ልብ አንጠልጣዩ "የጠፋው ሬሳ"
ተከታታይ ትረካ
#ክፍል_፮
.......ሙሉ በሙሉ ከእግር እስከ ራሱ ጥቁር በጥቁር ለብሶ ጀርቦውን ለኔ ሰጥቶ አንድ ሰው ቆሞ አየው የምሆነው የማረገው ጠፋኝ ተርበተበትኩ መጮህ እየፈለኩ አልቻልኩም መሮጥ እየፈለኩ እግሬ ከዳኝ ብቻ ባትሪውን እሱ ላይ አነጣጥሬ ዝም ብዬ ቆምኩኝ ላቤ እንደ ጉድር ይወርዳል ሰውነቴ ግሏል አተነፋፈሴ ተቀይሯል እንደውም መተንፈስ እየተሳነኝ ነው ከፊት ለፊቴ የቆመው ሰው አንገቱን ወደኔ ማዞር ጀመረ በዚህ ጊዜ እግሮቼ ወደሗላ ማፈግፈግ ጀመሩ ድንገት ከበስተሗላዬ የሳቅ ድምፅ ሰማው በድንጋጤ ከመቅፅበት ዞርኩኝ ግን ማንም አልነበረም ፊቴን ወዲያውኑ ወደ ቅድሙ ሰው መለስኩ ግን እሱም አልነበረም...አሁን ይሄንን ነው መፍራት ያየሗቸው እና የሰማሗቸው ከአይኔ ይሸሻሉ...ጥንቃቄ በተሞላው አረማመድ ሀሳቤን ቀይሬ ወደ ድንኳኑ ማዝገም ጀመርኩ ዞሪያዬን እየቃኘው መጓዜን ቀጠልኩ እኔ ከማበረው ባትሪ ውጪ ጫካው በድቅድቅ ጨለማ ተውጧል እርምጃዬ ከመቆም አይተናነስም በጣም ዝግ ያለ ነው...ውስጤ በጣም እየፈራ ነው እዚ ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ብቻዬን መጓዜ ለራሴም እየደነቀኝ ነው የሚያግዘኝ አንዳች ልዩ ሀይል እንዳለ ይሰማኛል...ከራሴ ጋር እያወራሁ ጉዞዬን እየቀጠልኩኝ ሳለ ከበስተሗላዬ መሬት ላይ የሚንፏቀቅ የብረት ድምፅ ተሰማኝ ወዲያውኑ ዞርኩኝ ግን ምንም አልነበረም...የሚከተለኝ ነገር እንዳለ ጀርባዬ ይነግረኛል ጥላውም አካሌ ላይ ይከብደኛል ግን ከአይኔ ከመቅፅበት ይሰወራል ይህ ነገር ከመንፈስ ጋር ጥብቅ ትስስር እንዳለው ይሰማኛል ከጨለማው ጋ ተዋዶ ነፍስን የሚያስጨንቅ ክፉ መንፈስ ነው...ይሄን ሀሳብ በውስጤ እያመላለስኩ ሳለ በድንገት ከጨገገው ሰማይ ላይ ፍክት ያለች ጨረቃ ወጣች ሰዓቱ ወደ እኩለ ለሊት እየተጓዘ ነው የተከሰተው ነገር እጅግ አስደነቀኝ ወዲያው የሰይጣን መልዕክተኛ የሚባለው የወፍ ዘር(ቁራ) ከየት መጣ ሳይባል አጠገቤ ካለ ዛፍ ላይ ቆሞ በእኩለ ለሊት መጮህ ጀመረ ድምፁ እስከዛሬ ከሰማዋቸው ድምፆች ከበደኝ መሬት ላይ ወደኩ ጆሮዬንም በእጆቼ ያዤ እዛው መሬት ላይ ቀረሁ ግን የቱንም ያህል ጆሮዬን ብይዘውም ድምፁን ማቆም አልቻልኩም ከመጠን አልፎ አወከኝ ልቤን አደከመው አንዳች ሀይል ከሱ ጋር እንዳለ ያስታውቃል ከድምፁ መሀል ብዙ የጣር ድምፆች ይሰማሉ "ወይኔ...ኡኡኡ" የሚሉ አይነት ድምፆች አልፎ አልፎም ሳቅ ይቀላቀልበታል እዛው በተኛሁበት ለደቂቃዎች ቆየሁኝ የቁራው ድምፅ የለም ቁራውም ከዛፉ ላይ አይታይም ጨረቃዋል ጠልቃለች ጫካው ወደ ቀድሙ ድቅድቅ ጨለማነቱ ተመልሷል የማየውን ነገር ማመን አቅቶኛል ከተኛሁበት በእርጋታ ተነሳሁኝ...ቁራው ሲጮህ ደንግጬ ስወድቅ ባትሪውን ጥዬው ነበር እሱንም ለመፈለግ በእጆቼ መዳበስ ጀመርኩ ላገኘው አልቻልኩም በጉልበቴ እየዳሁ መፈለጌን ቀጠልኩ ከትንሽ ፍለጋ በሗላ በሁለቱም እጄ የሚያዝ ነገር አገኘሁ በግራ እጄ ባትሪውን እንዳገኘሁት ተረድቻለሁ ግን ቀኝ እጄ ላይ ያለውን ማስተዋል አልቻልኩም...ባትሪውን አብርቼ ስመለከተው ሰዓት ያለበት የሰው እጅ ነበር በድንጋጤ እሪታዬን አቀለጥኩት ወዲያውኑ እነ ባርሰናይት ስሜን እየተጣሩ በመደናገጥ ስሜት ውስጥ ሆነው ወደኔ መጡ "ሜርሲ ሜርሲ" እያሉ ደጋግመው ይጣራሉ አንደበቴ ተሳስሯል ምላሽ መስጣት አልቻልኩም ብቻ ያለሁበትን እንዲያውቁ ባትሪውን ከፍ አድርጌ አበራሁት ሁሉም ወደኔ መጡ "ምን ሆንሽ ሜርሲዬ" ብላ ቅድስቴ ተንበርክካ እቅፍ አረገችኝ ምንም ምላሽ አልሰጠሗትም ብቻ የማልቆጣጠረው እንባ ከአይኔ ይወርዳል ባባም ግራ ቀኙን ከቃኘ በሗላ "የሆንሽውን ተረጋግተሽ ንገሪን ሜርሲ" አለኝ ለሱም ምላሽ አልሰጠሁትም ዝም ነበር ያልኩት እንደሚመስለኝ የቅድሙ የቁራ ጩኸት እና የጨረቃዋ ወገግታ ለኔ ብቻ ነው የታየኝ ግን የ፡እጁ ለሁሉም ይታያል ብዬ አሰብኩ ወዳስጮኸኝ ነገር ባትሪዬ አበራሁላቸው ሁሉም ተደናገጡ "ተነሺ ከዚ አካባቢ እንራቅ" አለ ባባ በእጆቹ እኔን ለማንሳት እየሞከረ...እንደምንም ብዬ ተነሳሁና ወደ ድንኳናችን አመራን እነ ባርሳ በጣም ፈርተዋል ባባ በያዘው ባትሪ ዙሪያውን እየቃኘ ደህንነታችንን እየጠበቀ ነው ዱንኳናችን ጋ እንደደረስን መተኛት እንደምፈልግ ነግሬያቸው ወደ ድንኳኔ አስገቡኝ ጭንቀቴንና የተፈጠሩትን ነገሮች ለመርሳት እንቅልፍ የተሻለ ነውና ጋደም አልኩኝ ከደቂቃዎች በሗላ ቅድስቴ ጮኸች ከተኛሁበት ተስፈንጥሬ ተነሳሁና ወደሷ አመራሁ ባባ እና ባርሰናይትም አብረዋት ነበሩ "ምንድነው ቅድስቴ" ብዬ ወደሷ ተጠጋሁ "አንቺጋ ስንመጣ ሮቤል ተኝቶ ነበር አሁን ፍራሹ ላይ ያለው ደሙ ብቻ ነው".........
........P.7....ይቀጥላል.........
ቶሎ ቶሎ እንድለቅ 👍አሳዩኝ
ከተመቻቹ ÷
#𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
#𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
#𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏
¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱