የክረምት ዶፍ ዝናብ ገላሽን ካራሰው
ሽቅብ እወጣለሁ
ደመናን ላፈርሰው ።
ንፋስ በክንፎቹ ጉንጭሽን ቢዳብስ
ስታገል አድራለሁ አየር ሳበሰብስ
ደግሞ ይሄን እወቂ
ሆዴ እንደሚበላኝ ያለኔ ስትስቂ
እንቅልፍ እንደማጣ
በፀሐይ ስትፈኪ
ምራቄ እንደሚመር
በእግዜር ስትመኪ
እኔ ነኝ ጠባቂሽ
እኔ ነኝ ደስታሽ
እኔ ነኝ ፈገግታሽ
ሁሉንም የምሆን
እግዜር አላህ ሰማይ
ንፋስ ውሃ ድንጋይ
ያንቺ ብቻ አገልጋይ
ያንቺ ብቻ ታጋይ
መብረር ያሰኘሽ 'ለት ክንፋም ልሁን ልክነፍ
ውሃ ያሰኘሽ 'ለት ወንዝ ውቅያኖስ ልጥለፍ
ብቻ ደስታሽ ሁሉ በእኔ በኩል ይለፍ ።
ስቀና እንዲህ ነኝ !
#ዘሩባቤል
┄┅┅┄┅✶♥️✶┅┄┅┅┄
❤️❤️❤️ #Share ❤️❤️❤️
😘😍@Yenefekir😘😍
💝@Yenefekir💝
ሽቅብ እወጣለሁ
ደመናን ላፈርሰው ።
ንፋስ በክንፎቹ ጉንጭሽን ቢዳብስ
ስታገል አድራለሁ አየር ሳበሰብስ
ደግሞ ይሄን እወቂ
ሆዴ እንደሚበላኝ ያለኔ ስትስቂ
እንቅልፍ እንደማጣ
በፀሐይ ስትፈኪ
ምራቄ እንደሚመር
በእግዜር ስትመኪ
እኔ ነኝ ጠባቂሽ
እኔ ነኝ ደስታሽ
እኔ ነኝ ፈገግታሽ
ሁሉንም የምሆን
እግዜር አላህ ሰማይ
ንፋስ ውሃ ድንጋይ
ያንቺ ብቻ አገልጋይ
ያንቺ ብቻ ታጋይ
መብረር ያሰኘሽ 'ለት ክንፋም ልሁን ልክነፍ
ውሃ ያሰኘሽ 'ለት ወንዝ ውቅያኖስ ልጥለፍ
ብቻ ደስታሽ ሁሉ በእኔ በኩል ይለፍ ።
ስቀና እንዲህ ነኝ !
#ዘሩባቤል
┄┅┅┄┅✶♥️✶┅┄┅┅┄
❤️❤️❤️ #Share ❤️❤️❤️
😘😍@Yenefekir😘😍
💝@Yenefekir💝