Репост из: ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል
ጌታችን መጻጉዕን የፈወሰበትን፣ አልዓዛርን ከሞት ያስነሣበትን፣ ዓይን ያበራበትን፣ በአጋንንት እስራት የተያዙትን ነጻ ያወጣበትን፣ ዕለት በክብረ በዓል ደረጃ ሳታከብር የቃናው ተአምር ከጌታችን ንዑሳን በዓላት ውስጥ ተደምሮ እንዲከበር ያደረገችበት ጥልቅ ምሥጢርን ስለያዘና ስላዘለ ነው፡፡ ይህ ሰርግ የሚደረገው ጌታችን ከአእላፋት መላእክቱ ጋር በሚመጣበት በዕለተ ምጽአት ነው፡፡ ዕለተ ምጽአት ሙሽራዪቱ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በቅዱሳን ምግባር አጊጣ የምትታይበት፣ የጽድቅ ዘይት ይዘው መገኘት የቻሉ ልባሞች ከቤተ ክርስቲያን ጋር ሰርጉን የሚታደሙበት፣ እንደ ቃናው ደስታ በሰማያዊቱም ኢየሩሳሌም፥ በደስታም ወደ ተሰበሰቡት ወደ አእላፋት መላእከት በሰማያትም ወደ ተጻፉ ወደ በኵራት ማኅበር፥ የሁሉም ዳኛ ወደሚሆን ወደ እግዚአብሔር፥ ፍጹማንም ወደ ሆኑት ወደ ጻድቃን መንፈሳት የምንደርስበት ዕለት ነው፡፡ (ዕብ.፲፱፥፳፪)
ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ የቃናን ሰርግ ከሰማያዊው ሰርግ ጋር አሰናስሎ ሲያመስግን እንዲህ ይላል፡፡ “ወደ ሰርግ በዓልዋ ዕለት ደስታን ይዘህላት ስለመጣህ ቃና ታመስግንህ! አክብረኸዋልና ሙሽራው የደፋው ዘውድ አንተን ያከብርሃል። የሙሽራዋ አክሊልም የአንተን ድንቅ ሥራ ያደንቃል፡፡ ቤተ ክርስቲያንህን በሙሽራዋ መስለሃታልና በቃና መስታወትነት ምሳሌዎች ሁሉ ትርጒማቸውን አገኙ፡፡ የቃናዎቹ እንግዶች ደግሞ አንተ የመረጥሃቸው (ወደ ሰማያዊው ራት) የጠራሃቸው ናቸው:: ምጽአትህንም በሰርግ ቤቱ ደስታ መሰልከው::”
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንደ ሙሽራ አጊጣ፣ ለበጉ ሰርግ ያለ እድፍና ያለ ነውር ውብ ሆና ተዘጋጅታ በምትቀርብበት በዚያ ሰማያዊ ሰርግ ለመገኘትና ወደ በጉ ሰርግ ራት ገብተን፣ ካጌጡ ቅዱሳን ጋር ለመቀመጥና ለመብላት የበቃን ያድርገን!
መልካም በዓል!
ምንጭ፡- ትርጓሜ ወንጌል እና “ቃና ዘገሊላ”
በዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ