♥️ ተማሪዋ ♥️ ...
🌹...ክፍል 36...🌹
.
.
.
.
ጆሮዬን ማመን ተሳነኝ። ከባልቦላው ያጠፋችኝ ያህል ውስጤ ድርግምግም አለ። ከነበርኩበት ጣፋጭ የፍቅር ትኩሳት ወርጄ በረዶ ሆንኩ።
ተወርውሬ ደብዘዝ ያለውን መብራት ቦግ ሳደርገው ከስሬ የተንጋለለችው ቃል አይኗን ከሀይለኛው ብርሀን ለመከላከል በክንዷ እንደመጋረድ እያለች "ምነው ኤፍዬ?" ስትለኝ በዝምታ አፈጠጥኩባት።
"ምነው ኤፊ ለምን አበራኸው?" አለችኝ ደግማ ክንዷን ገለጥ አድርጋ እየተመለከተችኝ።
"አአአአ አሁን ምንድን ነው ያልሽው ቃል?" አልኳት
"ለምን አበራኸው ነዋ ያልኩህ አይሰማህም እንዴ ኤፍዬ"
"አይ ከዛ በፊት"
"ከዛ በፊት ማለት?"
"ከማብራቴ በፊት ምንድን ነው ያልሽው
ኪኪኪ እንዴ እሱንም እማ አልደግመውም "
"ለምን ? ለምንድን ነው እማትደግሚው?"
"እህ በፍቅር እና በስሜት ውስጥ ሆነህ ያወራኸውን ነገር እኮ ሲደገም ይለዛል ለዛው ይጠፋል ደስ አይልም"
"ግድ የለም እኔ መስማት ስለምፈልግ ድገሚው"
"መስማት ስለፈለክ ነው ወይስ ደግመህ መስማት ስለፈለክ"
"ደግሜ መስማት ስለፈለኩ ?" አልኳት እሷ በፈገግታ ውስጥ ሆና እያወራችኝ ስለነበር ደግማልኝ እስክሰማው መደንገጤም መለወጤም እንዳይታወቅብኝ እየሞከርኩ።
"በናትህ መብራቱን እንደቅድሙ አድርገው ኤፍዬ?"
"ንገሪኛ መጀመሪያ"
"እንዴ ካልደገምኩልህ አታጠፋውም እኔ አጠፋዋለሁዋ ምነው ማሽከርከር የሚያቅተኝ መሰለህ እንዴ ብላ ቀና አለችና ማብሪያ ማጥፉያውን ወደ ግራ ዘውራ አደበዘዘችው።
" እና አትነግሪኝም "
"አልነግርህም "
"ቃልዬ እባክሽ "
"እንዴ••የምርህን ነው አንጣ ወረቀትና እስክርቢቶ ያልኩትን ልፃፍልህና ሌላ ግዜ አልተሸነፍኩም ብዬ ብክድ እንኳን ማስረጃ ይሆንሃል ከፈለክም ደጋግመህ ታነበዋለህ ኪኪኪኪ"
ቃልዬ ምን እያለች እንደሆነ ሊገባኝ አልቻለም።በዚህ ሰአት ወረቀትና እስክርቢቶ ኬት ያመጣል ብላ ነው አደል የምትጫወትብኝ አልኩና ስልኬን አንስቼ ከስልኬ ላይ የማስታወሻ መፃፊያውን መተግበሪያ ከፍቼ
"ይሄው መጨረሻ ላይ ያልሽኝን እዚህ ላይ ፃፉልኝ ወረቀት ምናምን ኬት ይመጣል በዚህ ሰአት "
"አይ ኤፍዬ!" እያለች ሞባይሉ ላይ ፃፈችና ሰጠችኝ።
ፅሁፉን ሳነበው ሽምቅቅ ብዬ አንድ ፍሬ አከልኩ ። ቃልዬ ሞባይሌ ላይ ፅፋ የሰጠችኝ •••" ዛልኩልህ የኔ ፍቅር ይላል።
ጆሮዬ እና አይኔ መስማማት አቃታቸው። ማንን እንደምረግም ግራ ገባኝ ። ጆሮዬን ልርገም ሀሳቤን? ። ውስጤ ያ ሀሳብ ያ ጥርጣሬ ባይኖር ጆርዮ ኬት አምጥቶ "ዛልኩልህ የኔ ፍቅር " የሚለውን ንግግር ዛኪዬ የኔ ፍቅር ብሎ ይሰማል።
ጥርጣሬ የፍቅር ሰንኮፍ የደስታ ጭንጋፍ ነው ። እኔ የምፈልገው ከቃልዬ ጋር በደስታ እና በፍቅር መቀጠል ነው። ስለዛ ልጅ ማሰብ ካላቆምኩ ደግሞ ያንን ማጣጣም አልችልም። ለአንደና ለመጨረሻ ግዜ ከአይምሮዬ ላወጣው ምንም ሳይፈጠር ምንም የተጨበጠ ነገር ሳይኖር ዝም ብዬ ስለሱ ላላስብ ላልጨነቅ ቃልዬንም ላላስጨንቅ ለራሴ ቃል ገባሁ።
"አንተ ጨቅጫቃ ሴቭ አድርገውና ሁሌ አንበበው እሺ መሸነፏን ትክዳለች ብለህ ነው አደል ካልደገምሽው ብለህ እርርይ ያልከው ኪኪኪ ሆሆ በቃ አሸንፈኻል ተሳክቶልሀል እሺ ኤፍዬ እሁንስ ደስ አለህ? " አለችኝ። አቅፋኝ እየተኛች። በኔና በቃልዬ መካከል ያለውን የሀሳብ ልዩነት ሳስበው ዘገነነኝ። እኔ ሌላ ነገር ልቀሰቅስ ደስታችንን ላደፈርስ ያልተናገረችውን ተናገረች ብዬ ላስደግማት ስጋጋጥ እሷ ግን እዚህ ሀረር ከመጣን ጀምሮ ስናወራ ስንቃለድ ከነበርንበት ርዕስ ሳትወጣ እዛው የፍቅር ወግ ላይ ነበረች። እንኳንም ለነገር ቸኩዬ እንዲህ ስትይ ሰማሁ አላልኳት እያልኩ ከጎኗ ጋደም አልኩ።
ምን ብዬ እንደማመልጥ ግራ ገብቶኝ በዝምታ ቆየሁና መንተዕፍረቴን " አይ አመመኝ በቃህ ያልሽኝ መስሎኝ ነበር ለዛ ነው እሺ ቃልዬ" ስላት።
"እስካሁን እዛው ላይ ነህ እንዴ በቃ እርሳው እንተኛ እቀፈኝ"አለችኝ አቅፊያት ተኛሁ። አይነጋ የለ ነጋ ። አይደርስ የለ ወደ ድሬ የምንሄድበት ሰአት ደርሶ ተነሳን።
ተሳፍረን ትንሽ እንደሄድን
"ኡፍፍፍ ምናለበት ባትሄጂ በቃ አሁን ሄደንም አብረን አንድ ቤት ውስጥ የምንገባ ቢሆን ቃልዬ" አልኩና የልቤን መሻት ተነፈስኩላት። ጣቶቼን በጣቶቿ መሀል እያፍተለተለች
"እኔም እንደዛ መሆን ቢችል ደስ ይለኝ ነበር ፣ አሁን ባይሆንም ሁሉም ነገር በግዜው ይሆናል፣ ሂወት እኛ በፈለግነው ልክ ቀላል አትሆንም ያንን አውቀን መቅደም ያለበትን ማስቀደም ግድ ነው አደል ኤፍዬ?"
"አዎ ልክ ነሽ " አልኳት ። ቃልዬን ማስጨነቅም መጨቅጨቅም አልፈልግም። የሀረርን ደስ የሚል ቆይታ ልበርዘው አልፈልግምና እሷን ልክ ነሽ ብዬ ፋይሉን ዘጋሁና በውስጤ ከፍቼው ከራሴ ጋር መጨቃጨቄን ቀጠልኩ
መቅደም ያለበትን ማስቀደም ስትል ምን ልትለኝ ፈልጋ ይሆን? ለቃልዬ ከፍቅር በፊት መቅደም ያለበት ምን ይሆን?
ቃልዬ ከፍቅር እና በፍቅር ተሳስሮ አብሮ ከመኖር በፊት እንዲሟላ የምትፈልገው የህይወት ጣጣ ምን ይሆን?
እሱማ ስንት ጣጣ አለ። ይህቺ አለም ጣጣዋ መች ያልቅና ?። እኔ ከቃልዬ ጋር ብኖር የሚርበኝ ሁላ አይመስለኝም።
ቢሆንም መምስል እና መሆን እንደሚለያይ ማመን ግድ ነው። የማይርበኝ ቢመስለኝም ሊርበኝ ይችላል። ነገሩ ከሆድ ውጪ ስንት ጣጣ አለ ። ለሆድማ የባጃጇ ገቢ መች ያንሰናል። ግን ብዙ ነገር አለ በትንሹ ቃልዬም ትምህርቷን መጨረስ እኔም አሁን ካለሁበት የተሻለ ደረጃ ላይ መድረስ ግድ ይላል።
አይ በኔ በኩል እንኳን ችግር የለም ከቃልዬ ጋር ሆኜ ለመስራት ለመለወጥ ለማደግ ምን ይከለክለኛል ? ምንም ። ቢሆንም የቃልዬን እቅድ እና ፍላጎትም ማክበር አለብኝ።
ማን ያውቃል ልክ ስድስት ወር ሙሉ ተገናኝተን እና ተጨዋውተን ስንለያይ በዚህ ሁኔታ እስከመቼ ነው የምንቀጥለው ለምንድን ነው ? የግኑኝነታችን ሁኔቴ ወደ ሌላ ደረጃ ማደግ የለበትም እንዴ? ብዬ ሳልጫናት፣ ሳልጨቀጭቃት፣ እሷ በፈለገችና በፈቀደች ሰአት ይህንን ጣፋጭ የሀረር ቃይታችንን እንዳመቻቸችው ሁሉ የኔን የአሁን ፍላጎት ተቀብላ አብረን መኖር እንድንጀምር መወሷንን ታበስረኝ ይሆናል።
እያልኩ በሀሰብ ማእበል ስወዘወዝ "ኤፊዬ" የሚለው የቃልዬ ጥሪ አባነነኝ።
"ወዬ ቃል"
"ምን እያሰብክ ነው ረጅም መንገድ ዝም ያለከው? ዘጋኸኝ እኮ"
"ምንም ቃልዬ ብቻ እንደትናንት ማታው አይነት ስሜት እየተሰማኝ ነው"ትናንት ማታ ብዙ ስሜቶች አስተናግደናል የተኛው ነው አሁን የተሰማህ?"
"ሚኒባስ ውስጥ ከገባን ቡሀላ ድሬ እንደደረስን አንቺም ወደግቢ እኔም ወደቤት እንደምንሄድና እንደምንለያይ ሳስበው የተሰማኝ ውረድ ይዛሀት ውረድ የሚል ስሜት"
"ካካካካ በቃ አሁንም እንውረድ "
'የት እዚህ ሀሮማያ ደርሰናል እኮ"
"እህህህህ አንተ የምሬን መሰለህ እንዴ ?"
"የምርሽን ቢሆን ደስ ይለኛል በቃ ሀረር እንመለስና አያቴ ቤት የተከራዩትን ሰዎች አስወጥተን እንኑር""ሂድ ወደዛ"
"የትም አልሄድም ቃልዬ ካንቺ የሚለየኝ "
"እንዳጨርሰው ኤፊ እንደዚህ አይነት ንግግር ይረብሸኛል"
"እሺ አልጨርሰውም" ብያት ዝም አልኩ ከንቺ የሚለየኝ ሞት ብቻ ነው ልላት ነበር እውነትም የሚረብሽ ነገር አለው አልኩ ለራሴ ።
.
.
ከ 150 ላይክ ቡኋላ ክፍል 37 ይለቀቃል🌹
https://vm.tiktok.com/ZMhV8Ma3n/