርት ለመስጠት የተዘጋጀው ትምህርት ቤቱ የሥነ-ምግባር እና ሰብዓዊነት ላይ ያተኮሩ ኮርሶች ተቀርጸውለታል ተብሏል።

ትምህርት ቤቱ ለጊዜው በልዩ ዲፕሎም ትምህርት ለመስጠት ዝግጅቱን ቢያጠናቅቅም በሂደት ግን በመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪም ትምህርት ለመስጠት ውጥን ስለመያዙም ተነግሯል፡፡

“ለስልጠናው ትኩረት ያደረግናቸው በመጀመሪያ ለራሳቸው ሰልጥነው ከዚህ ስወጡ ደግሞ ማህበረሰቡን ለማሰልጠን የተዘጋጁትን ወጣቶች ነው” ሲሉ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ፕሬዝዳንት አበራ ቶላ ተናግረዋል።

አዲስ አበባ ሳሪስ አከባቢ በሚገኘው የማኅበሩ ማሰልጠኛ ማዕከል ትምህርቱን ለመስጠት መምህራንን ከማዘጋጀት ጀምሮ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁም የተነገረለት ሲሆን አሁን ላይ በመጀመሪያ ዙር ስልጠናው ትምህርት ቤቱ 50 ተማሪዎችን እንደሚቀበል ታውቋል፡፡

ከ1970ዎቹ ጀምሮ ኢትዮጵያ ውስጥ አገልግሎት መስጠት የጀመረው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ስድስት ሚሊየን አባላት እና 100 ሺህ በጎ ፈቃደኞች አሉት፡፡ 

ዘገባው የዶቼቬሌ ነው።

@tikvahethmagazine

23k 0 13 5 40

በአማራ ክልል ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት 112 ቢሊየን ብር ያስፈልጋል ተባለ

የአማራ ክልል ትምህርት ቤቶች በሰሜኑ ጦርነት እና አሁን ላይ በክልሉ ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት በመውደማቸው በርካቶች ከትምህርት ገበታቸው ውጪ መሆናቸው ይታወቃል።

በመሆኑም የክልሉ ትምህርት ቢሮ  ጉዳት የደረሠባቸውን ትምህርት ቤቶች መልሶ ለመገንባት 112 ቢሊየን ብር  እንደሚያስፈልግ አስታውቋል፡፡

በክልሉ ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት እና በሰሜኑ ጦርነት በርካታ ትምህርት ቤቶች መጎዳታቸውን የቢሮው ዕቅድ ዝግጅትና ክትትል ዳይሬክተር ዘመነ አበጀ ተናግረዋል፡፡

ዳይሬክተሩ አክለውም በምሥራቅ ጎጃም ዞን ከ400 በላይ ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል ብለዋል።

በተጨማሪም በክልሉ ጉዳት የደረሰባቸውን ትምህርት ቤቶች ወደ አገልግሎት ለመመለስ 112 ቢሊየን ብር እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል፡፡

ቢሮው አስጠናሁት ባለው ጥናት መሠረት ይህ ገንዘብ ትምህርት ቤቶችን ከመገንባትና ከመጠገን በተጨማሪም ተጓዳኝ የትምህርት ሥራዎችን ለማከናወን የሚውል ነው ብሏል።

መረጃው አማራ ኮምኒኬሽን ቢሮ ነው።

@tikvahethmagazine

25k 0 15 7 81

📢የዱባይ ሪል እስቴት ኤክስፖ 📢

ሰላም ኢትዮጵያ 🇪🇹

ከፍ ያለ የኢንቨስትመንት ገቢ ከዱባይ ሪል ስቴትማግኘት ይሻሉ? በተለያዩ የዩናይትድ አረብ ኢሜሬትስ ግዛቶች ውስጥየቤት ባለቤት ለመሆን እና አስተማማኝ የገቢ ምንጭወይም የመኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት የሚሹ ከሆነ ዕድልከበርዎ ቆማ ታንኳኳለች፡፡

✓ ከአንድ መቶ ሺህ ዶላር  ጀምሮ በተለያዬ የአከፋፍል ዘዴ በመክፍል ቋሚ ሀብት ማፍራትይችላሉ፡፡

✓ ቅድመ ክፍያ ከ 10% ጀምሮ ይቻላል፡፡

✓ የቤት ባለቤት ሲሆኑ ከ 2 እስከ 10 ዓመት የሚቆይናየሚታደስ የመኖሪያ ፈቃድ ለራስዎ እና ለቤተሰብዎያገኛሉ፡፡

✓ ከጥር 21 እስከ 25/2017 ዓ.ም. ባሉት ቀናት የቤትባለቤት የሚሆኑበትን፣ ሀብት የሚያፈሩበትን፣ በሂደትም አዋጪ የሆነ ትርፍ የሚያገኙበትንመንገድ በአካል ተገኝትን እናማክርዎታለን፡፡

✓ ይኼን መልካም አጋጣሚ ለመጠቀም @ / በስልክ ቁጥር+ 971 529180516 በመደወል ይመዝገቡ፡፡ ያነጋግሩን ! ዕድል ከደጃፍዎ ቆማለች ! አሁኑኑ ይጠቀሙባት!!!


" እናታችንን አፋልጉን ! "

" እናታችን ወይዘሮ አቦዘነች ማሞ  ይባላሉ ። የአዕምሮ ህመም ተጠቂ ሲሆኑ ፣ ጥር 13  2017  ከቀኑ 6.30 አካባቢ የካቲት 12 ሆስፒታል ለህክምና በሄዱበት ወቅት በድንገት ጠፍተዋል።

በሰአቱ ፣ ዥንጉርጉር  ቀሚስ ፣ ከላይ ቀይ ጃኬት ፣ አነስ ያለ  ጋቢ እና ከታች ስሊፐር ጫማ ተጫምተው ነበር።

መልካቸው ፣ ቀይ ፣ ቁመታቸው አጠር ያሉ ፣ እድሜያቸው 50 አካባቢ ናቸው

እናታችንን ያየ በ0985236156 / 0919146913 / 0949771786 ደውሎ ቢያሳውቀን ወሮታ ከፋይ ነን " - ፈላጊ ልጆቻቸው

@tikvahethmagazine

33.7k 0 20 11 165

#Konso 📶

በኮንሶ ዞን ከትናንት ጀምሮ የነበረው  የኔትወርክና የኢንተርኔት መቆራረጥ መንስኤ የ4G ኔትዎርክ ማሻሻያ እየተደረገ ከመሆኑ ጋር የተያያዘ ነው ተብሏል።

የኢትዮ ቴሌኮም ኮንሶ ሾፕ ሱፐርቫይዘር አቶ ጌቱ ጎዳ የማስፋፊያ ፕሮጀክቱ ለአንድ ወር ያህል ጊዜ የሚቆይ መሆኑን ገልጸዋል።

በቀጣይም ለተወሰኑ ጊዜያት የኔትወርክና የኢንተርኔት መቆራረጥ ለአጫጭር ደቂቃዎች ሊያጋጥም እንደሚችልና ህብረተሰቡ በትዕግስት እንዲጠባበቅ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

መረጃው የዞኑ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ነው።

@tikvahethmagazine


በዳውሮ ዞን ማሪ ማንሳ ወረዳ ቦንብ ፈንድቶ በ8 ሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ።

በዳውሮ ዞን ማሪ ማንሳ ወረዳ አሳሊ ቀበሌ ልዩ ስፍራው ዱቤ 02 ንዑስ ተብሎ በሚጠራበት መንደር ቦንብ ፈንድቶ በ8 ሰዎች ላይ ጉዳት ማድረሱን የደቡብ ምዕራፍ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፓሊስ አስታውቋል።

ኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነትና ኮምኒኬሽን ዳሬክቶሬት ዳሬክተር ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለጹት የቦንብ ፍንዳታው የተፈጠረው ጥር 13 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ላይ ነው።

በዚህም ፍንዳታ በስድስት ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት እና በሁለት ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት የደረሰ ሲሆን ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች በተርጫ ጠቅላላ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ነግረውናል።

ፖሊስ ባደረገው ማጣራት የአደጋው መነሻ ምክንያቱ የአንድ ግለሰብ አሮጌ መኖሪያ ቤት አፍርሶ በአዲስ ለመስራት በአከባቢው አጠራር ዳጉዋ (በደቦ) ሥራ ላይ የነበሩ ስምንት ሰዎች በቁፋሮ ወቅት ያገኙትን F1 የተባለ የእጅ ቦንብ ባለማወቅ በድንጋይና በመዶሻ በመቀጥቀጣቸው ፍንዳታው መከሰቱን አስረድተዋል፡፡

ፖሊስ የእጅ ቦንቡ በግለሰቡ መኖሪያ ቤት ተቀብሮ ሊገኝ እንደቻለ ግለሰቡን በቁጥጥር ስር አውሎ ቦንቡ ከየት እንደመጣ፣ እንዴት ግለሰቡ ቤትስ ሊገኝ እንደቻለ ተጨማሪ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝና የምርመራ ውጤቱ እንደተጠናቀቀ ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግ ኢንስፔክተር ደጀኔ ነግረውናል።

ህብረተሰቡ መሰል የፍንዳታ አደጋዎች እንዳይደርስ ምንነቱ የማይታወቅ ነገሮችን ሲያገኝ ከመቀጥቀጥ በመቆጠብ ለሚመለከተው አካል እንዲያሳውቅ እና ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ሲሉም አሳስበዋል።

@tikvahethmagazine


የስፔን ጠቅላይ ሚኒስትር ከአውሮፓ ውጭ የሚመጡ ዜጎች ቤት እንዳይገዙ ሊከለክሉ ነው፡፡ 

ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ ስፔን የገጠማትን የመኖሪያ ቤት እጥረት ለመቅረፍ ከአውሮፓ ውጭ የሚመጡ ዜጎች በሀገሪቱ  በቶችን እንዳይገዙ በከፊልና ሙሉ በሙሉ የሚያግደውን እቅድ ይፋ አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ''ስፔን ውስጥ ቤተሰብ ኖራቸውም አልኖራቸውም ከአውሮፓ ውጭ የመጡ ዜጎች በኛ ሀገር ቤት መግዛት አይችሉም'' ሲሉ ተናግረዋል፡፡ 

ይህንን እና በውጪ ዜጎች የንብረት ይዞታ ታክስ ላይ ያለውን ታክስ በ100 % ለማሳደግ ጭምር እቅድ ያስቀመጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እቅዳቸው ገና ወደ ህግ አውጪው ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት ይጠበቃል።

ባለፈው ዓመት በስፔን ነዋሪዎች መኖሪያ ቤቶችን ለማግኘት በመቸገራቸው ምክንያት የተቃውሞ ሰልፎችን ስፔን ተመልክታለች።

ማድሪድን ጨምሮ በታዋቂ ከተሞች የኪራይ ዋጋ መናር የአካባቢው ነዋሪዎች ከስፔን ገበያ ውጪ እየተደረጉ እንደሆነ እንዲሰማቸው አድርጓል።

በስፔን ውስጥ ከሚሸጡት አምስት ቤቶች ውስጥ አንዱ በውጭ ዜጎች የሚገዛ ሲሆን ብዙዎቹም ነዋሪ ያልሆኑ ናቸው።

ከአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ውጭ የሆኑ ዜጎች በ2023 ብቻ 23,000 ቤቶችን መግዛታቸው ተሰምቷል፡፡

Credit : Reuters, Independent

@tikvahethmagazine


⌛️95% የተጠናቀቁ አፖርታማዎች

📍በቦሌ ቡልቡላ ከሁዳ ኢንጅነሪንግ!

👉በካሬ 96,600ብር ጀምሮ
👉የተናጥል ዲጅታል ካርታ ያላቸው
👉137 ካ.ሜ ባለ ሶስት መኝታ
👉በወለል 2 ቤቶች ብቻ
👉50% ቅድመ ክፍያ ቀሪውን በ6 ወር ከፍለው የሚጨርሱት
👉 የከርሰምድር ውሀ፣ስታንድባይ ጄኔሬተር፣የጋራ ሰገነት እና በቂ የመኪና ማቆሚያ ያላቸው

ለበለጠ መረጃ :- 0931333432 ወይም 0909340800


🖼️ ፍቅረ ህትመት እና ማስታወቂያ ሥራ 🖼️

የህትመት እና ማስታወቂያ ፍላጎትዎትዎን ሃሳብዎን ከነገሩን ንድፈ-ሃሳቡን ከማውጣት ጀምሮ አይነ-ግቡዕ የሆነ ሥራ ሰርተን በራሳችን ማሽኖች አትመን ያሉበት ቦታ ድረስ መጥተን እናስረክብዎታለን።

ይደውሉ እና ይዘዙን ወረቀት ነክ ህትመቶች አልባሳት ላይ ህትመቶች እንዲሁም የተለያዩ ቁሶች ላይ እናትማለን። ከማስታወቂያ እና ህትመት ሥራ ጋር የተያያዘ ማማከርም እንሰጣለን።

ለነጋዴዎች እና አምራች ድርጅቶች ልዩ ቅናሽ አለን። ኑ አብረን እንስራ! ኑ አብረን እንደግ!

በዚሁ አጋጣሚ በፊት ተራራ የነበረው ስማችን ወደ ፍቅረ ህትመት ሥራ መቀየሩን ልንነግርዎ እንወዳለን።

☎️ ይደውሉ 0927361854 , 0799100230 , 0985257938

📱 TikTok 📱 Telegram 📱Facebook

📍 https://maps.app.goo.gl/heRTnskHQDUj2jgQ9


"የ20 ኢትዮጵያውያን ህይወት አልፏል" - IOM

መነሻውን ከጅቡቲ በማድረግ 35 ኢትዮጵያውያንን አሳፍሮ ወደ የመን ሲያቀና የነበረ የስደተኞች መርከብ በኃልኛ ንፋስ ተመቶ በደረሰው አደጋ የ20 ኢትዮጵያውያን ህይወት ማለፉን ዓለማቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) አስታውቋል

አደጋው ቅዳሜ ዕለት (ጥር 10) መድረሱን፤ የ9 ሴቶች እና የ11 ወንዶች ህይወት ማለፉን የጠቀሰው ድርጅቱ በመርከቡ የነበሩ 15 ኢትዮጵያውያን እና ሁለት የየመን ዜግነት ያላቸው መርከበኞች ደግሞ በህይወት መትረፋቸውን ገልጿል።

@tikvahethmagazine

35.6k 0 19 17 187

"ወቅቱ በጋና ነፋሻማ በመሆኑ ከድንገተኛ የእሳት አደጋ ተጠበቁ" - የሀላባ ዞን ፖሊስ መምሪያ

በስልጤ ዞን በሁልበራግ ወረዳ በቢላዋንጀ ቀበሌ በግምት ከቀኑ 6:30 አካባቢ በተከሰተው ድንገተኛ እሳት ቃጠሎ አራት የሳር ክዳን ቤቶች ከነ ንብረታቸው ሙሉ በሙሉ መውደማቸውንና በአንድ የሰር ክዳን ቤት ላይ መጠነኛ አደጋ መድረሱን ፖሊስ አስታውቋል።

የእሳት አደጋው ወደከፋ ደረጀ ሳይደርስ ከሀለባ ዞን የእሳትና ድንጋተኛ አደጋ መቆጣጠሪያ መኪና ደረሶ በተደረገው ርብርብ እሳቱን መቆጣጠር መቻሉ ነው የተገለጸው።

⚠️ ወቅቱ በጋና ነፋሻማ በመሆኑ ሁሉም ማኅበረሰብ አከባቢውን፣ ንብረቱን፣ እራሱን ከድንገተኛ እሳት አደጋ እንዲጠብቅ የሀላባ ዞን ፖሊስ መምሪያ መልዕክቱን አስተላልፏል።

@tikvahethmagazine


ሁሉንም በአንድ የያዘ ስማርት ካርድ ወደ ሥራ ለማስገባት እየተሰራ ነው ተብሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የፋይዳ መታወቂያ ቁጥር የያዘ፣ የመንጃ ፍቃድ ቁጥር ያለው እንዲሁም እንደ ኤቲ ኤም ካርድ የሚያገለግል ሁሉንም በአንድ የያዘ የነዋሪነት መታወቂያ ስማርት ካርድ ወደ ሥራ ለማስገባት በፕሮጀክት ደረጃ እየሰራ መሆኑን ጠቅሷል።

የአዲስ አበባ ከተማ የነዋሪነት መታወቂያን ስማርት አርጎ አሁን ከምንጠቀምበት የተሻለ ተደርጎ ሰዎች የተለያዩ ካርድ ይዘው ከሚንቀሳቀሱ ሁሉንም አገልግሎቶችን በአንድ የያዘ ካርድ በቀጣዮቹ 6 ወራት ውስጥ ወደ አገልግሎት ለማስገባት በእቅድ ይዞ እየሰራ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከኤጀንሲው ሰምቷል።

ካርዱ የሚሰራበት ዋነኛ አላማም አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያሉ ችግሮችን በመቅረፍ፣ ነዋሪዎች 3 ወይም 4 ካርድ ይዘው ከሚንቀሳቀሱ በ1 ካርድ ሁሉንም አገልግሎቶች አግኝተው አገልግሎት አሰጣጥና ተጠቃሚነትን ቀላል ለማረግ መሆኑን አሳውቋል።

ኤጀንሲው ለቲክቫህ እንደገለፀው ይህ ጉዳይ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር ትስስር ሊኖር እንደሚገባና በአሁኑ ሰዓትም ፋይዳ ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

ለወደፊት ደሞ ስራው ተጠናቆ ካርዱ ወደስራ ሲገባ ባንኮች እና ሌሎች የሚመለከታቸው ተቋማት የጋራ ትብብር እንደሚፈጠርም ተገልጿል።

ይህ አገልገሎት በሚቀጥሉት 6 ወራት ውስጥ ወደ ስራ ለማስገባት እቅድ የተያዘለት ፕሮጀክቱ አሁን ላይ ማሳያዎች (Samples) እየተሰራ ይገኛል።

አዲስ የሚሻሻለው የመታወቂያ አገልግሎት ፕሮጀክት ተግባር ላይ መዋል ሲጀምር ወይም የሚሻሻሉ፣ የሚጨመሩ ጉዳዮች ሲኖሩ ኤጀንሲው ለህዝብ በይፍ እንደሚያሳውቅም ነው ያስታወቀው።

@tikvahethmagazine


#AddisAbaba

" አባታችንን አፋልጉን ! "

አባታችን ገብረማርያም መለሰ ጥር 9 ቀን 2017 ዓ/ም ከሰዓት በኃላ ከቤት እንደወጡ አልተመለሱም።

እድሜያቸው 85 ዓመት ሲሆን መጥፋታቸውን ለፖሊስ አመልክተናል።

በሰዓቱ ለብሰውት የነበረው ጥቁር ጃኬት ነበር። ከዘራም በእጃቸው ይዘዋል።

መጨረሻ ጊዜ የነበሩበት ቦታ ወሰን 02 አካባቢ ነው።

ቤተሰብ ተጨንቋል አባታችንን አፋልጉን፤ መረጃ ለመስጠት 0911452386 ላይ ደውሉልን። " - ፈላጊ ቤተሰቦቻቸው

@tikvahethiopia

Показано 18 последних публикаций.