ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የተላለፈ መልእክት፤
አገራችን ላይ የኮሮና ቫይረስ ከገባ ቀናት ተቆጥረዋል። ዳዴ እያለም ቢሆን ቁጥሩ እየጨመረ ይገኛል። ሊመጣ ለሚችለው ማዕበል ከሁላችንም ኃላፊነት ይጠበቃል። እርግጥ እኛ ሐኪሞችና የጤና ባለሙያዎች ወገናችንን የህይወት ዋጋ ከፍለንም ለማገልገል ዝግጁ ነን። በንደዚህ አይነት ጊዜ ከታማሚው የሚርቅ የጤና ባለሙያ የለም። ግን ጣሊያንና ስፔን መሰል ባለትላልቅ ኢኮኖሚና ጠንካራ የጤና ሴክተር አገሮች በሽታው የፈጠረውን ጫና ተመልክተናል። ለምሳሌ በዓለም 8ኛ የኢኮኖሚ ባለቤት የሆነችው ጣሊያን ኮሮና ከአቅሟ በላይ ሆኖ በአንድ ቀን ብቻ ከ700 ሰው በላይ ሰው ሲሞትባት አይተናል። እናም ከዚህ ተነስተን በአገራችን ካለው የጤና ሴክተር ደረጃና የሆስፒታሎቻችን አቅም አንጻር ትልቅ ፈተና ሊሆንብን እንደሚችል ከወዲሁ መገመት አለብን። እናም ከስር የዘረዘርኳቸውን ሐሳቦች በቀና ልብ እንድታዳርሱና የሚመለከታቸው አካላትም እንዲዘጋጁበት እንድናደርግ አሳስባለሁ።
1ኛ፤ ታማሚዎችም ለማከም በቂ ቦታ ስለማዘጋጀት፦ በመንግስታችን እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች እንዳሉ ባውቅም አይበለውና ቫይረሱ በስፋት መሰራጨት ቢጀምር በርካታ ታማሚዎችን ለይቶ ለማከም የሚያስችል፣ ለኮሮና ብቻ የሚያገለግል ሰፊ ቦታ ያስፈልገናል። ይህ ኃላፊነት በመንግስት ላይ ብቻ የሚጣል ሳይሆን የትላልቅ ሆቴል ባለቤቶችና ሌሎች ባለሃብቶች ወገኖቻቸውን የማስታመሚያ ስፍራ ለመስጠት ከወዲሁ ሊያስቡበት ይገባል። አብረን የመቆምና እንደምንለው የተቀደሰች ምድር ህዝቦች መሆናችንን የማሳየው ጊዜ አሁን ነው። ከመጸለያችን ጎን ለጎን በመረዳዳትና ከራስ ጥቅም በላይ ህዝብን በማስቀደም እንደ ስማችን መገኘት አለብን። በተጨማሪም እንደዚህ አይነት ማከሚያ ስፍራዎችን አዲስ አበባ ላይ ብቻ ማዘጋጀትም በቂ አይሆንም። በተለይ በዋና ዋና ከተሞች ለይቶ ማከሚያ ስፍራዎች ከበቂ አልጋና መሳሪያዎች ጋር ቀድሞ ማዘጋጀቱ በኋላ ከመጣደፍ ያድናል።
የቻይና ዉሃንና የሰሜን ጣሊያን ሆስፒታሎች በቦታ እጥረት ሰው በሰው ላይ ሲደራረብ ነበር። ይህም ተላላፊና ገዳይነቱን ጨምሮታል፣ ስለዚህ ቀድመን ቦታዎችን አዘጋጅተን እንጠብቅ። (ፈጣሪ ከጠበቀንና በሽታው እንደሌሎቹ ካላጠቃን ያዘጋጀናቸውን ቦታዎች ወደፊት ማፍረሱ ቀላል ነው፤ ሳንዘጋጅ ከተያዝን ግን ምንከፍለው ዋጋ ከባድ ነው!)
2ኛ፤ የህክምና መሳሪያዎች፦ በተለይም ጓንት፣ ጎግሎች፣ ማስክና የፕላስቲክ ልብሶችን መሰል የህክምና እቃዎች በተቻለው መጠን ተሰራጭተው በሚዘጋጁት ቦታዎች መቀመጥ አለባቸው። የአሊባባ ባላቤትና ሌሎችም የአገር ውስጥና የውጭ ባለሃብቶች እያረጉ ያሉትን ድጋፍ ማመስገን ያስፈልጋል። ግን እቃዎቹ ለክፉ ጊዜ በቂ መሆናቸውና መዳረሳቸውን በጊዜ ማረጋገጥ አለብን።
3ኛ፤ የህዝባችን ከበሽታው ራሱንና ሌላውን የመጠበቅ፣ ምልክቶቹ ካሉት ራሱን የማግለልና የሰውነቱ የመከላከል አቅም (Immunity) መገንባትን የሚመለከት ሲሆን በተለይም የሚዲያ ባለሙያዎች በዚህ 15 ቀን
ሰርግ፣ ስብሰባ፣ ለቅሶ፣ የመዝናኛ ኮንሰርትና ፓርቲዎች፣ የኃይማኖት ስርዓቶች፣ ትራንስፖርቶች... ወዘተ ላይ ሰዎች በብዛት መገኘት እንደማይችሉ አበክረው መናገር አለባቸው። ለትንሽ ጊዜ ሰዎች መራራቅና በተቻላቸው መጠን ንክኪን ማስቀረት እንዳለባቸው ማስተማር አለባቸው፤ ሁሉም በየአቅሙ ሳሙና፣ ሳኒታይዘር፣ መልቲቫይታሚንና ዚንክ እየገዛ አጠገቡ ለሚገኙ አቅም የሌላቸው (የኔ ቢጤና ጎዳና ተዳዳሪዎችን ጨምሮ) ማዳረስ አለበት።
እንዲህ በእውቀት፣ በእምነትና በመተሳሰብ ከቆምን እሱም ያግዘናል። ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ ነኝ - (ሼር በማድረግ የዜግነት ግዴታችሁን ተወጡ!
@wegoch