ኦገኖቼ ባልተቤትየውኮ እንፋታ አለኝ 😭😭😭😭
እርግጥ እሱ "ወጋሁ!! እኔ አልወጣኝም!" ብሏል.... በቀጥታ አላለም እንጂ ብሏል.... 'ከኔጋ መዋል ከጀመረ ተንከሲስነት እየለመደ መጥቶ እንጂ ድሮ የዋህ ሰው ነበር' ብያችሁ የለ??? ይኸው የቀረው ቅኔ: አሽሙር: ሽሙጥ .... ነበር... እሱንም ጀምሯል::
ምንድነው የሆነው መሰላችሁ??? ባለትዳሮች ታውቁታላችሁ!! ልክ ተጋብተን መኖር ከጀመርን ቀን ጀምሮ ሳንማከር (አንዳንዱ ተነጋግሮ) መኝታችንን የባል ቦታና የሚስት ቦታ ብለን ርስታችንን እንመዳደብ የለ??? ... ( በድሮ ጊዜ እንደአሁኑ አልጋችንን እንደቀይወጥ ክፍሉ መሃል ላይ ጉሊጥ የምናደርገውን ስታይል ሳናመጣ በፊት አልጋው ግድግዳ ታክኮ በሚቆምበት ወቅት ... የሚስት ቦታ በግድግዳ በኩል... የባል ቦታ ወደበር ወይም ከግድግዳ ተቃራኒ ነበር የሚሆነው አሉ!! ምክንያቱም ድንገት የሆነ ነገር ቢፈጠር ለምሳሌ ሌባ ቢገባ... አባወራው መዥረጥ ብሎ የአባወራ ምከታ ተግባሩን እንዲከውን ነው አሉ:: እንደ ዘንድሮ በእግሩ ጥፍር አልጋው ላይ ቆሞ ሚስቱን እየተጣራ "አይጧ መጣችልሽ!!" የሚል ባል አልነበረም አሉ..... አሉ ነው እንግዲህ 🤪🤪🤪)
እናላችሁማ ይኸው 5 ዓመት በትዳር ስንቆይ የመጀመሪያ ቀን ያስከበርናትን የአልጋ ርስት ተደፋፍረን የማናውቅ ሰዎች ... ትናንት ማታ እሱ በጊዜ ተኝቶ እኔ አርፍጄ ልተኛ ስሄድ እቦታዬ ላይ ለሽ ብሎ አላገኘሁትም??? ....... መቼም አንዳንዴ አንዳንዴም ቢሆን ጥሩ ሰው እሆን የለ??? ድምቅ አድርጎ ከተኛበት አልቀሰቅሰውም ብዬ በሱ ቦታ ተኛሁ!!! .... ገና ገልጬ ስገባ ቅዝቃዜው ተው.... (መኝታ ቤት ውስጥ heater አንለኩስም!! የዚህ ሀገር ሰዎች ማታ ንፁህ አየር እየተነፈስን ነው ማደር ያለብን ብለው ጭራሽ መስኮት የሚከፍቱት ታሪክ አላቸው!!.... ማለቴ በ -10 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ነውኮ የምላችሁ🙄🙄 እህህህ ምን እያልኳችሁ ነውና?? .... እኔ ለራሴ እየበረደኝ እንቅልፍ ሊወስደኝ ይቅር እና ማሰብም ነው የማልችለው.... እሱ ደሞ ጭራሽ እንደሞላለት ሰው በቦክሰር ሁላ ነው የሚተኛው... ይሄን ለማስታረቅ የእኔ ቦታ ላይ ከአንሶላዬ ስር የምትነጠፍ እንደአንሶላ የሳሳች ማሞቂያ ገዝተን ... ተከባብረንና ... አንቺ ትብሽ አንተ ተባብለን ነበር የኖርነው .... )
እና ይሄ ከፍተኛ ሴራ አይደለም??? ቦታዬን ከነሙቀቱ ቀምቶኝ ለሽ ብሎ ደሞ አተኛኘቱ እንቅልፍ እንቢ ላለው ሰው ደም ሲያፈላ 🤷🏽♀️🤷🏽♀️🤷🏽♀️🤷🏽♀️ ታግዬ ታግዬ ሽልብ ቢያደርገኝ ሰው ቤት እንግድነት ሄጄ ለመጀመሪያ ጊዜ የማድር አይነት ስሜት እየተሰማኝ ብንን ማለት .... መባነኑ ሲቀር ... ከትንሽዬዋ የጉንዳን መንጋ ጀምሮ ያላባረረኝ እንስሳ የለም በህልሜ .... ቀጭኔዋ ፀጉሬ የደረቀ ሳር መስሏት ነው መሰለኝ ፀጉሬን ይዛ አንጠልጥላኝ መሬት እርቆኝ "ወይ መሬት ያለ ሰው" ስል ነቃሁ!!!..... ለሽ እሱ ምናለበት.... ሙሉ ለሊትማ ደግ አልሆንም ብዬ ቀስቅሼው
"ምን እንደፈለግክ በግልፅ ተናገር!! ከዚህ ሁሉ ለምን እንፋታ አትልም!!" አልኩት....
"(አበስኩ ገበርኩ አይነት ነገር በኖርዌጅኛ አጉተምትሞ ሲያበቃ አይኑን ሳይገልጥ ) ማታኮ ቶሎ የምትተኚ መስሎኝ ላቅፍሽ ስጠብቅሽ እንቅልፍ ጥሎኝ ነው!! ( እንጣዬ ነው ያለው ... ጨዋ ሳደርገው ነው) " ብሎ ደገመውኮ ..... ደገመው ስላችሁ🙄🙄🙄🙄 ለሽ!!!! .... እሺ እኔ በዚህ ለሊት ንጋት 12 ሰዓት ለእናንተ ላቃጥር ነጠላዬን አቀብሉኝ ማለት ነበረብኝ??? እሱኮ እንደተኛ ነው በርስቴ..... እና ይሄ እንፋታ ከማለት ቢበዛ እንጂ ያንሳል???? 🤣🤣🤣🤣
ውብ ቀን ውብኛ አዋዋል ዋሉልኝማ❤️❤️❤️❤️