Veronica Melaku


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Блоги


ይህ የቴሌግራም ቻናል ነሐሴ 18/2013 ተከፈተ!

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Блоги
Статистика
Фильтр публикаций


በሁለቱም ጎራ በኩል በተደጋጋሚ እንደምንሰማው አንድነቱን እውን ለማድረግ ብዙ እርቀት ተጉዘናል ይላሉ! ታዲያ ሁሉም ለአንድነት ያለሰለሰ ጥረት ካደረጉ ለምን አልተሳካም? እስቲ እናንተ የተረዳችሁትን በጨዋ ደንብ አጋሩን!!


ፕሮፖጋንዳ ፍሬ የሚያፈረው ተመጥኖ ሲለቀቅ ነው፤ አየሩን ለማይዝ ተብሎ የሚለቀቅ ፍሮፎጋንዳ (የኢራቅ ፋኖ ተመሰረተ አይነት) ከጥቅም ጉዳቱ ያመዝናል!!


ጥያቄው!
1) የአዲስ አበባ ህዝብ የሰራውን ስህተት የአማራ ክልል ህዝብ ይደግመዋል ወይ?
2) ታጋይ እስክንድር ለድርድር ቀረበ ብለን እናስብና፤ መደራደር የጦርነት ማብቂ ነው፤ ድርድር ተደርጎ ጦርነት ይቆማል፤ ድርድር (ዋናው ነጥቦቹ እንጂ) አይደረግ ነው የምትሉት?
3) የታጋይ እስክንድር ሀይል በራሱ መንገድ ይሒድ። ቀሪው ሀይል በራሱ መንገድ ይሂድ። የበለጠ ለአማራ ጠቃሚ ሁኖ የተገኘውን ህዝቡ ይደግፍ። ከዚያ ውጭ የብልፅግና አክቲቪስት የሚተፋልህ አትላስ እንደበቀቀን አታስተጋባ!! አይ ካልክ መብትክ ነው!!

መንጋነት ይውደም
አሰላሳይነት ይቅደም

4.8k 0 2 46 125

አሁንም ደግሜ ደጋግሞ እላለሁ ከፕሮፖጋንዳ በተለይም ከሀሰተኛ ራሳችን እንጠብቅ! በሀሰት የትም አይደረስም!!

አባታችን ፕ/ር አስራትም እንዲሁ በመንጋ በሀሰት ተዘምቶባቸው ነው ሀሳባቸው ሳይሳካ የቀረው!! የአሁኑ አማራ(አብዛኛው) ከዚያ ትምህርት ያልወሰደ፣ በሒደት የማይበስል፣ ማንም የሚጋልበው፣ በመንጋ የሚነጉድ እጅግ አደገኛ የፖለቲካ ደን*ር ነው።

ሰላም ዋሉ፤
ደህና እደሩ
ሰላም አምሹ


"ኸየ አማራ ዶንቆሮው" ይላል ሞጣ 😄
በምን ልብ ብሎ አየልኝ


የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ሰለባ የሚሆን አማራ እራሱ ላይ የመከራ ጊዜ ይጨምራል፤ በElias Mesert ታጋይ እስክንድር ነጋ ላይ የተሰራውን የሀሰት መረጃ እቃወማለሁ!! ለአማራ እንደ አማራ የተለየ የትግል መስመር ያለው ቡድን ቢኖር እንኳን እደግ ይባላል እንጂ አልይህ አይባልም!! እውነት እያደር ይጠራል!!

ለግራ ዘመሞቹ ጥያቄ!
ዘመነ ከብልፅግና ለመደራደር የድርድር ቦታው አሜሪካ ይሁን ማለቱ የመሰረት ሚዲያ ምንጮች አደረሱ። የሚል ዜና ብታነቡ ምላሻችሁ.. ዘመነ ባንዳ ነው፤ ጠላት ነው ትላላችሁ?

መሪህን አሳልፈህ አትስጥ
ወጣት ከታሪክ ተማር

5k 0 1 42 84

እስቲ ወደዚህ ጎራ ብላችሁ አወንታዊ አስተዋፆ አድርጉለት ።
1 ወር የወሰደ ስራው ነው! እኛ ከ1 እስከ 2 ደቂቃ በመውሰድ እናበረታታው! 👇
like እና የማበረታች comment እንፃፍለት።
https://youtu.be/JHgWm8r2kUU


ትግል ያለ ሐሳብ፤ ሐሳብም ያለ ትግል ከንቱ ነው!
አንብብ! ጸንተህ ታገል!!!
👆👆👆

10k 0 6 17 81

አንዳንድ ሰዎች ዝም ቢሉልን የምር እንደታገሉ እንቆጥርላቸው ነበር!

9.2k 0 3 20 133

ትኩረት፤ መርህ!

የትግላችን አላማ እንደ ህዝብ የታወጀብንን የህልውና አደጋ መቀልበስ እና የህዝባችንን ነጻነት በዘላቂነት ማረጋገጥ አይደለምን? ከዚህ ውጪ የተለየ አላማ እንደሌለን ግልፅ ነው፡፡ ይህን ክቡር አላማ ማሳካት የምንችለው በመደራጀት እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡ ጠንካራ የፖለቲካ፣ የሲቪክ፣ የሚዲያ ወዘተ ድርጅቶችን መፍጠር የምንችለው ደግሞ የሚያሰባስበን የጠራ ርእዮት ሲኖረን ነው፡፡ ከአማራ ብሄርተኝነት ውጪ ሊያሰባስብን፣ ሊያደራጀን እና ለነፃነት ሊያበቃን የሚችል አንዳችም ርእዮት እንደሌለ ደግሞ ለሚገባው ሁሉ ፍንትው ብሎ የሚታይ እውነታ ነው፡፡

ያለን ግዙፍ ሀብት የአማራ ብሄርተኝነት ነው፡፡ አንዳንዶች ስለ ብሄርተኝነት ሳያነቡና ሳይገባቸው አማራ አማራ ሲሉ ከቆዩ በኋላ፣ ተመልሰው ያልገባቸውን ብሄርተኝነት ሲረግሙት ይታያሉ፡፡ መጀመሪያም አልገባቸውም ዛሬም አልገባቸውም፡፡ እነሱን መተው ነው፡፡ አጀንዳ አለማድረግ፡፡ አንዳንዶች ደግሞ በእውቀትና በአላማ ብሄርተኝነታችን እንድንተው እየሰሩ ነው፡፡ እነዚህ አማራን ያለ ትጥቅና ድርጅት ለማስቀረት የሚሰሩ የአማራ ጠላቶች ናቸው፡፡ እነዚህን አምርሮ መታገል ያስፈልጋል፡፡ እነዚህን ማሸነፍ የሚቻለው ደግሞ ብሄርተኝነቱን በማጠናከር ነው፡፡

የአማራ ብሄርተኞች ሁልጊዜም ትኩረታችን በህዝባችን ላይ መሆን ይገባዋል፡፡ ሁልጊዜም ብሄርተኝነቱ እንዲጠናከር መስራት፣ አረም እንዳያጠቃው መኮትኮት፣ አካታችና አሳታፊ እየሆነ እንዲያድግ ማጠናከር ይገባናል፡፡ የአማራ ትልቁ ሀብቱ ብሄርተኝነቱ መሆኑን አውቀን ሁልጊዜም እሱን በማጠናከር ላይ ማከተኮር ይኖርብናል፡፡
ህዝባችን አሁን ለሚገኝበት ደረጃ የበቃው በአንድ አገዛዝ ዘመን አይደለም፡፡ አሁን ለምንገኝበት ደረጃ ያበቃን ተከታታይ አገዛዞች ያደረሱብን በደል ውጤት ነው፡፡ ስለሆነም ትግሉ ጊዜ የሚጠይቅ መሆኑን፣ መስዋእትነት የሚያስከፍል መሆኑን፣ ብዙ ውጣ-ውረድ ያለው መሆኑን፤ ግን ደግሞ ብሄርተኝነታችን አጠንክረን ከያዝን በአሸናፊነት የምንወጣው መሆኑን መገንዘብ ወሳኝ ነው፡፡ ሥር የያዘ ትግል፣ በእውቀት የሚመራ ትግል፣ ከመንቦጅቦጅና ወረተኛነት ያለፈ ትግል፣ በርእዮትና በድርጅት የሚመራ ትግል ማካሄድ ወሳኝ ነው!

በነፋስ አመጣሽ አጀንዳ ከመጠለፍ ራስን መጠበቅ፤ ሁልጊዜም ውስጣዊ አንድነትነት በሚያጠናከር ተግባር ላይ ማተኮር አስፈላጊ ነው፡፡ በየዘመናቱ መሳሳት ከማይሰለቸውና የሃሳብ ድርቅ ከመታው ጎራ ጋር አብረን እንራኮት፡፡ ብዙ ስራ አለብን!

ጊዜው የስራ ነው!!!


ጎንደር 💪


ብር-ሸለቆ ዝም ማለት አይቻልም!
ፋኖ 💪


Asres Mare Damtie

በሞት አፋፍ ላይ ያለ ስርዓት የሚፈፅመውን አረመኔያዊ ድርጊት ህዝባችን አምርሮ ሊታገለው ይገባል።

የዐቢይ አሕመድ የጥፋት አገዛዝ በሁሉም ኢትዮጵያዊ ላይ ሲያሻው በተመሳሳይ ሰዓት ሲፈልግ ደግሞ በፈረቃ ጅምላ ግድያና እልቂትን እየፈፀመ ቀጥሏል፡፡ አገዛዙ የከፈተውን ጦርነት ማሸነፍና መቋቋም ሲያቅተው አንዱ ሌላውን የገደለ ለማስመሰል ሲቀሰቅስ፣ ንፁሃንን ሲገድልና በእሳት ጭምር ከነነፍሳቸው ሲያቃጥል አሳይቶናል፡፡

የአማራን ሕዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር ደም ለማቃባትና በጥርጣሬ እንዲተያይ ለማድረግ የሚፈጽማቸው ግፎች በቀጠሉበት በዚህ ወቅት በኦሮምያ ክልል ሰሜን ሸዋ አካባቢ አሰቃቂ ግድያዎች ተፈጽመዋል፡፡ ይህንን ድርጊትም ፈፅሞ እናወግዛለን። ይሄን ማውገዝ እንኳን እንደኛ ካለ በደል እና መገደል አንገሽግሾት ለነፃነት ከወጣ ታጋይ ብቻ ሳይሆን
ከማንኛውም ሰብዓዊ ፍጡር የሚጠበቅ ነው።

መሰል ግድያዎችን በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎችም ሆነ በአማራ ክልል ሲፈጽም የሚታወቀውም ሆነ አሰቃቂ ጅምላ ጭፈጨፋዎችን ሲያካሂድ በዓለም ጭምር ሲወገዝ የነበረው የብልጽግናው አገዛዝ ወንድም ከሆነው የኦሮሞ ሕዝብ ጋር ሕዝባችንን ለመነጠል በማሰብ ይህንን ነውረኛ ተግባር መፈፀሙን መጠራጠር አያስፈልግም፡፡

በመሆኑም:-
1/ አለም አቀፍ ገለልተኛ አጣሪ ቡድን ይህንን ነውረኛ ተግባርና አሰቃቂ ወንጀል እንዲመረምረው እንጠይቃለን፡፡
የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶችም አስፈላጊውን ሁሉ እንድታደርጉ ጥሪ እናስተላልፋለን፤

2/ ሌሎች ኢትዮጵያዊያንም የአገዛዙን ሴራ ተረድተዉ መሰል ድርጊቶችን እንዲያወግዙ እና በመሰል ሴረኛ መንገድ ሕዝቦችን ለማጫረስ የቆረጠውን አገዛዝ እንዲታገሉት ጥሪ እናቀርባለን፡፡

3/ እንዲህ ያሉ አሰቃቂ ግድያዎች የሚያቆሙበት፣ ኢትዮጵያዊያን በተለመደው ወንድማማችነታቸው የሚኖሩበት አገር ለመፍጠር የምንታገለው እኛ የፋኖ ኃይሎች ይህንን ድርጊት የምናወግዘውና በምንቆጣጠራቸው ግዛቶችም ሆነ በምንሰጣቸው ስምሪቶች መሰል ጥፋት እንዳይፈፀም አበክረን የምንጠነቀቅ መሆናችንን እንገልፃለን፡፡

4/ በመጨረሻም በጭካኔና ነውረኛ መንገድ አሰቃቂ ግድያ የተፈፀመበት የኦሮሞ ወንድማችን እና ሌሎች በጥይት ተደብድበው ለሞቱት የኦሮሞ ወንድሞቻችን ቤተሰቦች ከልብ መጽናናትን እንመኛለን፡፡

አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!


አገዛዙ የመጨረሻ ካርዶቹን መምዘዝ ጀምሯል፤ ይህም የፋኖ ትግል climax state ላይ እንደደረሰ ማሳያ ነው!!
ግብር በሚከፍሉት መንግስት ለተጨፈጨፉ ወንድም ህዝቦች ነፍሳቸውን አምላክ በገነት ያሳርፍ!!!


እጅግ አድካሚ የነበረው ስራችን ወደ መጠናቀቁ ነው፤ በቅርቡ ለአማራ ብሔርተኞች ብቻ ታላቅ የምስራች ይኖረናል!!

ግን ከሚያላጋ ፕሮፖጋንዳ ራሳችሁን ለመጠበቅ ተዘጋጁ!!


እምቢ በል!

የአማራ ህዝብ ጥቃት የሚያንገበግብህ ከሆነ፣ የአማራ ህዝብ የሕልውና አደጋ እንዲቀለበስና ህዝባችን ነፃነቱን አረጋግጦ በሰላም እንዲኖር ቁርጠኛ እምነት ያለህ ከሆነ “እምቢ!” ማለት ያለበህ ጉዳዮች አሉ፡፡

1/ ቅርጫት ውስጥ እንድትገባ የሚፈልጉ ብዙ አካላት ስላሉ እምቢ በል፡፡ አንዱን ታጋይ ደግፈህ ሌላውን እንድትቃወም፣ አንዱን ቡድን ደግፈህ ሌላውን እንድትቃወም፣ የአንዱ ጎራ አባል እንድትሆን የሚፈልጉ አሉ፡፡ በዚህና በዚያ ሆነው ይወጉሃል፡፡ ያዋክቡሃል፡፡ እንዲህ ነህ፣ እንዲያ ነህ ይሉሃል፡፡ የእከሌ ደጋፊ ነህ፣ የእከሌ ተቃዋሚ ነህ ይሉሃል፡፡ ከአንተ የሚጠበቀው እምቢ ማለት ነው፡፡ ቅርጫት ውስጥ አለመግባት ነው፡፡ ሁልጊዜም ወገናዊነትክን ከአማራ ህዝብ ጋር ብቻ ማድረግ ነው፡፡ አማራ ክልል የሚገኘው ብቻ ሳይሆን በመላው ኢትዮጵያ የተሰራጨውና በውጭም የሚኖረው አማራ ሁሉ ወገንህ ነውና በእኩል መንፈስ እየው፡፡ ቀጭኗን መንገድ መራመድ ይገባሃል፡፡ በሂደት መንገዷ ትሰፋለች፡፡ ትግል ያሳፋታል፡፡ ብዙ ልባሞች መምጣታቸው አይቀርምና፡፡

2/ ብሄርተኝነትን ከዘረኝነት ጋር እያያዙ የሚያጣጥሉ ሰዎች ይገጥሙሃል፡፡ ብሄርተኝነትን ካለመዘመን ጋር እያያዙ የሚተነትኑ ያልገባቸው ሰዎች ይገጥሙሃል፡፡ “አማራ ብሄርተኛ ሊሆን አይችልም፣ የአካባቢ ማንነቶች ጠንካራ ናቸው፣ የአማራ ብሄርተኝነት አይነሳም” ወዘተ ወዘተ ይሉሃል፡፡ እንዲህ የሚሉህ ስለ ብሄርተኝነት አንድም መጽሃፍ አንብበው የማያውቁ ናቸው፡፡ አንተ ግን ብሄርተኝነት የከተማ/ዘመናዊት ክስተት መሆኑን እወቅ፡፡ በጎሳ ያልተደራጀ በመሆኑ እንደ አማራ ለብሄርተኝነት የተመቸ ህዝብ እንደሌለ ይግባህ፡፡ ዛሬ የሰልጣኔ ጣሪያ ላይ የደረሱት ከእንግሊዝ እስከ ጃፓን፣ ከአሜሪካ እስከ ጀርመን ሁሉም ብሄርተኞች መሆናቸውን እወቅ፡፡ ስለሆነም የአማራ አባቶች ስህተት ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ማለታቸው እንዳልሆነ፣ ስህተታቸው ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ የሚሉት አማራነታቸውን ጥለው እንደሆነና ስህተቱም እሱን እንደሆነ ይግባህ፡፡ ብሄርተኝነት መቼም የማይሸነፍ መሆኑንም በደንብ ማወቅ ይገባሃል፡፡ በአንደኛው ትውልድ ድክመት ድሉ ሊዘገይ ይችል ይሆናል እንጅ ብሄርተኝነት አይሸነፍም፡፡ ደካማው ትውልድ ለልጆቹ የቤት ስራ ሲያስቀምጥ ልባሙ ትውልድ ግን ነፃነትን ያወርሳቸዋል፡፡

3/ የአማራ ብሄርተኝነት ዣንጥላ መዋቅር መሆኑን አጥብቀህ ያዝ፡፡ ሌሎች የፖለቲካ፣ ወታደራዊ፣ የሲቪክ፣ የሚዲያ ወዘተ ድርጅቶች በብሄርተኝነቱ ስር ያሉ እንጅ ብሄርተኝነቱን የሚተኩ አለመሆናቸውን ጠንቅቀህ እወቅ፡፡ አንድ የአማራ ድርጅት ሊዳከም ይችላል፡፡ ሊፈርስም ይችላል፡፡ ያ ድርጅት ተዳከመ ወይም ፈረሰ ማለት ግን የአማራ ብሄርተኝነት አለቀለት ማለት እንዳልሆነ ይግባህ፡፡

4/ የአማራ ብሄርተኝነትን ከሃይማኖት ጋር አታቀላቅል፡፡ ሁሉም የየራሱ ቦታ አለው፡፡ የራስክን ሃይማኖት ያዝ፡፡ ነገር ግን መታገል ያለብህ ለሁሉም ሃይማኖቶች እኩልነት መሆን ይገባዋል፡፡

5/ በተሸነፈ ማህበረሰብ ውስጥ አሸናፊ ግለሰብ ሊኖር እንደማይችል ተረዳ፡፡ ችግር ውስጥ ካለ ማህበረሰብ ወጥተህ ተመችቶህና የሕሊና እረፍት አግኝተህ ልትኖር እንደማትችል ይግባህ። ስለሆነም ሁልጊዜም የህዝብህ ጉዳይ እንቅልፍ ይንሳህ፡፡ በሚገነባ እንጅ በአፍራሽ ተግባር ላይ አትገኝ፡፡ የተግባር ሰው ሁን! የስራ ሰው ሁኚ!!!

የአማራ ብሄርተኝነት ይለምልም!!!

25.4k 0 17 25 147

ከአንድነት ሃይሉ ጋር መስራት ይቻላል?

ከአንድነት ሃይሉ ጋር መስራት ይቻላል? መልሱ "ይቻላል ብቻ ሳይሆን መቻልም አለበት" የሚል ነው፡፡ ወሳኙ ጥያቄ "በምን አግባብ?" የሚለው ነው፡፡ መልሱ “አማራነታችን ይዘን!” የሚል ነው፡፡ እንደከዚህ ቀደሙ ማንነታችን ጥለን ሊሆን አይችልም፡፡ አማራነትን በሁለተኛ ደረጃ አስቀምጠን ሊሆን አይችልም፡፡ ይህን ወሳኝ መርህ እስከያዝን ድረስ በሚያግባቡን ጉዳዮች ላይ ለኢትዮጵያ አንድነት ከሚታገሉ ወገኖች ጋር መስራት ይቻላል፡፡ ይገባልም፡፡ ከአንድነቱ ጎራ ጋር ብቻ ሳይሆን ከሌሎች ብሄረሰቦች ሃቀኛ ታጋዮች ጋርም መስራት ይቻላል፡፡ ይገባልም፡፡ አቋማችንን ይዘን፡፡ ጥቅማችን አሳልፈን ሳንሰጥ!

ጨፍጫፊው ቡድን ራሱን ለማጠናከር ከሀገር ውስጥም ሆነ ከውጭ አጋሮችን ይፈልጋል፡፡ ሃይል ለማሰባሰብ ይታትራል፡፡ እኛም ከጨፍጫፊው ቡድን በላይ መስራት ይጠበቅብናል፡፡

ከሌሎች ሃይሎች ጋር በሚያግባቡን የጋራ ጉዳዮች ላይ አብሮ ለመስራት ግን መጀመሪያ እኛው ራሳችን እንደ ብረት የጠነከረ አንድነትና ህብረት ሊኖረን ይገባል፡፡ ከሌሎች ጋር መስራት የሚገባን “በእነዚህ፣ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ነው” ብሎ ለመነጋገር መጀመሪያ የራስን ጎራ እውነትም “አንድ ጎራ” ማደረግ ያስፈልጋል፡፡ ሰንበሌጥ ሌሎችን ልደገፍ ይላል እንጅ የሚደገፈው የለም፡፡ ዋርካ መሆን ያስፈልጋል!

በትንሽ ፖለቲካ መርመጥመጡን ትተን ሁልጊዜም አማራን በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ እናተኩር፡፡ ሁልጊዜም ህብረታችን በሚያጠናክሩ ተግባራት ላይ እንሰማራ፡፡ ሌሎችን መግፋት መገፋትን ያስከትላል፡፡ መጠቃቃትን ያመጣል፡፡ የጋራ ውድቀትን ይጋብዛል፡፡ በሚገነባ ተግባር ላይ ብቻ እናተኩር!

ለድል እንታገል!

የአማራ ብሄርተኝነት ይለምልም!!!


ዳንኤል ብርሃኔ እና እኔ

ዳንኤል ብርሃኔ ወንበርተኛዬ (batch) ነው፡፡ ሃሳባችን ባይገጥምም ከመወያየትና ከመከራከር ተቆጥበን አናውቅም ነበር፡፡ መቼም አምባገነኖች የራሳቸውን ቅዠት ካመኑ አደገኛ እንደሚሆኑ የታወቀ ነው፡፡ ዳኒ የዚህ በሽታ ሰለባ ነበር፡፡ ወያኔ እስከ 100 አመት ሊገዛ ይችላል ብለው ከሚያምኑት ወገን ነበር፡፡ በረከት ስምኦን ከዚያ አነስ በማድረግ ቢያንስ 60 አመት ይል ነበር፡፡

ባህር ዳር ላይ ወጣቶች በኢህአዴግ አልሞ ተኳሾች የተገደሉ ሰሞን ነው፡፡ ዳኒ ሚካኤል በሚገኘው ታፍ ህንጻ እልል ያለ ስቱዲዮ ግንብቶ “ሆርን አፌዬርስ” የተሰኘ ሚዲያ ጀምሮ አለሁ አለሁ ማለት ጀምሮ ነበር፡፡ የጫት ቅንጣቢውን በኪሱ ይዞ ቡናውን ማግ እያደረገ ያወራኛል፡፡ “ምን ይታይሃል? እስኪ አስተያየትክን እንስማው” ይለኛል፡፡ “ስርአቱ አልቆለታል፡፡ በተለይ አማራ አምርሯል፡፡ ሃቁ ባይዋጥላችሁም ከዚህ በኋላ ኢህአዴግ ተመልሶ አማራን በሃይል ማስገበር የሚችል አይመስለኝም” ወዘተ ወዘተ እለዋለሁ፡፡ ከት ከት ብሎ ይስቃል፡፡ የተለመደ ነው፡፡ አማራው ተመቷል፣ አይነሳም ብለው ነው የሚያምኑት፡፡ “ህወሃትን አታውቀውም፡፡ ለነገሩ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚክስ ትምህርት እኮ በፖለቲካና በህግ ዙሪያ አትድረስ የተባለ ነው የሚመስለው” እያለ የፖለቲካ ትንታኔ አቅሜን ያጣጥላል፡፡ ይቀጥልና “ክፉዎች ናቸው፡፡ ተቀጣቅጠው አፈር ቅመው ይነሳሉ እንጅ ይወድቃሉ ብለህ እንዳታስብ፡፡ ደግሞ አደራህን እየወደቁ ነው ብለህ ከማይሆኑ ሰዎች ጋር እንዳትነካካ” ይለኛል፡፡ ምክርም ማስፈራሪያም ነው፡፡ እኔም በሃሳቤ አጠንክሬ አልገፋበትም፡፡

መጨረሻ ላይ የሆነውን ሁላችንም ስለምናውቀው አንሄድበትም፡፡ ወዳጄ ዳኒም ያን የመሰለ በአቶ ተክለብርሃን አምባዬ ህንጻ ላይ የተሰራ የተንጣለለ ስቱዲዮ ሳይጠቀምበት መቀሌ ከተመ፡፡ የቀረው ታሪክ ነው፡፡

አምባገነኖች ህዝብን ዋጋ የሚያስከፍሉት የራሳቸውን ቅዠት ስለሚያምኑ ነው፡፡ ጋዳፊ “አረንጓዴው መጽሃፍ” የሚባል መጽሃፍ ነበረው፡፡ ነገርዬው ከማኦ “ቀዩ መጽሃፍ” መኮረጁ ነው፡፡ ታዲያ ጋዳፊ የፈጠረውን ቅዠት በማመን ራሱን ማሻሻል ባለመቻሉ መጨረሻ ላይ የገጠመውን የምናውቀው ነው፡፡ መንግስቱ ሃይለማርያምም “ተው የአለም ሁኔታ ተቀይሯል፣ ሶሻሊዝምም አደጋ ላይ ነው” እየተባለ በራሳቸው በነ ጎርቫቼቭ ጭምር ሲነገረው ጭራሽ እነሱን “ከላሽ! በራዥ!” እያለ የሶሻሊዝም ታማኝ ነኝ ብሎ ክችች አለ፡፡ መጨረሻ ላይ የገጠመውን እናውቀዋለን፡፡ የወያኔ አምባገነኖች ሁኔታም ተመሳሳይ ነው፡፡ አብዮታዊ ዲሞክራሲ የሚባለውን ንድፈ ሃሳብ እያነበነቡ ከእሱ ውጪ ፍቱን መድሃኒት የለም አሉ፡፡ ራሳቸውን መለውጥ ተሳናቸው፡፡ መጨረሻቸው አላማረም፡፡ ሀገርንም ጨምረው ዋጋ አስከፈሉ፡፡

የዛሬዎቹም የራሳቸውን ቅዠት አምነው እያዛጉን ይገኛሉ፡፡ ፍቱን መድሃኒቱ እኛ የጻፍነው ነው እያሉ ነው፡፡ ትልቁ አደጋ ይህን የፈጠሩትን ቅዠት እንደ ፍቱን መድሃኒት ማመናቸው ነው፡፡ ስለዚህም እነሱ የያዙትን ሃሳብ የሚቃወመው በሙሉ ጠላት ነው፡፡ መታሰር አለበት፡፡ መሳደድ አለበት፡፡ መጥፋት አለበት፡፡ ዛሬም እንዲህ አይነት በራሳቸው ቅዠት የሰከሩ ገዥዎች አሉ፡፡ ዛሬም በገዥዎች ቅዠት የሰከሩ እና ልክ እንደ ዳንኤል በእውነት ላይ የሚሳለቁ ጭፋራዎች አሉ፡፡

ታዲያ መፍትሄው ምንድን ነው? መፍትሄው ትግል ብቻ ነው፡፡ ወያኔዎች ከነቡትቶ ሃሳባቸው እንደወደቁት፣ ሌሎችም አምባገነኖች እንደተንኮታኮቱት እነዚህም በትግል ይሸነፋሉ፡፡ በፅኑ ትግል የማይሸነፍ አምባገነን የለም!

ለድል እንታገል!

የአማራ ብሄርተኝነት ይለምልም!!!!


የሚያኮራ እና መጠናከር ያለበት ጅምር!

የአማራ ጋዜጠኞችና አክቲቪስቶች ትዊተር (X) ላይ የጀመሩት እንቅስቃሴ በጣም የሚያኮራና ይበልጥ ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ነው፡፡ ሁሉንም የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች በሚገባ አሟጠን በመጠቀም ለህዝባችን ድምጽ መሆን መቻል አለብን፡፡ በተለይ ትዊተር ላይ የሚካሄዱት ዘመቻዎች የጊዜ ሰሌዳ ወጥቶላቸው መልእክቶች በደንብ እየተቀረፁ ሳይቋረጡ መቀጠል ይገባቸዋል፡፡ ያለ ጥርጥር ተስፋ ሳንቆርጥ የምንሰራ ከሆነ ድምጻችን ሰሚ ያገኛል፡፡

ስለሆነም በተለይ ትዊተር ላይ የሚከሄዱት ዘመቻዎች በተቀናጀና በጥሩ ጥሩ ግራፊክሶችና መልእክቶች በታጀበ መልኩ እንዲቀጥሉ ዘመቻውን የጀመሩትን እህቶችና ወንድሞች ማበረታታት ይገባል፡፡
ውጤት እስክናመጣ እንታገል!

ያዝ ለቀቅ አያስፈልግም!
ፅናት!!!

የአማራ ብሄርተኝነት ይለምልም!!!


አማራ ከዲሞክራሲ የሚያጣው ምንም ነገር የለም!

የአማራ ህዝብ ከዲሞክራሲ የሚያገኘው እንጅ የሚያጣው አንዳች ነገር የለም፡፡ ግንባር ቀደም ቁጥር ያለው ህዝብ ዲሞክራሲን ሊፈራ አይችልም፡፡ አይፈራምም፡፡ ዲሞክራሲን መርሃችን ማድረግ ያለብን ግን ብዙ ቁጥር ስላለን አይደለም። ዲሞክራሲ ለሕልውና ትግሉ ቁልፍ ስለሆነ ነው።

ስለ ዲሞክራሲ ሲነሳ አንዳንድ ሰዎች “አሁን ስለ ዲሞክራሲ የምናወራበት ጊዜ አይደለም፣ መጀመሪያ ሕልውናችን እናረጋግጥ፣ ሕልውናችን ሳይረጋገጥ ስለ ዲሞክራሲ ማሰብ ቅንጦት ነው” ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ ትልቁ ስህተት ይህ ነው፡፡ ምናልባት እንዲህ አይነት አስተያየት የሚሰጡት ዲሞክራሲን ከልቅ ህግ አልባነት ጋር እያያዙት ይመስላል፡፡

ዲሞክራሲን ግን ያለ ህግ ማሰብ አይቻልም፡፡ ያለ ስርአት የሚታሰብ ዲሞክራሲ የለም፡፡ ዲሞክራሲ ለአማራ ሕልውናውን ካረጋገጠ በኋላ እውን የሚያደርገው ጉዳይ ሳይሆን ራሱን ሕልናውን እውን ለማድረግ የሚጠቅመው መሣሪያ ነው፡፡ የምናቋቋማቸው ተቋማት/ድርጅቶች ጠንካራና ውጤታማ ሊሆኑ የሚችሉት በዲሞክራሲያዊ አግባብ ሲቋቋሙና ሲመሩ ነው፡፡ ውሳኔዎች ከተቻለ በሙሉ ስምምነት፣ ካልሆነ በድምፅ ብልጫ መወሰን አለባቸው፡፡ የብዙሃኑ ውሳኔ ተግባራዊ ይሆናል፣ አነስተኛ ቁጥር ያገኙት (የአናሳው ወገን) መብት የከበራል፡፡ እንዲህ አይነቱ አሰራር በትጥቅ ትግል ውስጥ ላሉት ሃይሎችም ሆነ በሲቪል ተቋማት ዘንድ ወሳኝ ነው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የአማራ ተቋማት ዲሞክራሲዊ መሆን በሌሎች ብሄረሰቦችና በአለም አቀፉ ማህበረሰም ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነትን የሚያስገኝ ትልቅ ጸጋ ነው፡፡ እንዲህ ሲሆን ነው የአማራው ሃይል ገና ወደ ስልጣን ሳይመጣ የሞራልና የሃሳብ መሪነት (moral and intellectual leadership/hegemony) የሚኖረው፡፡ በመጡልን መባል ትልቅ ነገር ነው፡፡ እነሱ ስልጣን ቢይዙ በጎ ለውጥ ይመጣል መባል ትልቅ ፀጋ ነው፡፡

የአማራ ብሄርተኝነት ይለምልም!!!

Показано 20 последних публикаций.