The Home of all የሁሉም ቤት


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Познавательное


Well come to the home of all in this channel all things about human being life post every day
* Motivate for free
* learn for free
* earn more for free
Buy ads: https://telega.io/c/+LiBy-b_3bjIyMjk0
══════❁✿❁═════════

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Статистика
Фильтр публикаций


አማክሩኝ ቤተሰቦቼ

ስሜ F ይባላል በጣም የምወዳት ፍቅረኛ አለችኝ ወደ 5 ወር አብረን ቆይተናል ከምላችሁ በላይ ነው በጣም ነው የምወዳት የማፈቅራት የተዋወቅነው ቴሌግራም ላይ ነው 3 ግዜ በአካል ተገናኝተናል እሷ የዩኒቨርስቲው ተማሪ ናት እኔ ደሞ ዩኒቨርሲቲ ጨርሼ አሁን ላይ የምኖረው የምሰራውም በቤተቦቼ ድርጅት ነው።
ምን መሰላችሁ ቤተሰቦቼ ፍቅረኛዬን ሁሌም እኔ ነኝ አስታውሼ የምደውለው ጠዋት ጠዋት text የማደርግላት እኔ ነኝ።
እሷ ከስንት አንዴ ነው ጥዋት ደና አደርክ ብላ text የምታደርግልኝ አንዳንዴ ስደውልላት አታነሳም ምነው ስላት ክላስ ነበርኩ ለዛ ነው ሁሌም የምትለኝ ነገር ነው።
ፍቅር በአንድ በኩል ሲሆን ይከብዳል ሁሌም እኔ ነኝ ወሬ ማስጀምረው የተለያዩ ሃሳቦችን እየመጣሁ እንወያያለን ግን ለሷ ያለኝ ፍቅር እየቀነሰ እየመጣ ነው በዚህ ሁኔታ ደሞ ይዘልቃል ብየ ማሰብ እየከበደኝ እየመጣ ነው።
አታፈቅረኝም ብየ እንዳላስብ ደግሞ ስለ ወደፊቱ ሂወታችን ስለምንወልዳቸው ልጆች ታወራኛለች ብቻ ከኔ ጋር ሁና ወደፊት የምታሳልፋቸውን ግዚያት እየናፈቃት እንደሆነ ትነግረኛለች።
ግን እኔ እዚህ ግራ ገባኝ ልለያት አስብና ሁለት ቀን ወይንም ሶስት ቀን ሳልደውል text ሳላደርግ ከቆየሁ ምነው ጠፋህ ምን አጥፍቼ ነው ምን አደረኩ ካጠፋሁ ይቅርታ ብላ ደሞ ምንም ባላጠፋች ነገር ይቅርታ ስጠይቀኝ ፍቅሬ ይጨምራል አንቺ ምንም አላደርግሽም ስራ ተበላሽቶብኝ ነው ብየ አስተባብላለሁ ምን እንደማደርግ ነው ግራ የገባኝ እባካችሁን እርዱኝ🙏🙏🙏🙏🙏

የሚቀርብ ታሪክ ካላችሁ በ
@MKFREZO መላክ ትችላላችሁ


​​«እውነተኛ ታሪክ»
ነገሩ የተከሰተው በሆላንድ መዲና አመስተርዳም ነው፡፡ ባልና ሚስት ከነ ሁለት
ልጆቻቻው በሚኖሩበት መኖርያ ቤት በር ላይ ሳይክል አስረው ያስቀምጣሉ፡፡
ጥዋት ሲነሱ ግን ሳይክላቸው ከቦታዋ አልነበረችም ተሰርቃለች፡፡ ይህ ክስተት
ከሳይክሎች ብዛት አንፃር ሲታይ ሆላንድ ላይ የተለመደ ስለሆነ ከምንም ኣልቆጠሩት፡፡
ከሁለት ቀን በኃላ ቤተሰብ ጥዋት ሲነሳ ሳይክሏ ከቦታዋ ተቀምጣለች እግሯ ላይ
ደሞ ኣበባ እና ደብዳቤ እንዲሁም 4 ቲኬት ነበራት፡፡ አባት ደብዳቤውን አነበበው
በመጀመርያ ይቅርታ እጠይቃለሁ? እኔ ሌባ ሁኜ ኣይደለም፡፡ አስቸኳይ ጉዳይ
ገጥሞኝ አማራጭ ስላጣሁ ሳይክሏን ወስጄ ነበር፡፡ ለዚህም የምስጋናየ
መግለጫ ይሆን ዘንድ እነዚህ ማራኪ አበባዎች አበርክቼላችዋለሁ፡፡ ለውለታችሁ
ደሞ ቅዳሜ እዚሁ አቅራቢያችሁ ባለው ሲኒማ ቤ አዲስ ለሚመረቀው ፊልም
መግቢያ ይሆናችሁ ዘንድ 4 ቲኬት ገዝቼላችዋለሁ፡፡
ማይክል እና ቤተሰብ ተሳስቀው ዝም አሉ..... ቅዳሜ ደረሰና ቤተሰብ የጓጉለትን ፊልም ለማየት ሄዱ፡፡
በልባቸው አመስግነው ወደ ቤት ሲመለሱ..... ቤታቸው በሙሉ ተዘርፎ
ጠበቃቸው:: 😊😊

        ስንተማመን በመጠኑ 😋😋


Репост из: Airdrop Avenue
19

እንኳን ለ ቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ❤️


------ዊሊያም ሼክስፔር------
☞ "ሲዖል ባዶ ነው፡፡ ምክንያቱም ሁሉም ዲያብሎሶች ያሉት እዚህ ምድር ላይ ነው፡፡"
☞ "ከክፋት ስትርቅ ሰላምህን ታበዛለህ፤ ቅንና መልካም ስትሆን ደግሞ ከጭንቀትና ከጸጸት ትድናለህ።"
☞ "ለማንኛውም ሠው ጆሮህን ስጥ፤ ድምፅህን ግን ቀንስ፤ ሁሉንም ውደድ፤ ጥቂቶቹን እመን፤ ማንንም ግን አትበድል፡፡"
☞ "የውሸት ጓደኛና ጥላ ሁለቱም አንድ ናቸዉ። ሁለቱም የሚቆዩት ፀሐይ እስካለች ድረስ ነው።"
☞ "ጨውን ሺ ጊዜ ስኳር ብትለው ስሙን እንጂ ጣዕሙን መቀየር አይችልም።"
☞ "የቀንን ውበት አይቶ ለማድነቅ የግድ ጨለማን መጠበቅ ያስፈልጋል።"
☞ "መልካም ስም ለሰው ልጅ የመንፈስ ቀንዲል ናት።"
☞ "ማንም
ሰው ህይወት ስህተት ወይም ትክክል መሆኑን የሚያውቀው ሲፈተን ነው።"


ፈጥረኸኝ_እያለህ

☀️ፈጥረኸኝ እያለ አሟልተህ በጤና
ማመስገን የማልችል ደካማ ነኝና
ለስጋዬ ማሰብ አድርጎኛል መና
ቪላ አልሰጠህኝ እንዲሁም መኪና
አልማዝ ወርቅም የለኝ እያለኝ ግን ጤና
እያልኩኝ ሳማርር አልገባኝምና
ለዚህ ለብልጭልጭ ለብስባሽ ገላ
ዛሬን አምሮ ታይቶ ነገን ለሚገማ
ሁሉስ መች አወቀው ነገ እንደሚቀማ
አምላክ ግን ሲጠራን ወርቄን ማቄን የለ
አልማዙም መኪናው ሁሉም የኛ አይደለ
ባንዲት አቡጀዲ ከነ ሀጢያታችን ከጉድጓድ አይደለ ??
ታድያ ምን አለበት ተመስገን እያልን
ከተሰጠን በልተን ካለንም ተቃምሰን
ይችን ብርቅርቅ አለም ወደ ኃላ ትተን
የሰይጣንን ሥራ ለሰይጣኑ ሰጥተን
የኛ የሆነውን አመስግነን ይዘን
ተመስገን ተመስገን በቃሉም ተገዝተን
እንኑር በፍቅር ባንድነት ተስማምተን🙏
🙏


ዛሬ ከ ፍቅረኛየ ጋ ተጣላን የተጠላንበት reason እነግራቸዋለሁ ማነው ጥፋተኛ እናንተ ንገሩኝ

እሷ -ኢህአዴግ ሲገባ ታዝዬ ነበር አለች 

 እኔ -ሰክረሽ  ነዋ አልኳት

እሷ- ጥላኝ ሄደች 😥


በሚያስገርም ሁኔታ 393 comment ተደርጎ ነበር ነገር ግን ውድድር ማንም የሸነፈ የለም ሁሉም like አለው።

Like በማድረግ ተወዳዳሪ የሌለው Future እና Dagi ናቸው🤣🤣

ሌላ ግዜ ጥያቄና መልስ ይኖረናል።


አረ እየተሳሰባቹሁ family ምንድነው እንደዚህ መጨካከን😂


Comment ላይ ምንም like ላላገኙ ለ ሁለት ሰዎች የ50 ብር ካርድ አላችሁ።

ማሳሰቢያ ‼️‼️
ውድድሩ እስከ ምሽቱ 5 ሰዓት ብቻ ነው የሚቆየው።
መልካም እድል 🤝🤝🫡

956 0 2 400 8

ከጎደለን ይልቅ የተሰጠን ይበልጣል !!
====================


ይህ ሰው ፖል ሪቻርድ አሌክሳንደር ይባላል። የተወለደው በ1946 ሲሆን በ6 አመቱ በፖሊዮ በሽታ ይያዛል። እንደ ፈረንሳዮች ከ 1952 ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በ "ብረት ሳንባ" ማሽን ውስጥ ይኖራል።

ከአንገቱ የላይኛው ክፍል በስተቀር መላ ሰውነቱ ፓራላይዝድ ነዉ። በምስሉ ላይ የምትመለከቱት የመተንፈሻ ማሽን ውስጥ ከገባ ዛሬ 71 አመት ሆኖታል። በዚህ ማሽን ምክንያት ነው በሕይወት ያለው። ከዚያ ለደቂቃ ከወጣ መተንፈስ ስለማይችል በህይወት አይቆይም። የሚያስገርመዉ ግን የህግ ትምህርትን ከታወቀ ዩንቨርስቲ ተመርቆ በህግ ሙያ ያስተምራል ።

አንዳንድ ጊዜ የጤንነታችንን እና የሰላማችንን  ዋጋ አንረዳዉም። እጅ እግር እያለን በሚረባዉ እና በማይረባዉ ነገር እናማርራለን። ይህ ሰዉ ግን ሁሌም በህይወት በመኖሩ ያመሰግናል ።

ከጎደለን ይልቅ የተሰጠን ይበልጣል እና ሁሌም በህይወት በመኖራችን እናመስግን።


Advertising

ሽሻይ ሞባይል ሽያጭ
ማንኛውም ስልክ ይዘዙን ያሉበት ቦታ ድረስ እናመጣለን
ስ.ቁጥር 0956322300
Telegram @Shushay9h


🙏


መብራት ልከፍል ሔጄ
:
:
:
መብራት እስኪመጣ ጠብቅ አሉኝ 😭


በሰላሳ ምናምን ዓመቱ ቤት ውስጥ በስራ ሰዓት ተኝቶ
:
"ስራ ስራ ልፋ ልፋ ጥረህ ግረህ ብላ" ሚለውን ሙዚቃ ያዳምጣል🙊🙉🙈


#ልጅ: አባዬ ጓደኛዬ እኮ አንድ ቀኝ እጅ ብቻ ነው ያለው

#አባት: ሲያሳዝን አንደኛው ተቆርጦ ነው?

#ልጅ: አይ አንዱ ግራ እጅ ነው😜😜😜


ከሴት ጋ ስትሆን ከሚመጣ የኔ ቢጤ በላይ ምቀኛ የለም
:
:

አምስት ብር አገኛለው ብዬ ኪሴ ስገባ 50 ብር በታች የለም በሼም 50 ብር ሰጥቼ ፀፀቱ ሊገለኝ ነው


ኖርዌይ ዉስጥ ያሉ እስር ቤቶች ለየት ይላሉ ። ለሁሉም እስረኞች የተሟላና ዘናጭ ክፍል ነዉ የሚሰጣቸዉ። እስረኞች ግቢያቸዉ ዉስጥ ካሉት ትልልቅ ሱቆች የፈለጉትን ልብስ ገዝተዉ የመልበስ መብት አላቸዉ ።

የእስር ቤቱ ግቢ ዉስጥ ትልልቅ ሲኒማዎች ፣ ሬስቶራንቶች ፣ ጂም ፣ ፈረስ መጋለቢያ ፣ የእግር ኳስ ፣ መረብ ኳስ የተለያዩ የስፖርት ሜዳዎች ፣ ቤተክርስቲያኖች ፣ ትምህርት ቤቶችና ብዙ ነገሮችን የተሟሉለት ስለሆኘ እስረኞች በየወሩ ከመንግስት በሚሰጣቸዉ ብር የፈለጉበት ቦታ ገብተዉ ጊዜ ማሳለፍና መዝናናት ይችላሉ።

ምግባቸዉንም ጊቢ ዉስጥ ካሉት ትልቅ ሱፐር ማርኬቶች ገዛዝተዉ ክፍላቸዉ ዉስጥ ማብሰል ይችላሉ


1567 በአለም ባለረጅም ፂም ባለቤት የነበረው  Hans Steininger ከእሳት  አደጋ ማምለጥ ሲሮጥ ፂሙ አደናቅፎት ወድቆ ነበር የሞተው፡፡


እንደ አውሮፓዊያን ዘመን ቀመር በ 193ዐ ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደውን የዓለም ዋንጫ የመሃል ዳኛ በመሆን የመሩት ሰውዬ እኝህ ናቸው።

ዳኛው ሰርግ ቤት የተጠሩ ይመስል ከረባት ሁሉ አልቀራቸውም ነበር።


ሙሉ ክቡን ፒዛ ብቻዋን ፀጥ አድርጋ ጨረሰችና አፏን በናፕኪን እየጠረገች ''አብሮ ለመኖር ፍቅር ብቻ በቂ ነው!!'' አላለችም😳😜
  
    #እየሔድሽ_እንዳይመሽብሽ 🚶‍♀🚶‍♀

Показано 20 последних публикаций.