☀️ አላህ (ሱ·ወ) እስልምናን ለኛ እኛንም ለእስልምና በመምረጡ ፤ እሱ ዘንድ ብቸኛው እና ተቀባይነት ያለው ዲን በማድረጉ ምስጋና ይገባው ።
☀️ እስልምናን ለአለም በማድረስ ለተላኩት እና የነቢያቶች መደምደሚያ በሆኑት በ«ሙሀመድ» ላይም የአላህ ሰላም ይስፈን ።
☀️ የሰው ልጆች ከተፈጠሩበት እለት አንስቶ ዓለም እስከምትጠፋበት ቀን ድረስ ሰዎች እንዲጓዙበት ከፈጣሪያቸው የታዘዙበት እምነት * ኢስላም * ነው ።
☀️ ይህ ስርዓት ዱንያ ላይ ለሰዎች አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን በሙሉ ጠቅልሎ የያዘ ከመሆኑም በተጨማሪ፤ በቀጣዩም ዓለም ( በአኺራ) በምንም ሊተመን የማይችል ሽልማትና ደስታ የሚያስገኝ ነው ።
☀️ በተቃራኒው ይህንን ስርዓት ባልተቀበለና ባልተከተለ ላይ ደግሞ ማብቂያም ሆነ እረፍት በሌለው አሳማሚ ቅጣት ይስተናገዳል ።
☀️በሌላ አባባል በሁለመናቸው ሙስሊም ለሆኑ ‘ ጀነት’ ኢስላምን ላልተቀበሉ ደግሞ ‘ ጀሀነም ’ የተባለ ሀገርን ያዘጋጀ ስርዓት ነው ።
☀️ ማንኛውም ሰው "ሙስሊም " ነኝ በማለቱ ብቻ ወይም ደግሞ የሙስሊም ስም በመጠቀሙ ብቻ ‘ጀነትን’ ያገኛል ማለት አይደለም!!!
☀️ በመሆኑም የዱንያንም ሆነ የአኼራን ስኬት ለመቀዳጀት ኢስላም ያዘዘውን መታዘዝ ፣ የከለከለውን መከልከል የግድ ይላል ።
☀️ አላህ (ሱ· ወ) ለሰው ልጆች በየጊዜው #መፅሀፍትን በማውረድ ፣ ነቢያትን በመላክ፣ እነዚህንም ነብያት ትዕዛዛትንና ክልከላዎችን እንዲያስተምሩ በማድረግ በአጠቃላይ የሚድኑበትን መንገድ ያሳያቸዋል ።
☀️ለዚህ ኡመት ( ህዝብ) ደግሞ የቀደሙትን መፅሀፍቶች የሚሽር « ቁርአን» ፤ የነቢያቶች መቋጫ አድርጎ «ሙሀመድን» አለይሂ ሰላቱ ወሰላም ልኮልናል ።
☀️ አልሀምዱሊላህ ‼ ይህም ማለት የእስልምና ምንጮች « ቁርአን» እና « የታላቁ ነቢይ "ሱና"» ብቻ ናቸው ማለት ነው ።
☀️ ከነዚህ ሁለቱ ምንጮች እንደተገኘው እስልምና ከአምስት [ 5] ነገራቶች የተገነባ ነው ።
እነርሱም ፦
① ከአላህ በቀር በእውነት የሚገዙት አምላክ እንደሌለ ሙሀመድም ( አለይሂ ሰላቱ ወሰላም ) የአላህ ባርያ( ፍጡር): እና መልዕክተኛው መሆናቸውን መመስከር ፣
② “ሰላትን ” በተከታታይነት መስገድ ፣
③ "ዘካን" መስጠት ፣
④ " ረመዷንን ” መፆም እና
⑤ ለቻለ ሰው “ሀጅን” ማድረግ ናቸው ።
@yenebiyatwrs