━━━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━━━
አይ አንቺ....''ያምሃል!'' አልሽኝ አይደል
የማይሆን ወድጄ ለማይሆን ስጋደል
(ርዕሱ ነው)
ባይገርምሽ....
ላንቺ ሲሆን ጊዜ
መንገዱ በሙሉ ጨርቅን መሰለልኝ
ስንክል የሌለበት
ከደጃፍሽ ቆምኩኝ
"ወዬ" የሚልን ቃል ካንቺ ላልሰማበት
ኳ
ኳኳ
ኳኳኳ
"ማነው..?"....የጎረነነ ድምፅ ከጆሮዬ ገባ
አካሌን ሰንጥቆ
"ማነው" ደግሞ ይላል ማንነቴን አውቆ
ደጋገመው ማነህን ቃል
ያንተ ሌባ የሷ አፍቃሪ መሆኔማ ይታወቃል።
ባይገርምሽ....
ያነ ግዙፍ ባልሽ የመታኝ ፊቴ ላይ ምስልሽን አትሟል
"ያምሃል!"...ነው ያልሽኝ
አዎ!....ጉልበታም ፍቅረኛሽ እሱ እራሱ ታሟል
"ከሷ እራቅ!"...እያለ...
ይደበድበኛል ጠዋት እና ማታ
ታሞ አሳመመኝ ከልቤ ሊያወጣሽ የሞከረ ለታ
ያገባች ሴት ማፍቀር ህመም ቢሆን ዳር ትርጉሙ
"ያምሃል!" መባል ነው ለአፍቃሪ ህመሙ።
ላላገኝሽ እየገባኝ ተመኘሁሽ የውነት የውነት
ችግሬን ብትሰሚኝ እስቲ ምን አለበት
ልክ ነሽ ያመኛል!
እንቅልፍ የለም ባካላቴ ጭራሽ ዝርም አይልበት
'አፈቀርኩሽ' ባልኩኝ ጊዜ 'ያምሃል' ቃል ጥለሺበት
ኑሮ አይደለም የምኖረው ወይ አልተኛ አልነሳ
ያንቺን ውበት ፀባይ አመል እንዴት ብዬ ባንዴ ልርሳ
ደርሶብኛል ብዙ ውጊያ ባደረኩት ጥብቅ ትግል
የውሻ ነው የሱ አመል...ባልሽ ደግሞ ቶሎ ሚግል
ባይገርምሽ....
እንባ እንባ ይላል ሳቄ ደርሶ ድንገት ይከፋኛል
ውጥን ቃሌ ችላ ይላል ሁለመናሽ ያሳመኛል
ደግሞ አለ እንጂ ያረፈብኝ የባልሽ እጅ ያንቺ ምስል
መስታወት ፊት በቆምኩ ጊዜ አንቺን አንቺን የሚመስል
ብቻ ተይው....
ግን.....ያመኛል አይደል?
የማይሆን ወድጄ ለማይሆን ስጋደል
ግን....መታመም ነው መውደድ?
በፍቅር መተብተብ በፍቅር መገመድ
እንጃ....
ግን...
ያገባች ሴት ማፍቀር
ምንም ቢሆን ዳር ትርጉሙ
"ያምሃል" መባል ነው ለአፍቃሪ ህመሙ።
┄┅┅┄┅✶♥️✶┅┄┅┅┄
❤️❤️❤️ #Share ❤️❤️❤️
😘😍@Yenefekir😘😍
💝@Yenefekir💝
አይ አንቺ....''ያምሃል!'' አልሽኝ አይደል
የማይሆን ወድጄ ለማይሆን ስጋደል
(ርዕሱ ነው)
ባይገርምሽ....
ላንቺ ሲሆን ጊዜ
መንገዱ በሙሉ ጨርቅን መሰለልኝ
ስንክል የሌለበት
ከደጃፍሽ ቆምኩኝ
"ወዬ" የሚልን ቃል ካንቺ ላልሰማበት
ኳ
ኳኳ
ኳኳኳ
"ማነው..?"....የጎረነነ ድምፅ ከጆሮዬ ገባ
አካሌን ሰንጥቆ
"ማነው" ደግሞ ይላል ማንነቴን አውቆ
ደጋገመው ማነህን ቃል
ያንተ ሌባ የሷ አፍቃሪ መሆኔማ ይታወቃል።
ባይገርምሽ....
ያነ ግዙፍ ባልሽ የመታኝ ፊቴ ላይ ምስልሽን አትሟል
"ያምሃል!"...ነው ያልሽኝ
አዎ!....ጉልበታም ፍቅረኛሽ እሱ እራሱ ታሟል
"ከሷ እራቅ!"...እያለ...
ይደበድበኛል ጠዋት እና ማታ
ታሞ አሳመመኝ ከልቤ ሊያወጣሽ የሞከረ ለታ
ያገባች ሴት ማፍቀር ህመም ቢሆን ዳር ትርጉሙ
"ያምሃል!" መባል ነው ለአፍቃሪ ህመሙ።
ላላገኝሽ እየገባኝ ተመኘሁሽ የውነት የውነት
ችግሬን ብትሰሚኝ እስቲ ምን አለበት
ልክ ነሽ ያመኛል!
እንቅልፍ የለም ባካላቴ ጭራሽ ዝርም አይልበት
'አፈቀርኩሽ' ባልኩኝ ጊዜ 'ያምሃል' ቃል ጥለሺበት
ኑሮ አይደለም የምኖረው ወይ አልተኛ አልነሳ
ያንቺን ውበት ፀባይ አመል እንዴት ብዬ ባንዴ ልርሳ
ደርሶብኛል ብዙ ውጊያ ባደረኩት ጥብቅ ትግል
የውሻ ነው የሱ አመል...ባልሽ ደግሞ ቶሎ ሚግል
ባይገርምሽ....
እንባ እንባ ይላል ሳቄ ደርሶ ድንገት ይከፋኛል
ውጥን ቃሌ ችላ ይላል ሁለመናሽ ያሳመኛል
ደግሞ አለ እንጂ ያረፈብኝ የባልሽ እጅ ያንቺ ምስል
መስታወት ፊት በቆምኩ ጊዜ አንቺን አንቺን የሚመስል
ብቻ ተይው....
ግን.....ያመኛል አይደል?
የማይሆን ወድጄ ለማይሆን ስጋደል
ግን....መታመም ነው መውደድ?
በፍቅር መተብተብ በፍቅር መገመድ
እንጃ....
ግን...
ያገባች ሴት ማፍቀር
ምንም ቢሆን ዳር ትርጉሙ
"ያምሃል" መባል ነው ለአፍቃሪ ህመሙ።
┄┅┅┄┅✶♥️✶┅┄┅┅┄
❤️❤️❤️ #Share ❤️❤️❤️
😘😍@Yenefekir😘😍
💝@Yenefekir💝