ደምበኛዋ ነኝ ፣ ደንበኛዬ ናት ያገልግሎት ገንዝብ ይሄን ያህል ነው ክፈል አትልም። ስንት ልክፈል ቀንሽልኝ አልላትም።
ሴተኛ አዳሪነቷን ላለማጉላት ነው ባደረች ቁጥር ክፈለኝ የማትለው? ሴተኛ አዳሪነቷን ላለማጉላት ይሆን በተኛን ቁጥር ስንት ነው ብዬ የማልከፍላት?
"የሆነ ብር አለህ እንዴ? ኪራይ መጣብኝ" ትለኛለች ያውም ብዙ ብር ነው ያለኝ ብዬ እሰጣታለሁ።
"ዛሬ አብረን እንሁን?" ስላት ብዙ ግዜ መልሷ እሺ ነው። የሴትነት ግዳጅ ላይ ብቻ አትሁን'ንጂ ቀጠሮ ቢኖራት 'ንኳ ትሰርዛለች...
ቀኑ 23 ከሆነም አትችልም።
"ታውቃለህ አይደል?"
ምኑን ዓይነት ስመለከታት...
"አንተን ማግኘት ብርታቴ እንደሆነ፤ ሴተኛ አዳሪነቴን ስለምታስረሳኝ፤ ታሪክ እንዳለኝ፥ ህልም እንዳለኝ አንተ ብቻ ነህ የምታስታውሰኝ!!"
ታውቃለህ ?
ዝምም ብዬ በትንሽ ፈገግታ ትክ ብዬ ሳያት...
እውነት እውነት ትላለች .....
ጠይም ናት፥ ቀጭን ናት፥ ሰልካካ ናት፥ ሁሉ ነገሯ ልከኛ ነው አብረን ተኝተን ነቅቼ አተኛኟን ሳየው ያሳዝናል
ሳለኝ ብላ የተኛች ሞዴል ትመስላለች።
"በ23 ለምን አሰሪም?" ስላት ከ23 ጋ ቁርኝት አለኝ 23 የኔ ቀን ብቻ ናት ትለኛለች።
አርፋለሁ!
"ሌላም ምክንያት ንገሪኝ?" ስላት "ሚስጥር ነው " አለቺኝ።
ሁሉንም አታወራም ስትከለክል ፈገግ ብላ ነው።
"ስወድሽ" አልኳት ...
"እምቢ" አለች ...!
ሁሌም ቤቴ ነው የምጠራት...ደርባባ ናት...ቆንጆ ናት። ቡርቴ ትባላለች ዐይኗ ጉልት ያለ ነው። ቤቴ ስትመጣ ተመላላሽ ሰራተኛዬ ሰትሠራ ያጎደችውን ትሞላለች፤ ያልጸዳውኝ ታፀዳለች። ወጥ ልስራ ምን ልስራልህ? ትላለች።
እንዴት አከበርኳት? እንዴት አከበረቺኝ? አላውቅም !
እንደዚህች ዓይነት ደርባባ እንዴት ሴተኛ አዳሪ ሆነች?
ገጠመኜን አወራታለሁ ትሰማኛለች ዕቅዴን እነግራታለሁ ትሰማኛለች አሰማሟ ምቾት ስላለዉ አወራለሁ ።
ብሶት እና እጦቴን ከራሷ አንፃር አይታ አታፅናናኝም በመረዳት በማዘን ነው የምትሰማኝ አሰማሟ እኔ የተሻልኩ ቦታ ላይ እንዳለሁ አይደለም !!
ሳማክራት ገላዋን በመሸጥ ለምትተዳደር በጣም ሲከፋት መጠጥ ውስጥ የተሸሸገች ሴት ምክር የምጠይቅ አልመስልም !
ሰው ባለበት ቦታ ብቻ አይመዘንም ኣ!
እንዋሰባለን ጡቷንም ከንፈሯንም ትፈቅድልኛለች። ወሲባችን የወንድ አዳሪ እና የሴት አዳሪ አይመስልም ትንሽ መዋደድ፥ ትንሽ መነፋፈቅ፥ ትንሽ ሕይወት ያለው ይመስለኛል ።
"ቡርቴ ለምን ሴተኛ አዳሪ ሆንሽ ?"
ሆኜ ነው ራሴን ያገኘሁት። መች እንደሆንኩ ቀኑን በትክክል አላውቅም ።
ዳዊት ነው ሴተኛ አዳሪ ያደረገኝ ። ዳዊትን ሳውቀው ዳዊት የተባለው ባጋጣሚ አይደለም አልኩኝ ። ምቹ እንደልቤ የሚባል ፍጡር ነው ።
እድሜ ይበልጠኝ ነበር
ትሁት ነው፥ ሃብታም ነው፥ ጨዋታ ይችላል፥ የማላውቃቸውን ውድ ሽቶዎች፥ የማላውቃቸውን ብራንድ ልብሶችና ውድ ጌጣጌጦች፣ ትላልቅ መዝናኛ ቦታዎች አሳየኝ። ዝነኛ ሰዎች ጋር አስተዋወቀኝ ።
ያስፈልጋታል የሚለውን ሁሉ ያደላድልልኝ ጀመር። ለቤተሰቦቼ መትረፍ ቻልኩ። ዳዊትን ከማግኘቴ በፊት የነበረኝ መርህ፥ አቋም ዕይታ ላላ። ዳዊት ሆነ የሚዘውረኝ...
ክብረ ንፅህናዬን፥ መንገዴ ዕይታዬ በዳዊት ተወሰደ...ከሃይማኖታዊ ስፍራ ራኩኝ ።
ቀስስ እያለ ውሎውን አዋለኝ። ውሎውን ለመድኩ። መጠጥ ለመድኩ። ማጨስ ለመድኩ...
የሆነ ቀን አንዲት ማድያት ያለባት ዕድሜ የምትበልጠኝ ቆንጀ መልከ መልካም መጥታ "ከትዳሬ ውጪልኝ አለቺኝ.... "
ስለምን እንደምታወራ አልገባኝም ነበር። ዳዊት ባለትዳር እንደሆነ ሦስት ልጆች እንዳሉት ከብዙ አባሪ ጋ አሳየቺኝ...
ለካ ቅምጡ ነበርኩ...
ስታወራኝ ብዙ ነገሬ በድን ሆኖ ነበር። ድንግጥ አልኩ ! ህልም መስሎኝ ነበር! ፈርቼ ነበር! አደባባይ ላይ እርቃን እንደ መቆም ዓይነት ስሜት ተሰማኝ። የሚያደርግልኝ ነገር ሁ፥ የሚያሳየኝ ነገር ሁሉ ግዚያዊ ነገር ብቻ ነበር።
ያወራናቸውንና የተላላክናቸውን የፅሁፍ እና የድምፅ መልዕክቶች በረበርኳቸው፤ ሁሉንም !! አንድም ስለ ልጆቹ፥ አንድም ስለሚስቱ ያወራልኝ ቦታ ሳላገኝ ቀረሁ።
የመጣንባቸውን መንገዶች፥ ሁኔታዎች ሳሰላስላቸው እንቅስቃሴው እና የሚወስደኝ የምናወራው ነገር ሁሉ ቅምጡ እንደ ነበርኩ ምልክቶች ነበሩት ።
አንዴንዴ የሚታይ ነገር መመልከቻችን ይታወራል !! ለሁሉም የሚታይ ነገር ለኛ ይሸሸጋል!
ዳዊት ዐይኑን በጨው አጥቦ ሌላ ማልያ ለብሶ መጣ። እንደገና ሌላ ማሳመኛ ይዞ መጣ።
ይሄን ያህል ደደብ ነው የምመስለው?? እንደገና ሌላ ሃዘን አጠቃኝ...
ጓደኛው አፅናናኝ ...
ወቀሰልኝ... አብሮኝ ቆመ... ተቆረቆረልኝ...አለሁልሽ አለኝ...አብሮኝ ሆነ...በዳዊት ቦታ በሂደት ተካኝ። ጓደኛ ሆኖ መጥቶ ቅምጥ አደረገኝ።
ሌላ አገር ሄደ ...
ሌላ እሱ ያስተዋወቀኝ ጓደኛዉ ቢዝነስ ሊያስጀምረኝ ቃል ገብቶልኝ ስናወራ ስንግባባ ስናወራ ስንውል ስናመሽ በሂደት ራሳችንን አልጋ ላይ ማግኘት ጀመርን።
የሆነ ቀን ለከፈለኝ ሁሉ ቀሚሴን ስገልብ እራሴን አገኘሁት። ለራሴ ያለኝ ክብር በሂደት ተሸረሸረ ።
ለከፈለኝ ሁሉ እርቃኔን የማሳይ ሆንኩ፣ ከከፈለኝ ሁሉ ጋ እተኛለሁ ።
ብዙ ግዜ ራሴን ላጠፋ አስቤ አውቃለሁ።
ምን ያዘሽ?
ተስፋ ... !
የማውቃቸው ሴተኛ አዳሪዎቹ ሲያልፍላቸው፤ ሲያገቡ ሲያምርባቸው ተስፋ አደርጋለሁ!! የወደቀ ሲነሳ ስመለከት ተስፋ አደርጋለሁ!
ያጣ ሲያገኝ ሳይ ተስፋ አደርጋለሁ! በየደረጃችን ተስፋ ላይ ሙጥኝ ብለን የምንልወሰወስ ፍጡር ነን አይደል?!!
ቡርቴ?
ወዬ
ምን መሆን ትፈልግያለሽ ?
ብዙ ነገር! ግን ሁሉም ዕቅዴ ውስጥ ከሴተኛ አዳሪ ሕይወት መውጣት የሚል አለ።
By Adhanom Mitiku
@wegoch
@wegoch
@paappii