✞ ጋሜል- የመዝሙር ግጥሞች ✞


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Религия


✟ የኦርቶዶክሳውያን መንፈሳዊ የምስጋና ቤት ✟
ቤተ ክርስቲያንን አንተውም ከቶ
የሰጠንን አምላክ በደሙ መስርቶ
የሰጠንን ጌታ በመስቀሉ ሞቶ
የአምላካችንን ቤት አንተውም ከቶ
ለማስታወቂያ ሥራ➠ @Naolviva
💿 የተዋሕዶ የመዝሙር ግጥሞች 💿
   ✍ / ትምህርቶችን ለማግኘት ✍
👇👇👇
https://t.me/maedot_ze_orthodox

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Религия
Статистика
Фильтр публикаций


በአጭር ጊዜ ህይወታቹን የሚቀይሩ የተረጋገጡ የ Draw ትኬቶች መሸጫ ቻናል እንጠቁማቹ ተጠቀሙ 👇

betting ሁሌ ማሸነፍ ከፈለጋቹ ይሄንን ቻናል ተቀላቀሉ 👇


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ከ15 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል


የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!

10+10×0+10=???


✞ የኢዮብ መልሱ ✞

እንደምነህ ቢሉት ዘመዶች ከድተውት
ሚስቱ ትታው ሄዳ ልጆች ሞተውበት
ዓይኖቹ በምሬት እንባ አላፈሰሱ
እግዚአብሔር ይመስገን [፪] ነበር የኢዮብ መልሱ

በሕይወት ገጥሞት የበረታ ፅልመት
በአንድ ቀን ሲነጠቅ ልጆችና ንብረት
አካሉ በቁስል ተይዞ በጠና
ኢዮብ እንዴት ቻለ ለአምላኩ ምስጋና

        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►

በሰጠበት መንደር ሲቆም ለልመና
ሚስቱ ሙት ስትለው ጌታን እርገም እና
የስንፍናን ነገር አይሰማም ጆሮዬ
ይክሰኛል እርሱ ይችላል ጌታዬ

        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►

ቅን ነገር መናገር ለአፌ ከቸገረኝ
አምላኬ እንዳያዝን ምነው ዝም በአልኩኝ
ልሳኔ እንዳይጠራ ሞት እና መከራ
ለምስጋና ቆሜ ነገን ዛሬ ልሥራ

        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►

እግዚአብሔር ይመስገን ቢጎድልም ቢሞላም
ለዓይኔ ሽፋሽፍት እንቅልፍ እንኳን ባጣም
ብዙ እንደነበረው ትናንትና ደጄ
ክፉውንም ደግሞ ይቀበላል እጄ

                 መዝሙር|
    ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


የካቲት ❷❸
🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁
እንኳን ለኢትዮጵያ ገበዝ (ጠባቂ) ለአድዋው አርበኛ፣ ለፍጡነ ረድኤት፣ ለገባሬ ተአምር ሊቀ ሰማዕታት ለቅዱስ ጊዮርጊስ በ1888ዓ.ም በአድዋ ጦርነት ንጉሠ ነገሥትን ምኒልክና ሰራዊቱ ለረዳበት፤ ኢትዮጵያ በሮማውያንን (ጣልያንን) ድል ለተቀዳጀችበት ለ129 (ለአንድ መቶ ሃያ ዘጠነኛው ) ለአድዋ በዓል በሰላም አደረሰን።

🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁


Репост из: ✞ ጋሜል- የመዝሙር ግጥሞች ✞
​​✞ ​​ዐቢይ ጾም ✞

በሊቀ ጉባኤ ቀለመወርቅ ውብነህ
    የካቲት ፴ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም

         ክፍል አንድ [፩]

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ
     አሐዱ አምላክ አሜን

ጾም ማለት መተው መከልከል ማለት ነው፡፡

ጾም በእግዚአብሐር የተቀደሰ ተግባር ስለኾነ ወደ ቅድስና ጎዳና የሚመራ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያናችንም ሥርዓት ሠርታ ጾምን ከአምላካችን ጋር ኅብረት እንዲኖረን፤ መንፈሳዊ ኃይል እንድናገኝ ታደርጋለች፡፡

በጾም ወራት ከመባልዕት መከልከል ብቻ ሳይኾን ዐይን ክፉ ከማየት፣ አንደበት ክፉ ከመናገር፣ ጆሮ ክፉ ከመስማት መቆጠብ እንደሚገባው በቅዱሳት መጻሕፍት ተጽፎአል፡፡ 

"ይጹም ዐይን ይጹም ልሳን እዝንኒ ይጹም እምሰሚዓ ኀሡም በተፋቅሮ" እንዲል ቅዱስ ያሬድ ጾመ ድጓ

በጾም ወራት ላምሮት፣ ለቅንጦት የሚበሉ ወይም ለመንፈሳዊ ኃይል ተቃራኒ የኾኑ ሥጋዊ ፍትወትን የሚያበረታቱ፣ ሥጋንና የሚያሰክሩ መጠጦችን ዳን.፲፥፪-፫

ቅቤና ወተትን ከመጠቀም መታቀብ እንደሚገባ ታዟል።መዝ.፻፰፥፳፬፣ ፩ቆሮ.፯፥፭፤ ፪ቆሮ.፮፥፮

በብሉይ ኪዳን ጾም ከፍተኛ ቦታ ነበረው፡፡ የብሉይ ኪዳን ነቢያት ከእግዚአብሔር በሚገናኙበት ወራት እህልና ውኃ በአፋቸው አይገባም ነበር።ዘፀ.፴፬፥፳፰

አስቴር አስቀድማ ሦስት ቀን ጾማ ጸልያ በእስራኤል ላይ የመጣውን መቅሠፍት እንዲመለስ አድርጋለች። አስቴር ፬፥፲፭-፲፮

በዘመኑ በኃጢአት ብዛት የታዘዘው የእግዚአብሔር መዓት የሚመለሰውም ሕዝቡ በጾም ሲለምኑትና ሲማልዱት ነበር። ዮናስ ፪፥፯-፲

በሐዲስ ኪዳንም ጾም ሰው ሠራሽ ሕግ ሳይኾን ራሱ ክርስቶስ የሠራው ሕግ ነው ማቴ.፬፥፪፤ ሉቃ.፬፥፪

ቅዱሳን ሐዋርያትም በየጊዜው ከመንፈስ ቅዱስ ትእዛዝ የሚቀበሉት በጾም በጸሎት ላይ እንዳሉ ነበር።ሐዋ፲፫፥፪

ለስብከተ ወንጌል የሚያገለግሉ ዲያቆናትና ቀሳውስትም የሚሾሙት በጾምና በጸሎት ነው።ሐዋ.፲፫፥፫፤ ፲፬፥፳፫

እንደ ቆርነሌዎስ ያሉ ምእመናን ያላሰቡትን ክብር ያዩና ያገኙ የነበረውም በጾምና በጸሎት ፈጣሪያቸውን በመማጸን ነው። ሐዋ ፲፥፴

ዐቢይ ጾም ጌታችን ከተጠመቀ በኋላ ዐርባ ቀን የጾመው፤ እኛም እንድንጾማቸው በቤተ ክርስቲያናችን ከታዘዝናቸው ሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት አንዱ ነው፡፡

ምእመናን ጌታችን ያደረገውን ምሳሌ ተከትለን ጾሙን በየዓመቱ እንጾመዋለን፡፡

ዐቢይ ጾም ስምንት ሳምንታት (፶፭ ቀኖች) አሉት፡፡ በውስጡ ስምንት ቅዳሜዎች፣ ሰባት እሑዶች ይገኛሉ፡፡ ይኸውም ዐሥራ አምስት ቀን ማለት ነው፡፡ እነዚህ ቀናት ከጥሉላት እንጂ ከእኽል ውኃ ስለማይጦሙ የጦሙ ወራት ዐርባ ቀን ብቻ ይኾናል፡፡

ጾሙ በተለያዩ ስሞች ይጠራል፤

አንደኛ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተጠመቀ በኋላ የጾመው በመኾኑ፣እንደዚሁም "ዐቢይ እግዚአብሔር ወዐቢይ ኀይሉ ዐቢይ እግዚአብሔር ወብዙኅ አኰቴቱ"መዝ.፵፯፥፩፤ መዝ.፻፵፮፥፭ የተባለ ጌታችን የጾመው ጾም ስለኾነ"ዐቢይ ጾም"ይባላል፡፡

ሁለተኛ "ሁዳዴ ጾም"ይባላል፡፡ ይህም የመንግሥት እርሻ ወይም ማንኛውም የሕዝብ ብዛት ያለበት ሥራ ሁዳድ ስለሚባል ሲኾን፣ ዐቢይ ጾምም ከአጽዋማት ዅሉ ብዙ ቀናት ስለሚጾምና ኃያሉ አምላካችን ስለጾመው ነው
አሞ ፯፥፩

ሦስተኛ "በአተ ጾም"ይባላል፡፡ የጾም መግቢያ፣ መባቻ ማለት ነው፡፡

አራተኛ "ጾመ ዐርባ"ይባላል፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው ፵ ቀን ስለኾነ  ማቴ.፬፥፩

አምስተኛ "ጾመ ኢየሱስ"ይባላል፡፡ ጌታችን እርሱ ጾሞ፣ ጹሙ ብሎ ስላዘዘን፡፡

ስድስተኛ "ጾመ ሙሴ"ይባላል፡፡ ቅዱስ ያሬድ በዘወረደ ጾመ   ድጓው "ከመዝ ይቤ ሙሴ እስመ ለዓለም ሙሴኒ ይቤ በውስተ ኦሪት" እያለ ስለዘመረ /የሰኞ ዕዝል/፡፡

ከዐቢይ ጾም ሳምንታት መካከል የመጀመሪያው ሳምንት"ዘወረደ (ዘመነ አዳም)ይባላል፡፡

ዘወረደ ማለት ከላይ የመጣ፣ የወረደ ማለት ነው፡፡ ይህም አምላካችን አዳምንና ልጆቹን ከሞት ለማዳን ሲል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው መኾኑንና የፈጸመውን የማዳን ሥራ ያመለክታል፡፡ 

"ከሰማይ ከወረደው በቀር ወደሰማይ የወጣ የለም" ካለው ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ቃል በመነሣት ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ዘወረደ እምላዕሉ አይሁድ ሰቀሉ ወሚመ ኢያእመሩ እግዚአ ኵሉ ዘየሐዩ በቃሉ" በማለት በጾመ ድጓው መጀመሪያ ላይ ይህን ዕለት ገልጾታል፡፡
ትርጕሙም "አዳምን ለማዳን ከሰማይ የወረደውን አምላክ አይሁድ ሰቀሉት፤ የሰማይ ሥልጣን ያለው የዅሉ ጌታ እንደኾነም ምንም አላወቁም" ማለት ነው፡፡

ይህም ድርሰት በቤተ ክርስቲያናችን የጾም መጀመሪያ የኾነው ዕለተ ሰንበት ዋዜማ፣ መግቢያ (መሐትው) ኾኖ ከዋዜማ በፊት ምንጊዜም በየዓመቱ ይቆማል፤ ይዘመራል፤ ይመሰገናል፡፡

በዚህ ሳምንት በተለይም እሑድና ሰኞ የሚነገሩት ውዳሴያት ከመጻሕፍተ ኦሪትና ነቢያት የተወሰዱ ናቸው፡፡ ሁለተኛም ሳምንቱ "ሙሴኒ"በመባል ይታወቃል፡፡

እግዚአብሔር አምላክ አዳምን ለማዳን ከሰማይ መውረዱንና በመስቀል መሰቀሉን ስለሚያወሳ ነው፡፡

በተጨማሪም ይህ የመጀመሪያው ሳምንት"ጾመ ሕርቃል"ይባላል፡፡ ሕርቃል (ኤራቅሊየስ) የቤዛንታይን ንጉሥ ነበር፡፡ ይህ ሳምንት በስሙ የተጠራበት ምክንያት...

    ክፍል ሁለት ይቀጥላል....

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


✞ እንዲህ በአራት ነጥብ ✞

እንዲህ በአራት ነጥብ ሊዘጋ ምዕራፉ
እግዚአብሔር ሊያሸንፍ የእርሱ ሆኖ ሰልፉ
መልካም ለመናገር አፉ ባይታደል
ይኼን እስኪያይ ጠላት ምን አለ ዝም ቢል[፪]


           አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
መልካሙን ደብቆ ክፉን እያሳየ
ይለኝ ነበር ጠላት እግዚአብሔር ዘገየ
ግን ሁሉን በጊዜው ውብ አግድጎ ሲሰራ
አፍሯል ለዘላላም ደንቆት የእርሱ ሥራ[፪]

           አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
በቃ ልጅ የለህም አትወልድም ሣራ
ላይሰማህ እግዚአብሔር ጮኸ ብትጣራ
እያለ ጠላቴ መስሎት ያሸነፈ
ይስሐቅ ተወለደ ያ ቀንም አለፈ [፪]

           አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ፍፃሜዬን ሳያይ ገና ከጅምሩ
ጠላት በእሱ ግምት ብዙ መናገሩ
አስብሎታል ቴቄል ተቀይሮ ስሙ
የዘገየ መስሎ ጌታ በመቅደሙ [፪]

           አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ድንጋይ ያሸከመን ውሃ ተሸከመ
ለእኛ ቀን ወጣልን ለእርሱ ግን ጨለመ
ገዳይ ቢዘገይም ሟች በመገስገሱ
ፈረሰኛው ሞተ እስከነ ፈረሱ [፪]

           አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ቢመስለንም ሌሊቱ ፍፁም የማይነጋ
ተቆልፎ የሚቀር በሩ እንደተዘጋ
እርሱን ተስፋ አድርገው ባመንክበት ፅና
ቀን አለው እግዚአብሔር ያደርግሃል ቀና [፪]

               መዝሙር|
ሊቀ መዘምራን ዲ/ን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


​​​​VALENTINE'S DAY
ሼር በማድረግ ትውልዱን ከጥፋት እንታደግ❗

አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለኛ ቤዛ ሆኖ በፍቅሩ የገዛን እጃችንን ለጣኦት እንድንሰጥ አይደለም ብዙ ዋጋ የተከፈለብን እስከ ሞት እንከን በሌለው ፍቅሩ የወደደን መንግስቱን እንድንወርስ እንጂ እንድንጠፋ አይደለም።

የቫላንታይ ቀን ድብቅ እውነታ ስንቶቻችን እናውቃለን? ይህን የቫላታይን ቀን (የፍቅረኛሞች ቀን) ብለን ስንቶቻችን ነን የምናከብረው ? ወይስ ሰው ስላከበረውና የስልጣኔ መገለጫ መስሎን ነው የምናከብረው ???

ከክርስቶስ ልደት በፊት በባቢሎን ፤ቤልዘቡል ፤በግሪክ ፓን ፤ ሮማ ሞሎቅ ፤ በላቲን ሳተርን ለሚባሉት ሰይጣኖች ያላገቡ ሴቶች ደም የሚፈስላቸው ቀይ ልብስ የሚለበስላቸው ጣኦቶች ናቸው ይህ ዛሬ ቫለንታይን ተብሎ የመጣው ማለት ነው።

የሚገርመው ደሞ ሴቶቹ በዚህ ቀን ለመደፈር ብለው እራቁታቸውን ጫካ መግባታቸው ነው በዚህ ቀን የተደፈረች እና ደሟን ያፈሰሰች ሴትም ሆነ ወንድ በጣኦቱ የተመረጠ እና የተባረከ ነው መባሉ ነው ይበልጥ ነገሩን ሰይጣናዊ የሚያደርገው።

ግሪክ አርኬዲያ ብለው በሚጠሩት አስቀያሚ ትርጉም ባለው ተራራቸው ላይ በዚህ ቀን ላይ ነው ያላገቡ ወንድ እና ሴቶቻቸውን ጣኦቱ ስር ወሲብ በመፈጸም ገላቸውን አርክሰው ለሰይጣን የሚገብሩት።

ይህ የሰይጣን ቀን ነው ክርስትና ይሄን ትከለክላለች ታወግዛለች። (ሁሉም ቀን የእግዚአብሔር ነው ግብሩ ነው የሰይጣን የሚያደርገው)

ኢየሱስ ክርስቶስ ከመውለዱ ከዘመናት በፊት አረማውያን ሮማውያኖች Feb 14 ማታ እና ለ Feb 15 ንጋት አጥቢያ የተኩላ አዱኚ ለሚሉት ሉፐርካልያ (luperkalya ) ጣኦት የሚዘጋች ክብረ በአል ነው፡፡

ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ክርስትና ተቀብሎ እውነተኛ የጽድቅ ሃይማኖት መሆኑን በማውጁ ማንኛውም የጣኦት አምልኮ እንዲቀር ቢያስጠነቅቅም የተውሰኑ የሮማውያን ሰዎች ግን በአሉን ማክበር አልተውም።

እንዴት ይህ አረማዊ ባህል ቫለንታይን የሚል ሰያሜ ተሰጠው? ቫለንታይን የሚል ስም በሮማውያን ዘንድ የተለመደ ስያሜ ነው፡፡ ቫለንታይን የጥንታዊ ታዋቂው ሉፐርኩስ ጣኦት ነው።

ሉፐርኩስ በግሪካዎያን ፓን (pan) ተብሎ ሚጠራው ከወገቡ በታች በግ አናቱ ላይ ቀንድ ያለው ጣኦት ነው። በጥንታውያን አይሁድ ደግሞ ይህ ፓን ባል (baal) በሚል ስያሜ ይታወቃል።

ጥንታውያን ሮማውያን ከባቢሎናውያን የቀዱት አረማዊ የልብ (heart) ምልክት ይጠቁማሉ፡፡ በባቢሎናውያን ባል (bal) ልብ የሚል ፍች ነው ያለው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ይህ አረማዊ የልብ ምልክት ለቫለንታይን ቀን (የፍቅረኛሞች ቀን) የምንለው መግለጫነት እንጠቀምበታለን። ባል የባቢሎናውያን ጣኦት ነበር።

በዚህ የኃጢአት ቀን በትንቹ ይህ ይሆናል

1. በዚህ ቀን February 14 በብዙ የሚቆጠሩ እህቶቻችንን ክብረ ንጽህናቸውን (ድንግልናቸውን) ያጣሉ❗

2. በርካታ ወጣቶች በስካር ምክንያት በሚያሽከረክሩት መኪና ህይወታቸውን እና አካላቸውን ያጣሉ❗

3. በአለማችን ላይ በከፍተኛ ሁኔታ የአልኮል መጠጥ ሽያጭ የሚከናወንበት ቀን ነው በአጠቃላይ የዝሙት እና ስካር መንፈስ የሚነግስበት በከፍተኛ ሁኔታ ሰይጣን በደም የሚረካበት ቀን ነው።

Valentine day ማለት ሰይጣን በጥልቅ እና ረቂቅ ሃሳብ ብዙዎችን የሚያጠምድበት ቀን ነው አስተውሉ ሰይጣን ከ7ሺህ አመት በላይ የክፋት ልምድ አለው።

እንግዲህ ምርጫው የአንተ/ቺ ነው :- የእግዚአብሔር ወይም የሰይጣን ልጅ መሆን???

" ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል፤ አንተም እውቀትን ጠልተሃልና እኔ ካህን እንዳትሆነኝ እጠላሃለሁ፤ የአምላክህንም ሕግ ረስተሃልና እኔ ደግሞ ልጆችህን እረሳለሁ። "
(ትንቢተ ሆሴዕ 4 : 6)

እግዚአብሔር አምላክ ማስተዋሉን ያድለን።
   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
    @yemezmur_gexem
   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


​​በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ አራት [፬]

ይህም ዮናስን ከቶ ደስ አላሰኘውም፥ እርሱም ተቈጣ።

ወደ እግዚአብሔርም ጸለየና። አቤቱ፥ እለምንሃለሁ፤ በአገሬ ሳለሁ የተናገርሁት ይህ አልነበረምን? አንተ ቸርና ይቅር ባይ፥ ታጋሽም፥ ምሕረትህም የበዛ፥ ከክፉው ነገርም የተነሣ የምትጸጸት አምላክ እንደ ሆንህ አውቄ ነበርና ስለዚህ ወደ ተርሴስ ለመኰብለል ፈጥኜ ነበር።

አሁንም፥ አቤቱ፥ ከሕይወት ሞት ይሻለኛልና እባክህ፥ ነፍሴን ከእኔ ውሰድ አለው።
እግዚአብሔርም። በውኑ ትቈጣ ዘንድ ይገባሃልን? አለ።

ዮናስም ከከተማይቱ ወጣ፥ ከከተማይቱም በስተ ምሥራቅ በኩል ተቀመጠ፤ ከተማይቱንም የሚያገኛትን እስኪያይ ድረስ በዚያ ለራሱ ዳስ ሠርቶ ከጥላው በታች ተቀመጠ።

እግዚአብሔር አምላክም ቅል አዘጋጀ፥ ከጭንቀቱም ታድነው ዘንድ በራሱ ላይ ጥላ እንድትሆን በዮናስ ላይ ከፍ ከፍ አደረጋት፤ ዮናስም ስለ ቅሊቱ እጅግ ደስ አለው።

በነጋው ግን ወገግ ባለ ጊዜ እግዚአብሔር ትልን አዘጋጀ፥ እርስዋም ቅሊቱን እስክትደርቅ ድረስ መታቻት።

ፀሐይም በወጣች ጊዜ እግዚአብሔር ትኩስ የምሥራቅ ነፋስ አዘጋጀ ዮናስ እስኪዝል ድረስም ፀሐይ ራሱን መታው፤ ለራሱም ሞትን ፈለገና። ከሕይወት ሞት ይሻለኛል አለ።

እግዚአብሔርም ዮናስን። በውኑ ስለዚች ቅል ትቈጣ ዘንድ ይገባሃልን? አለው። እርሱም። እስከ ሞት ድረስ እቈጣ ዘንድ ይገባኛል አለ።

እግዚአብሔርም። አንተ ትበቅል ዘንድ ላልደከምህባት ላላሳደግሃትም፥ በአንድ ሌሊት ለበቀለች፥ በአንድ ሌሊትም ለደረቀችው ቅል አዝነሃል።

እኔስ ቀኛቸውንና ግራቸውን የማይለዩ ከመቶ ሀያ ሺህ የሚበልጡ ሰዎችና ብዙ እንስሶች ላሉባት ለታላቂቱ ከተማ ለነነዌ አላዝንምን? አለው።

    ትንቢተ ዮናስ ተፈጸመ

     ወስብሐት ለአምላክነ

   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
    @yemezmur_gexem
   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


​​በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

       ትንቢተ ዮናስ
          ምዕራፍ ሁለት [፪]


እግዚአብሔርም ዮናስን የሚውጥ ታላቅ ዓሣ አሰናዳ፤ ዮናስም ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በዓሣው ሆድ ውስጥ ነበረ።

ዮናስም በዓሣው ሆድ ውስጥ ሆኖ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፥ እንዲህም አለ።

በመከራዬ ሳለሁ ወደ አምላኬ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፥ እርሱም ሰማኝ፤ በሲኦልም ሆድ ውስጥ ሆኜ ጮኽሁ፥ ቃሌንም አዳመጥህ።
ወደ ጥልቁ ወደ ባሕሩ ውስጥ ጣልኸኝ፥ ፈሳሾችም በዙሪያዬ ነበሩ፤ ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ በላዬ አለፉ።

እኔም። ከዓይንህ ፊት ተጣልሁ፤ ነገር ግን ወደ ቅዱስ መቅደስህ ደግሞ እመለከታለሁ አልሁ።
ውኆችም እስከ ነፍሴ ድረስ ከበቡኝ፤ ጥልቁ ባሕር በዙሪያዬ ነበረ፤ የባሕሩ ሣር በራሴ ተጠምጥሞ ነበር።

ወደ ተራሮች መሠረት ወረድሁ፤ በምድርና በመወርወሪያዎችዋ ለዘላለም ተዘጋሁ፤ አንተ ግን፥ አቤቱ አምላኬ፥ ሕይወቴን ከጕድጓዱ አወጣህ።

ነፍሴ በዛለችብኝ ጊዜ እግዚአብሔርን አሰብሁት፤ ጸሎቴም ወደ አንተ ወደ ቅዱስ መቅደስህ ገባች።
ከንቱነትንና ሐሰትን የሚጠብቁ ምሕረታቸውን ትተዋል።


እኔ ግን በምስጋና ቃል እሠዋልሃለሁ፤ የተሳልሁትንም እከፍላለሁ። ደኅንነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።

እግዚአብሔርም ዓሣውን አዘዘው፥ እርሱም ዮናስን በየብስ ላይ ተፋው።

       ምዕራፍ ሦስት [፫]

የእግዚአብሔርም ቃል ሁለተኛ ወደ ዮናስ እንዲህ ሲል መጣ።

ተነሥተህ ወደዚያች ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፥ የምነግርህንም ስብከት ስበክላት አለው።
ዮናስም ተነሥቶ እንደ እግዚአብሔር ቃል ወደ ነነዌ ሄደ፤ ነነዌም የሦስት ቀን መንገድ ያህል እጅግ ታላቅ ከተማ ነበረች።

ዮናስም የአንድ ቀን መንገድ ያህል ወደ ከተማይቱ ውስጥ ሊገባ ጀመረ፤ ጮኾም። በሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች አለ።

የነነዌም ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ፤ ለጾም አዋጅ ነገሩ፥ ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ።
ወሬውም ወደ ነነዌ ንጉሥ ደረሰ፤ እርሱም ከዙፋኑ ተነሥቶ መጐናጸፊያውን አወለቀ ማቅም ለበሰ፥ በአመድም ላይ ተቀመጠ።

አዋጅም አስነገረ፥ በነነዌም ውስጥ የንጉሡንና የመኳንንቱን ትእዛዝ አሳወጀ፥ እንዲህም አለ። ሰዎችና እንስሶች ላሞችና በጎች አንዳችን አይቅመሱ፤ አይሰማሩም ውኃንም አይጠጡ፤

ሰዎችና እንስሶችም በማቅ ይከደኑ፥ ወደ እግዚአብሔርም በብርቱ ይጩኹ፤ ሰዎችም ሁሉ ከክፉ መንገዳቸውና በእጃቸው ካለው ግፍ ይመለሱ።
እኛ እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ተመልሶ ይጸጸት እንደ ሆነ፥ ከጽኑ ቍጣውም ይመለስ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?

እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደተመለሱ ሥራቸውን አየ፤ እግዚአብሔርም ያደርግባቸው ዘንድ በተናገረው ክፉ ነገር ተጸጽቶ አላደረገውም።

     ምዕራፍ አራት ይቆየን....

   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
    @yemezmur_gexem
   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


​​በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

        ትንቢተ ዮናስ
         ምዕራፍ አንድ [፩]

የእግዚአብሔርም ቃል ወደ አማቴ ልጅ ወደ ዮናስ እንዲህ ሲል መጣ ።
ተነሥተህ ወደዚያች ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፥ ክፉታቸውም ወደ ፊቴ ወጥቶአልና በእርስዋ ላይ ስበክ።

ዮናስ ግን ከእግዚአብሔር ፊት ወደ ተርሴስ ይኰበልል ዘንድ ተነሣ፤ ወደ ኢዮጴም ወረደ፥ ወደ ተርሴስም የምታልፍ መርከብ አገኘ፤ ከእግዚአብሔርም ፊት ኰብልሎ ከእነርሱ ጋር ወደ ተርሴስ ይሄድ ዘንድ ዋጋ ሰጥቶ ወደ እርስዋ ገባ።

እግዚአብሔርም በባሕሩ ላይ ታላቅ ነፋስን አመጣ፥ በባሕርም ላይ ታላቅ ማዕበል ሆነ፥ መርከቢቱም ልትሰበር ቀረበች።
መርከበኞቹም ፈሩ፥ እያንዳንዱም ወደ አምላኩ ጮኸ፤ መርከቢቱም እንድትቀልልላቸው በውስጥዋ የነበረውን ዕቃ ወደ ባሕር ጣሉት፤ ዮናስ ግን ወደ መርከቡ ውስጠኛው ክፍል ወርዶ ነበር፥ በከባድ እንቅልፍም ተኝቶ ነበር።

የመርከቡም አለቃ ወደ እርሱ ቀርቦ። ምነው ተኝተሃል? እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ያስበን እንደ ሆነ ተነሥተህ አምላክህን ጥራ አለው።

እርስ በእርሳቸውም። ይህ ክፉ ነገር በማን ምክንያት እንዳገኘን እናውቅ ዘንድ ኑ፥ ዕጣ እንጣጣል ተባባሉ። ዕጣም ተጣጣሉ፥ ዕጣውም በዮናስ ላይ ወደቀ።

የዚያን ጊዜም። ይህ ክፉ ነገር በማን ምክንያት እንዳገኘን እባክህ ንገረን፤ ሥራህ ምንድር ነው? ከወዴትስ መጣህ? አገርህስ ወዴት ነው? ወይስ ከማን ወገን ነህ? አሉት።

እርሱም። እኔ ዕብራዊ ነኝ፤ በሕሩንና የብሱን የፈጠረውን የሰማይን አምላክ እግዚአብሔርን እመልካለሁ አላቸው።

እነዚያም ሰዎች ከእግዚአብሔር ፊት እንደ ኰበለለ እርሱ ስለ ነገራቸው አውቀዋልና እጅግ ፈርተው። ይህ ያደረግኸው ምንድር ነው? አሉት።

ባሕሩንም ሞገዱ አጥብቆ ያናውጠው ነበርና። ባሕሩ ከእኛ ዘንድ ጸጥ እንዲል ምን እናድርግብህ? አሉት።

እርሱም። ይህ ታላቅ ማዕበል በእኔ ምክንያት እንዳገኛችሁ አውቃለሁና አንሥታችሁ ወደ ባሕር ጣሉኝ፥ ባሕሩም ጸጥ ይልላችኋል አላቸው።

ሰዎቹ ግን ወደ ምድሩ ሊመለሱ አጥብቀው ቀዘፉ፤ ዳሩ ግን ባሕሩ እጅግ አብዝቶ ይናወጥባቸው ነበርና አልቻሉም።

ስለዚህ ወደ እግዚአብሔር ጮኸው። አቤቱ፥ እንደ ወደድህ አድርገሃልና እንለምንሃለን፤ አቤቱ፥ ስለዚህ ሰው ነፍስ እንዳንጠፋ ንጹሕም ደም በእኛ ላይ እንዳታደርግ እንለምንሃለን አሉ።

ዮናስንም ወስደው ወደ ባሕሩ ጣሉት፤ ባሕሩም ከመናወጡ ጸጥ አለ።

ሰዎችም እግዚአብሔርን እጅግ ፈሩ፥ ለእግዚአብሔርም መሥዋዕትን አቀረቡ፥ ስእለትንም ተሳሉ።

     ምዕራፍ ሁለት ይቆየን....

   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
    @yemezmur_gexem
   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


Репост из: ✞ ጋሜል- የመዝሙር ግጥሞች ✞
​​ጾመ ነነዌ

        ክፍል አንድ [፩]

             ከፈለገ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ

የነነዌ ጾም ከሰባቱ የቤተክርስቲያን አጽዋማት አንዱና የዐቢይ ጾም ማዘጋጃ ደወል ነው፡፡ ይህ የነነዌ ሰዎች የንስሐ ታሪክ በቤተክርስቲያናችን በጣም ታላቅ ዋጋ ያለውና የራሱ መዝሙር የሚዘመርለት፣ ቅዳሴ የሚቀደስበት ታላቅ መታሰቢያ ያለው ታሪክ ነው፡፡

ራሱ ጌታችንም የነዌ ሰዎችን የንስሐ ታሪክ በመጥቀስ አይሁድን ገስጾበታል፤ በፍርድ ቀንም በዚያ ትውልድ ዘንድ እንደሚፈርዱበት ተናግሯል፡፡

ይህም የሆነበት የነነዌ ሰዎች ደስ የሚያሰኝ የንስሐ ታሪክ ስላላቸው ነው፡፡ በዚህ ጽሑፍ ይህን አስደሳች የንስሐ ታሪክ በጾመ ነነዌ ከሚነበቡ የቅዳሴ ምንባባት አንጻር ለመመርመር እንሞከራለን፡፡

ኃጢአት ከእግዚአብሔር መለየት እንደሆን ሁሉ ንስሐ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር መመለስ ነው፡፡

በዚህ ከእግዚአብሔር ሊለዩ የሚችሉ ብዙ ፈተናዎች ባለቡት ዓለም እስካለን ድረስ ሕይወታችን ሁሉ የንስሐ ጊዜ ነው፡፡

ይሁን እንጂ ከሁሉም ጊዜ በተለየ ወደ እግዚአብሔር የምንመለስባቸው የጾም ወቅቶች ሲሆኑ ከእነዚህም ታላቁና ዋነኛው ዐቢይ ጾም ነው፡፡

ቅድስት ቤተክርስቲያናችን በዐቢይ ጾም ከእያንዳንዱ ምእመን ልቦና የንስሐ ፍሬን ትፈልጋለች፤ ያለትንሣኤ ልቦና /ንስሐ/ የክርስቶስን ትንሣኤ በእውነትና በደስታ ማክበር አይቻልምና፡፡

ለመሆኑ ከንስሐ የሚያሰናክሉን ነገሮች ምን ምን ናቸው? የነነዌ ሰዎች ታሪክ ስለዚህ ምን ያስተምረናል?

.ቅንጦትን መውደድ

ምንም እንኳን በደፈናው ገንዘብ የኃጢአት ምንጭ ነው ባንልም እንደ ወንጌል ትእዛዝ በክርስቲያናዊ መንገድ ካልተያዘ ግን እግዚአብሔርን ሊያስረሳና የኃጢአት ማስፈጸሚያና ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡

ብዙ ጊዜም ገንዘብና ባለጸግነት ከእግዚአብሔር በመለየታችን ያጣነውን ሰላምና ደስታ ለማግኘት ተስፋ የምንጥልበት ጣኦት ሆኖ ሊቀየር ይችላል፡፡

በሀብታችን በምናገኘው ጊዜያዊ ደስታና ሰላም ዘላለማዊውንና ፍጹምን የእግዚአብሔር ስጦታ መፈለግ፣ ወደ እግዚአብሔር መመለስን መናፈቅ ልናቆም እንችላለን፡፡

በዚህ መልኩ ብልጽግና ከንስሐ የሚያሰናክል ወጥመድ ይሆናል ማለት ነው፡፡

እግዚአብሔር ሀብት እንኳ ቢሰጠን ለተቸገረ በመመጽወት፣ ልጆቻችን በክርስቲያናዊ መንገድ በማሳደግ፣ የቤተክርስቲያንን አገልግሎት በማፋጠን የእውነተኛ ደስታና የጽድቅ መንገድ እንድናደርገው እንጂ እግዚአብሔርን የተጠማች ነፍሳችንን ጥሪዋን በማደናቀፍና ጩኸቷን በማፈን በሥጋ ድሎት ውስጥ የምንደበቅበት መሣሪያ እንድናደረገው አይደለም፡፡ ለ"ታላቂቷ ከተማ" ነነዌም የጥፋት መንገድ የሆናት በብልጽግናዋና በታላቅነቷ እግዚአብሔርን ረስታ የኃጢአት ከተማ መሆኗ ነው፡፡

በነቢዩ በዮናስ ታሪክ ውስጥ ገንዘብ ለዮናስ ከእግዚአብሔር የመከለያ መሣሪያ ሲሆን እናገኘዋልን፡፡"... ከእግዚአብሔርም ፊት ኮብልሎ ከእነርሱ ጋር ወደ ተርሴስ ይሔድ ዘንድ ዋጋ ሰጥቶ ወደ እርሷ /ወደ መርከቧ/ ገባ"እንዲል ዮና፩፥፫

በዚህ ሰዓት ለዮናስ ገንዘብ ባይኖረው ይሻል ነበር፡፡ እኛም ቢሆን ከንስሐ የሚመልስ፣ ለኃጢአት መሣሪያ የሚሆን ሀብት ከሚኖረን በድኅነት ብንኖር ይሻለናል፡፡

ምንም እንኳ በቤተክርስቲያናችን ትውፊት ዐቢይ ጾም አብዝተን የምንጸልይበት፣ በጾም በስግደትና በምጽዋት ልናሳልፈው የሚገባ ወቅት ቢሆንም ፤ አሁን አሁን ግን ገንዘብ ማግበስበሻ እየሆነ እንደሆነ እናያለን፡፡

በመሠረቱ በጾም ወቅት ከሆዳችን የምንቀንሰው ገንዘብ እንድናጠራቅመው ሳይሆን እንድንመጸወተው የሚገባ ነው፡፡

ለማጠራቀምማ የማያምኑ ሰዎችስ ምግብ ይቀንሱ የለ? ለዚህ ነው በነነዌ ጾም በመጀመሪያው ቀን /ሰኞ/ የሚነበበው የቅዱስ ያዕቆብ መልእክት "አሁንም እናንተ ባለ ጠጎች ስለሚደርስባችሁ ጭንቅ ዋይ ዋይ እያላችሁ አልቅሱ፡፡ ሀብታችሁ ተበላሽቷል፣ ልብሳችሁም በብል ተበልቷ፡፡ ወርቃችሁም ብራችሁም ዝጓል፤ ዝገቱም ምስክር ይሆንባችኋል፤ ሥጋችሁንም እንደ እሳት ይበላል፡፡ ለኋለኛው ቀን መዝገብን አከማችታችኋል፡፡ እነሆ እርሻሁን ያጨዱት የሠራተኞች ደመወዝ በእናንተ ተቀምቶ ይጮኻል፣የአጫጆችም ድምፅ ወደ ጌታ ጸባዖት ጆሮ ገብቷል፡፡ በምድር ላይ ተቀማጥላችኋል፤ በሴሰኝነትም ኖራችኋል፤ ለእርድ ቀን እንደሚወፍር ልባችሁን አወፍራችኋል፡፡"
ያዕ ፭፥፩
በማለት አስፈሪ ተግሳጽ የሚያስተላልፈው፡፡

ስለዚህ በዐቢይ ጾም አብዝተን የምንመጸውትበት፣ ከእግዚአብሔር የሆነውን ስጦታ የምንፈልግበት፣ የንስሐ ጊዜ ሊሆን ይገባል፡፡

.ለኃጢአት ሌላ ተጠያቂ መፈለግ

       ክፍል ሁለት ይቀጥላል...

ከ "የመዝሙር ግጥሞች" የተወሰደ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


✞ የእኔ መሓሪ ✞

የእኔ መሓሪ ሁሉን መርሻዬ
ሁሉን መርሻዬ
እንደ ሕልም አልፏል ትናንትናዬ
በአንተ ጌታዬ (፪)


    አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
አዳፋው ልብሴ ከነፃ
ከእዳ ከፈታኝ በነፃ
የጽድቁ ባሪያው ሆኛለው
ሳገለግለው ኖራለው
የእንባ ዘለላን ያቀፈው
አይኔም እልልታ ተረፈው
ደልዳዩ መዳፍ ደርሶሎኝ
ተራራው ሜዳ ሆነልኝ
    አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
አይኖቼን ከጉድ ጋርዶልኝ
ክንዶቼን በእጁ ይዞልኝ
ከእግሬ በታች ነው ወጀቡ
አሁን ታይቶኛል ወደቡ
ሰላም ይነፍሳል ዙሪያዬ
እረፍት ሆኖልኝ ጌታዬ
የባረከኝን ባርኬ
ተለወጠልኝ ታሪኬ
    አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ብርሃንህ ገፏል ድቅድቁን
በልቤ ተክሏል ሰንደቁን
ተቆጣጥሮኛል መውደዱ
መንገዴ ሆኗል መንገዱ
ያበቃው ነገር ቀጥሏል
ጭንቄ በሞቱ ተሰቅሏል
የኢየሱስ ሆኜ ምን አጣሁ
ሁሉን በስሙ ተወጣሁ
    አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
   እንደ እኔ ማንን ታግሷል
   ይቅርታ ፍቅሩን አልብሷል
   ማይገባኝን አድርጎ
    ያሳለፈልኝ ሸሽጎ
መልካም ነው ለኔስ መልካም
ፀጋው ያገዘኝ ስደክም
ሞትኩኝ ስል ምሕረት ደርቦ
አቆመኝ በሕይወት አስዉቦ

             መዝሙር|
   ዘማሪ ገ/አምላክህ ደሳለኝ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE


https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


✞ ወረት የሌለው ✞

ወረት የሌለው መውደድ
ወረት የሌለው ፍቅር
አንተ ጋር ብቻ ነው
ያለው እግዚአብሔር
(፪)


           አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ዘመን የማይዘው ጊዜ የማይገድበው
የአንተ ፍቅር ብቻ ቀን በቀን አዲስ ነው
ከዴማስ ጋር ስሄድ ትቼው የአንተን መንገድ
ከቶ መች ቀነሰ ለእኔ ያለህ መውደድ
           አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
በአመጽ ብጠፋም ከመንጋህ መካከል
ይመሻል ይነጋል እኔን ስትከተል
እንደወጣ ይቅር ብለህ መቼ ተውከኝ
ሴኬም ድረስ ወርደህ ልጅህን ፈለከኝ
           አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
በዝናዬም ዘመን ባለጸጋ እያለሁ
ቤቴ በወዳጆች ቀን በቀን ሙሉ ነው
እንደ ጤዛ ሲረግፍ ሐብትና ንብረቴ
ያለ አንተ ማን ነበር በፈርሰው ቤቴ
           አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
የታመንኩባቸው ወዳጆች ሲከዱኝ
ሕመሜ ስር ሆነው ደጋግመው ሲወጉኝ
ለአንተ ጊዜ ባጣም ለእኔ ጊዜ አለህ
ገፋህ ክፉ ቀኔን ከእኔ ጋራ አብረህ

             መዝሙር|
ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE


https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


"በፈጣሪ ልጄን አድኑልኝ" አባት

ይህ ቆንጅዬ ህፃን አሚር የሱፍ  ይባላል! በተወለደ 4ኛ ወሩ ህመም ሲያሰቃየውና እንቅልፍ ሲከለክለው እናትና አባት ወደ ጥቁርአንበሳ ሆስፒታል ይዘውት ይሄዳሉ!
ህፃን አሚር አንድ ወር አልጋ ይዞ ክትትል ካደረገ በኋላ ዶክተሮች "የልብ ክፍተት  ችግር አለበት፣ አስቸኳይ ቀዶ ጥገና ያስፈልገዋል"ተባሉ!

ልጁን ለማሳከም የተጠየቁት 1500000 ብር ነው ከአቅም በላይ ስለሆነ ልጃቸውን ለማዳን እናንተን እየተማፀኑ ነው😭 እባካችሁ #እንድረስላቸው🙏 እናግዛቸው🙏
 "ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"

አካውንት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000304310937-ዩሱፍ ሀምደለ (አባት)
#ስልክ 0705740135

☞አድራሻ ካራ ቆሬ ወታደር ሰፈር
☞ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል


✞ የተሰጠህ ክብር ✞

የተሰጠህ ክብር ግሩም ሐብተማርያም አቡነ
ተማፅነናል በአንተ በእውነት ሐብተማርያም አቡነ
የወንጌል መምህር ጻድቅ አባት ነህ
[፪]


በገድል ብትጸና            ሐብተማርያም
በጾም በጸሎት             ሐብተማርያም
ክብርን ተጎናፀፍክ        ሐብተማርያም
እንደ መላእክት             ሐብተማርያም
ስምህን ስንጠራህ        ሐብተማርያም
በፍቅርህ ተጠምደን      ሐብተማርያም
ጻድቁ አባታችን             ሐብተማርያም
መጥተህ እኛን ባርከን   ሐብተማርያም

         አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ጽድቅ እኮ ነው ምርጫው - ሐብተማርያም
የ ሐብተማርያም              ሐብተማርያም
የፈጸመው ገድል              ሐብተማርያም
ያሳየው ጽናት                   ሐብተማርያም
ለአምላኩ ያለውን             ሐብተማርያም
እውነተኛ ፍቅር                 ሐብተማርያም
ገለጽከው በሕይወት         ሐብተማርያም
በታላቅ እምነት                 ሐብተማርያም

         አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ኢትዮጵያ እልል በይ        ሐብተማርያም
እጅግ ደስ ይበልሽ          ሐብተማርያም
የእግዚአብሔር አገልጋይ - ሐብተማርያም
ጻድቅ አባት አለሽ           ሐብተማርያም
በምልጃው የሚረዳሽ      ሐብተማርያም
በጸሎት ከልሎሽ            ሐብተማርያም
በችግርሽ ጊዜ               ሐብተማርያም
ፈጥኖ የሚያድንሽ          ሐብተማርያም

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE


https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


✞ በስባረ አፅሙ ✞

በስባረ አፅሙ በገድለ ድካሙ
በፀናበት በአስቦ ገዳሙ
ስድስት ክንፍ አገኘ
ተክለሃይማኖት ምድራዊ መልዐክ ተሰኘ (፪)

 
ትናገር ደብረ አስቦ የተጋደለባት
ተክልዬ በአንድ እግሩ ቆሞ የፀለየባት
በመላዕክት ከተማ ሕብረት የፈጠረ
ከካህናተ ሰማይ መንበሩን ያጠነ
 
         አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
 
ቅዳሴ ቀድሷል ሚካኤል ተራድቶት
ወንጌልን መስርቷል በፅላልሽ ዳሞት
ተክለሃይማኖት ጻድቁ አዲስ ሐዋርያ
ሞገሷ ነህ አንተ ለኢትዮጵያ
 
         አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
 
የመንፈስ ልጆችህ አእላፍ ሆነዋል
በፀሎትህ ታምነው ቤትህን ሞልተዋል
የላመ የጣመ መና በሌለበት
ዳቤው ንፍሮው ውኃው ሆኗቸዋል ውበት

    አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
 
እፁብ ነው ድንቅ ነው የተሰጠህ ፀጋ
ቋጠሮ ቢፈታ ከአንተ የተጠጋ
የጻድቅ ሰው ፀሎት ምልጃው ይፈውሳል
ተክልዬን ያመነ ኧረ ምን ይሆናል

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE


https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


✞ ቅዱስ ጊዮርጊስ አማለደን ✞

ቅዱስ ጊዮርጊስ አማለደን አማለደን
ከመድኃኔዓለም አስታረቀን
ማረን ይቅር አለን ማረን ይቅር አለን
አማኑኤል ታረቀን


ሹመት ለመፈለግ - - ቅዱስ ጊዮርጊስ
ነገሥታት ዘንድ ሄዶ - - ቅዱስ ጊዮርጊስ
ጣዖት ሲያመልኩ አየ - - ቅዱስ ጊዮርጊስ
አምላኩ ተክዶ - - ቅዱስ ጊዮርጊስ
        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ክርስቲያን ነኝ የሚል - - ቅዱስ ጊዮርጊስ
በዓለም ሁሉ ጠፍቶ - - ቅዱስ ጊዮርጊስ
እኔ አምናለሁ አለ - - ቅዱስ ጊዮርጊስ
የአምላኩን ስም ጠርቶ - - ቅዱስ ጊዮርጊስ
        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
የዓለም ግሳንግሷ - - ቅዱስ ጊዮርጊስ
ጸባይዋ ሳይገዛህ - - ቅዱስ ጊዮርጊስ
ስለ ጌታ ፍቅር - - ቅዱስ ጊዮርጊስ
ከእናትህ ተለየህ - - ቅዱስ ጊዮርጊስ
        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
የመቅጫው መሳሪያ - - ቅዱስ ጊዮርጊስ
በዓይነት ተደቅኖ - - ቅዱስ ጊዮርጊስ
እኔ አልፈራም አለ - - ቅዱስ ጊዮርጊስ
በአምላኩ ተማምኖ - - ቅዱስ ጊዮርጊስ
        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ተፈጭቶ ተደቅቆ - - ቅዱስ ጊዮርጊስ
ደብረ ይድራስ ሳለ - - ቅዱስ ጊዮርጊስ
እጽዋቱ ሁሉ - - ቅዱስ ጊዮርጊስ
ጊዮርጊስ ጊዮርጊስ አለ - - ቅዱስ ጊዮርጊስ

           መልአከ ሰላም
  ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


✞ ተናገራ ✞

ተናገራ እዝራ ተናገራ ዳዊት ዘመራ(፪)

ተናገራ ዳዊት በመሠንቆ ዳዊት ዘመራ
ተናገራ እያጫወታት ዳዊት ዘመራ
    አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ተናገራ ሳታውቀው አለፈ ዳዊት ዘመራ
ተናገራ ያ መልአከ ሞት ዳዊት ዘመራ
    አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ተናገራ ውኆች ቀለም ሆነው ዳዊት ዘመራ
ተናገራ እንጨቶች ብእር ዳዊት ዘመራ
    አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ተናገራ ቢጽፉት አያልቅም ዳዊት ዘመራ
ተናገራ የማርያምን ክብር ዳዊት ዘመራ


✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


✞ ሞትሰ ✞

ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ይደሉ/፪/
ሞታ ለማርያም የሐፅብ ለኵሉ (፬) ኧኸ

ሞትማ ለሚሞት ሰው ይገባዋል (፪)
የማርያም ሞት ግን (፪) እጅግ
ያስደንቃል (፬) ኧኸ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE


https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


✞ ወልድኪ ይጼውአኪ ✞

ወልድኪ ይጼውአኪ (፪)
ውስተ ሕይወት ወመንግሥተ ክብር (፬)

ልጅሽ ይጠራሻል (፪)
ወደ ሕይወት እና ወደ ክብር መንግሥት(፬)


✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE


https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

Показано 20 последних публикаций.