ልብ አንጠልጣዩ "የጠፋው ሬሳ"
ተከታታይ ትረካ
#ክፍል_፩
.......ሜርሲ
እባላለሁ ቤተሰቦቼ እጅግ የናጠጡ ሀብታም ናቸው የተወለድኩ ወድምም እህትም የሌለኝ የቤቱ ብቻ ልጅ ነኝ...ያልኩት ይደረግልኛል አንዲትም ሳትቀር በጣም ይሽቆጠቆጡልኛል ዛሬም ዕለቱ የትምህርት ማቆሚያ የክረምቱ ደግሞ መጀመሪያ ስለሆነ ከጓደኞቻችን ጋር ወጣ ብለን የመለያያ ፕሮግራም ለማድረግ እየተዘገጃጀሁ ነው ለሳምት እንቆያለን ስለተባለ ልብሶቼን በሻንጣ በውል አዘጋጀሁ..."ሜርሲ ሜርሲ" አለች የቤት ምግብ አብሳያችን *አቤት ስንዱ* አልኳት የመኝታ ክፍሌን መዝጊያ እየከፈትኩ "አቶ አላዛር ሊያናግሩሽ ይፈልጋሉ" አለችኝ "እሺ መጣሁ" አልኳት አቶ አላዛር ማለት ውዱ አባቴ ነው...የመኝታ ቤቱን እያንኳኳሁ "ልግባ አባቢ" አልኩት "ግቢ የኔ ልጅ" አለኝ በምላሹ እኔም ወደ ውስጥ ገባሁ "እንዴት አደርሽልኝ የኔ ልዕልት ነይ እስቲ" ብሎ ግንባሬን ሳመኝ "የቀኖቹ ባለቤት እሱ ይመስገን ዛሬም አዲስ ቀን አየሁ" አልኩት "የኔ አንደበተ ማር ቃሎችሽ እኮ እንደ ከርቤ ዕጣን ያውዳሉ"አለኝ አልጋው ጎን ተቀምጬ ፀጉሬን እየነካካ "አባቢ ደሞ ምን የተለየ ነገር ተናግሬ ነው" አልኩት "እኔ ያልኩትን ራሱ ብትደግሚልኝ እንደ አዲስ ብርቅ ሆኖብኝ ነው ምሰማው" ብሎ ፈገግ አለ "ማሚስ የት ሄዳ ነው በጠዋት" ብዬ ጠየኩት "ጉዞ ሄዳለሁ ብለሽ የለ ከስንዱ ጋር ለጉዞሽ የሚሆን ስንቅ እየሰሩልሽ ነው የሆቴል ምግብ እንደማትጠቀሚ እያወቀች ዝም ብላ አትለቅሽ" አለኝ "እውይ የኔ እናት ሄጄ ልጠምጠምባታ" ብዬ ከአልጋው ስነሳ "የተጠራሽበትን ዋና ጉዳይ ሳልነግርሽ ወዴት ልትሄጂ ነው" አለኝ "እሺ ንገረኝ" አልኩት ወድያውኑ "ት/ት ቤት የሚያመላልስሽ ሹፌር አብሮሽ እንዲሆን ነግሬዋለሁ ከከተማ ውጪ ማንም አጠገብሽ ሳይኖር ብቻሽን ልተውሽ አልፈልግም አሁን ይመጣል"አለ "አረ አባቢ ችግር የለውም ጓደኞቼ እኮ አሉ ብዙ ነን የኔ አሳቢ አባቴ አመሠግናለሁ በነፃነት እንድዝነናና ፍቀድልኝ አባቢ ይሄን ብቻ ተቸገርልኝ ደሞኮ አድጌያለሁ"አልኩት "እሺ እንዳልሽ ስልክሽ ግን ሁሌም ክፍት አርጊው በምንም አይነት ሁኔታ ዝግ እንዳይሆን እንደውላለን አንቺም ደውዪ" አለኝ ማስጠንቀቂያ በሚመስል ትዕዛዝ "እሺ የኔ አባት አታስብ" ብዬ ግንባሩን ስሚው ከክፍሉ ወጣሁ ከዛ ማሚ ከኔ ክላስ ስትወጣ አየሗት የኔ እናት ብዬ ጥምጥም አልኩባትና ጉንጯን ሳምኳት "አረ ቀስ ወዜን እንዳትመጪው" አለችኝ እቅፍ አርጋ እየሳመችኝ..."የኔ ልጅ በጣም ተጠንቀቂ እሺ ነገሮችን በማስተዋል አድርጊ" አለችኝ ለኔ እጅግ እንደምትሳሳ አይኗ ላይ ይነበባል "እሺ የኔ እናት አታስቢ እኔ ያንቺ ልጅ አድጌልሻለሁ እኮ" አልኳት "ፈጣሪ ይመስገን ጎርምሰሽልኛል መልካም መንገድ የኔ ልጅ ታዲያ ቶሎ ቶሎ ደውዪ እሺ እድንጨነቅ አታርጊን" አለችኝ "እሺ እናቴ" ብዬ ወደ መኝታ ክፍሌ ገባሁ ተለቅ ያለ አገልግል ጠረጴዛዬ ላይ ተቀምጧል አይ የኔ እናት ...ለጉዞዬ የመረጥኩትን ልብስ ለበስኩኝ እጅግ አማረብኝ ስለ ራስሽ አወራሽ አትበሉኝና...እጅግ በጣም ቆንጅዬ ሴት ነኝ የናቴ ልጅ ራሴን በጣም ነው ማቆለጳጵሰው ሌላ ማን ያቆለጳጵሰኛል "ስንዱ ዕቃዬን ታግዢኛለሽ" አልኳት ድምፄን ከፍ አድርጌ በሩን ከፍቼ አንገቴን አስግጌ ጠራሗት "እሺ ሜርሲዬ" ብላ መጣች እሷ ሻንጣውን እኔ ደግሞ አገልግሉን ይዤ ወደ መውጫው ጉዞ ጀመርን "የኔ አባት እና የኔ እናት ትናፍቁኛላችሁ እስክንገናኝ ምወደው ፈጣሪዬ ምወዳቹን ይጠብቅልኝ"አልኳቸው ድምፄን ከፍ አድርጌ "እሺ ሰላም ግቢልን የኛ ልጅ" አለ አባቢ ማሚ መዳፏን እያወዛወዘች በፈገግታ ሸኘችኝ...የሳሎኑን በር ዘግቼ ወጣሁ የግቢ ጠባቂያችን "አምጪው ሜርሲዬ" ብሎ አገልግሉን ተቀበለኝ "አመሠግናለሁ አስራት አምላክ ይባርክህ" አልኩት "አሜን አለኝ በምላሹ "እና ምን አዲስ ነገር አለ" አልኩት "ምንም ሜርሲዬ ይነጋል ይመሻል ድጋሜ ይነጋል ድጋሜ ይመሻል" አለኝ በውስጤ "አይ የሰው ልጅ ምን አዲስ ነገር አለ ሲባል ምንም ይላል የዛሬውን ቀን ከዛሬ በፊት ያየውና ውሎ ያደረበት ይመስል"እላለሁኝ ግን ለአስራት መልስ አልሰጠሁትም ነበር...ጓደኞቼ ድረስ የሚያደርሰኝ ሹፌሬ ደጅ ላይ ቆሞ እየጠበቀኝ ነው "ሰላም አደርክ" አልኩትኝ ኮፈኑን እንዲከፍትልኝ በእጄ እየጠቆምኩት ወዲያው ከፈተው "አስራት አገልግሉን ከውስጥ አርገው ስንድዬ ሻንጣውን እዚ አስገቢው"አልኳቸው ሁለቱም "እሺ አሉኝ...እቅፍ አርጌ ሳምኳቸውና ሰላም ያገናኘን ብዬ ወደ መኪናው ገባሁ...
.........P.2..ይቀጥላል...........
ከተመቻቹ ÷
#𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
#𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
#𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏
¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱