ልብ አንጠልጣዩ ተከታታይ ትረካ
ምዕራፍ 2 #ክፍል6
......እሳት ጎርሶ እሳት ለብሶ ሲራመድ የእግሩ ዳና ይናገራል...ከዚ ስቃይ ለመገላገል እና የስጋዊ ጉዞዬን እንደጨረስኩ ይሰማኛል እዛው ተቀምጬ እንዳለሁ ፀጉሬን ይዞ እየጎተተ ወደ
መሃል አስጠጋኝ...የቆሰለው አካሌ ከወለሉ ጋር በተፈጠረው ፍትጊያ
እየተላላጠ ስቃዬን አበዛው በድጋሜ
እጅግ ቀዝቃዛ ውሃ ደፋብኝ አቤት ስቃይ
...ወለሉ ላይ ኩርምት ብዬ ተኝቼ አካሌ
ይንዘፈዘፋል ትንፋሼ እየተቆራረጠ ልብ
ምቴ ሊቆም እንደሆነ ይሰማኛል ግን ዘገየ
እኔ ስቃዩን አልቻልኩትም ከበደኝ...ፀጉሬን
ከአይኔ ላይ ገለል አድርጌ ስመለከት ጀርባውን ለኔ ሰቶኝ ከአንድ ጠረጴዛ ፊት ለፊት ቆሟል
ነገር ግን ምን ያደርግ እንደነበር መለየት አልተቻለኝም ጭንቅላቴ ለአንገቴ እንደ አንዳች ከባድ ሸክም ሆኖበታል...
እየደጋገምኩ ለመነሳት ብሞክርም አልቻልኩም...ጤናማ ሆነህ ያደረካቸው
ተራ ነገሮች አቅምህ ተሟጦ ስታስባቸው
ምነኛ እንደሚናፍቁ አሁን ተረዳሁኝ...
አንዳች ክስተት ተፈጥሮ ከዚ ሞት ካጠላበት የተረገመ ቤት ሞቼም ቢሆን
በወጣው አልኩኝ...ወለሉ ላይ ተንጋልዬ
ሽቅብ ሰውዬውን ስመለከት ያንን ደም የለመደ መጥረቢያ ይዞ ወደኔ እየተራመደ
መጣ አጠገቤም ደርሶ መጥረቢያውን
መሬት አስደግፎ ይዞረኝ ጀመር ለምን እንደሆነ ምክንያቱን ባላውቅም...ልክ በአይኔ ትይዩ ሲደርስ ጫማውን ስመለከተው ትናንሽ ስጋዎች እና የረጋ የደም ጠብታ ይታይበታል...አሟሟቴን ማሰብ ጀመርኩ "ድንገት ሳላስበው
ጭንቅላቴን ሁለት ያረገው ይሆን ወይስ
አንገቴን በጥሶ ይጥላዋል?" እያልኩ
መልስ አልባ ጥያቄዎችን ራሴን ጠየኩት
በተኛሁበት እየዞረኝ ደቂቃዎች ተቆጠሩ...
ነገር ግን ሰውዬው እስካሁን አንዳች ነገር
አላደረገኝም ይህ ሁኔታ ግራ ሆነብኝ...
በድንገት ሌላው ክፍል ባርሳ እንዳለች ትዝ አለኝ ትኑር ትሙት ግን አንዳች አላውቅም...አረመኔው ሰውዬ እንደጨቀነቀው እየተሰማኝ ነው ያለማቋረጥ ዝም ብሎ ይዞረኛል ስሜቱን በደንብ ለመረዳት እንደምንም ክንዴን ተመርኩዤ ቀና ስል ደም ባቆረፈደው ጫማ ከስር ወደላይ በግራ ጉንጬ በኩል ጥርሶቼ የተራገፉ እስኪመስለኝ ድረስ
ህመሙ ዘልቆ ተሰማኝ...ከሰውዬው ምት
የባሰው ደግሞ ጭንቅላቴን የተቀበለው
ወለል ነበር ደም ደም ሸተተኝ አፍንጫዬን
ነሰረኝ ጭንቅላቴም መድማት ጀመረ...
በዚ ሁኔታ ውስጥ እያለሁ በድጋሜ ፀጉሬን ይዞ ጎተተኝና ግድግዳ አስደግፎ
አስቀመጠኝ ከዛም የመጥረቢያውን ስለት አዞረና የግራ እግሬን ከጉልበቴ በታች ያለውን አጥንቴን ክፉኛ መታኝ ድምፄንም ከፍ አድርጌ ጮውኩኝ እየደጋገምኩ ጮውኩኝ አምርሬም አነባሁ
አጥንቴን ስለመታኝ ህመሙን አልቻልኩትም እግሬን ታቅፌ ወለሉ ላይ
ተኛሁኝ እግዜር ምን እስከሆን እየጠበቀኝ
እንዳለ ጥያቄ ሆኖብኛል መላ አካሌ ዝሏል ሞት ብቻ ነው የቀረኝ ግን ደሞ
ሞቴ በጣም ዘገየ...ሰውዬው አሁንም ፀጉሬን ይዞ ጎትቶ ግድግዳው ላይ
አስደገፈኝ ደሜ ከአናቴ ሲንቆረቆር ገላዬ
ላይ ይታወቀኛል የእግሬ አጥንት የተሰነጠቀ እስኪመስለኝ ድረስ ይቆረጥመኛል በዚ ስቃይ ውስጥ እያለሁ
ቀዝቃዛውን ውሃ በድጋሜ ደፋብኝ ከዛም ፊት ለፊቴ ተንበርክኮ አንገቴን ሲጥ አርጎ
አንቆ እየደጋገመ ከግድግዳው ጋር በሃይል ያጋጨኝ ጀመር ከዛም የፊጢኝ ያነቀውን አንገቴን ለቀቀው ወዲያውኑ ተዝለፍልፌ ወለሉ ላይ ተንጋለልኩ ደሜ ያለማቋረጥ እየፈሰሰ
በጆሮዬ ስር ይወርዳል የማየው ነገር ሁሉ መሽከርከር ጀመረ...
እያዞረኝ እንደሆነም ተሰማኝ ቀስ በቀስ የማየው ነገር እየደበዘዘ መጣ
ወዲያውኑም ጭልም አለብኝ ምንም ማየት አልቻልኩም ኩርምትምት እንዳልኩኝ
በደም ተጨማልቄና ረጥቤ ራሴን ሳትኩኝ.........
ምዕራፍ 2 .P7...ይቀጥላል.........
ከተመቻቹ ÷
#𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
#𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
#𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏
¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱