➖ بسم الله الرحمن الرحيم 🖊 ➖
☘☘ ከግጥም ማህደር ☘☘
•┈┈•✿❁✿•┈┈•
🍀🍀 እውነተኛ ጀግና 🍀🍀
➖➖➖➖➖➖➖➖➖
እውነተኛ ጀግና - ምድር ላይ ነበረ
ለጌታው ሲዋደቅ - በትጋት የኖረ
ከወንጀል ማዕበል - ነፍሱን እየገታ
ህይወቱን ሲገፋት- ከፅኑዎች ተርታ
ነፍሲያው አረፈች- መበርታቱን አይታ
ማሸነፍ ሲሳናት - ወትውታ ወትውታ
እውነተኛ ታጋይ - ምድር ላይ ነበረ
ሸይጣን እንዳይጥለው - ሲታገል የኖረ
ከጥፋት ለመሸሽ - መፍትሄውን አውቆ
ህይወቱን ሲገፋት - እጅግ ተጠንቅቆ
ሸይጣን ተሸነፈ - ታጋዩን ሰልችቶ
አልሳካ ሲለው - ጎትጉቶ ጎትጉቶ
እውነተኛ ጠቢብ - ምድር ላይ ነበረ
በማስረጃ ጥበብ - ህይወቱን የኖረ
በምራቻ ጉዞ - በርትቶ ሲተጋ
ህይወቱን ሲገፋት - ጀሊልን ፍለጋ
ተደሰተ ጌታው - በዚህ ጠቢብ ኑሮ
ስኬትን ለገሰው - ጨምሮ ጨማምሮ
የሱው ተቃራኒ - እንዲህ ያልበረታ
በነፍሲያ ጥሪ - ልቡ ተወትውታ
ተጎትቶ ቀርቶ - በሸይጣኑ ገመድ
ተይዞ ታሰረ - ተገኝቶ ከወጥመድ
ከዚህ መጠበቂያው - መበርታት ነውና
ራሕማኑ ያድርገን - እውነተኛ ጀግና
🖌 ኢብኑ ሱልጣን አልኢትዮቢ
እርማትና ማስተካከያ
➡️️ ዓብዱረዛቅ አልሐበሺ
ግምገማ
➡️ ኢሻራ የሳንሱርና አስተያየት ክፍል
ሸዋል 22 - 1441
t.me/isharaChannel2
☘☘ ከግጥም ማህደር ☘☘
•┈┈•✿❁✿•┈┈•
🍀🍀 እውነተኛ ጀግና 🍀🍀
➖➖➖➖➖➖➖➖➖
እውነተኛ ጀግና - ምድር ላይ ነበረ
ለጌታው ሲዋደቅ - በትጋት የኖረ
ከወንጀል ማዕበል - ነፍሱን እየገታ
ህይወቱን ሲገፋት- ከፅኑዎች ተርታ
ነፍሲያው አረፈች- መበርታቱን አይታ
ማሸነፍ ሲሳናት - ወትውታ ወትውታ
እውነተኛ ታጋይ - ምድር ላይ ነበረ
ሸይጣን እንዳይጥለው - ሲታገል የኖረ
ከጥፋት ለመሸሽ - መፍትሄውን አውቆ
ህይወቱን ሲገፋት - እጅግ ተጠንቅቆ
ሸይጣን ተሸነፈ - ታጋዩን ሰልችቶ
አልሳካ ሲለው - ጎትጉቶ ጎትጉቶ
እውነተኛ ጠቢብ - ምድር ላይ ነበረ
በማስረጃ ጥበብ - ህይወቱን የኖረ
በምራቻ ጉዞ - በርትቶ ሲተጋ
ህይወቱን ሲገፋት - ጀሊልን ፍለጋ
ተደሰተ ጌታው - በዚህ ጠቢብ ኑሮ
ስኬትን ለገሰው - ጨምሮ ጨማምሮ
የሱው ተቃራኒ - እንዲህ ያልበረታ
በነፍሲያ ጥሪ - ልቡ ተወትውታ
ተጎትቶ ቀርቶ - በሸይጣኑ ገመድ
ተይዞ ታሰረ - ተገኝቶ ከወጥመድ
ከዚህ መጠበቂያው - መበርታት ነውና
ራሕማኑ ያድርገን - እውነተኛ ጀግና
🖌 ኢብኑ ሱልጣን አልኢትዮቢ
እርማትና ማስተካከያ
➡️️ ዓብዱረዛቅ አልሐበሺ
ግምገማ
➡️ ኢሻራ የሳንሱርና አስተያየት ክፍል
ሸዋል 22 - 1441
t.me/isharaChannel2