ውዴ! ባንተ ያምራል😍
ስንቶች በማስመሰል ህይወቴነሽ ሲሉ፣
በፍቅር ስም ብለው በሀሰት ሲምሉ።
ከፊልም ከልቦለድ ከግጥም መድብሉ፣
በተዋሱት ቃላት እየሸነገሉ፣
ፍቅርን ቢናዘዙም ቃላት አሰማምረው፣
ያ'ንተ ሁለት ፊደል ትርጉሙ ረቂቅ ነው።
ውዴ....!
በዚች ቃል ስትጠራኝ ልቤን ሞላው ሀሴት፣
እኔ እስከሚመስለኝ ባለም ላይ ያለው ሴት።
እናም ዛሬም ተነስ ላዳምጥህ ምከረኝ፣
ያኔ ያልሰማውህ ዛሬ ላይ ፀፀተኝ።
ተይ ብለኸኝ ነበር....!
ፈጣሪን ማማረር ማጉረምረም ይቅርብሽ
የመከራ ሸክም ጠፍሮ እንዳይጭንሽ።
ያኔ ባልሰማህም ዛሬ እሰማሀለው፣
ተነስ ውዴ በለኝ የሚያምረው ባንተ ነው።
🦋🙏ከወደዱት ሼር🙏🦋
✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
✨ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!✨
●●✨@yegna_pp ✨●●
✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
ስንቶች በማስመሰል ህይወቴነሽ ሲሉ፣
በፍቅር ስም ብለው በሀሰት ሲምሉ።
ከፊልም ከልቦለድ ከግጥም መድብሉ፣
በተዋሱት ቃላት እየሸነገሉ፣
ፍቅርን ቢናዘዙም ቃላት አሰማምረው፣
ያ'ንተ ሁለት ፊደል ትርጉሙ ረቂቅ ነው።
ውዴ....!
በዚች ቃል ስትጠራኝ ልቤን ሞላው ሀሴት፣
እኔ እስከሚመስለኝ ባለም ላይ ያለው ሴት።
እናም ዛሬም ተነስ ላዳምጥህ ምከረኝ፣
ያኔ ያልሰማውህ ዛሬ ላይ ፀፀተኝ።
ተይ ብለኸኝ ነበር....!
ፈጣሪን ማማረር ማጉረምረም ይቅርብሽ
የመከራ ሸክም ጠፍሮ እንዳይጭንሽ።
ያኔ ባልሰማህም ዛሬ እሰማሀለው፣
ተነስ ውዴ በለኝ የሚያምረው ባንተ ነው።
🦋🙏ከወደዱት ሼር🙏🦋
✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
✨ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!✨
●●✨@yegna_pp ✨●●
✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯