ፍርድ ቤቱ : በነጻ እንዲሰናበቱ ወስኗል
#Ethiopia | በፌዴራል ፍርድ ቤት ሀዋሳ ምድብ ችሎት ተይዞ የነበረዉ የረ/ፕ ጸጋዬ ቱኬ፣ የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ኮሚሽነር አበራ አሬራና እንዲሁም የረ/ፕሮፈሰሩ የእህት ልጅ አብረሃም አማሎ ክስ ፍርድ ቤቱ በ11/06/2017 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት በነጻ እንዲሰናበቱ ወስኗል።
በሦስቱ ተከሳሾች ላይ የክልሉ አቃቤ ሕግ በሙስና ፈጽመዋል በሚል ክስ አቅርቦባቸዉ ሲከራከሩ የቆዩ ሲሆን ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ሲያከራክር ከቆየ በኋላ ነጻ መሆናቸዉን አረጋግጦ ከቀረበባቸዉ የሀሰተኛ ክስ ነጻ አዉጥቷቸዋል ሲሉ ጠበቃ ገብረመድህን ተክላይ በስልክ አድርሰውኛል።
የቀድሞው የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ እና የቀረቡባቸውን ክሶች የማይገባ ጥቅም በመቀበል የሙስና ወንጀል በመፈጸም እና በወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ በማቅረብ የተከሰሱት የቀድሞው የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ጸጋዬ ቱኬ፤ በቀረቡባቸው ሁለት ክሶች ላይ እንዲከላከሉ ብይን ተሰጥቶ ነበር። በቀድሞው ከንቲባ እና አብረዋቸው በተከሰሱ ሁለት ተከሳሾች ላይ ጥቅምት 19፣ 2017 ብይኑን የሰጠው፤ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሀዋሳ ማዕከል ነው።
የሲዳማ ክልል ፍትህ ቢሮ፤ በአቶ ጸጋዬ እና ሁለት ተከሳሾች ላይ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ የመሰረተው፤ ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር መጀመሪያ ላይ ነበር። በአንድ መዝገብ ክስ ከቀረበባቸው ተከሳሾች መካከል፤ የሲዳማ ክልል የቀድሞ የፖሊስ ኮሚሽነር አቶ አበራ አሬራ ይገኙበታል።
የክልሉ ዐቃቤ ህግ በአቶ አበራ እና በአቶ ጸጋዬ ላይ የመሰረተው የመጀመሪያ ክስ፤ በሙስና ወንጀሎች አዋጅ የተቀመጠን ድንጋጌ በመተላለፍ “የማይገባ ጥቅም በመቀበል የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል” የሚል ነው።
የመጀመሪያው ክስ፤ በሀዋሳ ከተማ ሳውዝ ስታር ኢንተርናሽናል ሆቴል ጎን የተወሰደ ቦታ ምትክ መሬት እንዲሰጥ ከቀረበ ጥያቄ ጋር የተያያዘ ነው።
የምትክ ቦታ ጥያቄ ቀርቦ የነበረው፤ ከአቶ ጸጋዬ አስቀድሞ በነበሩት የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ የአመራር ጊዜ እንደነበር በክሱ ተመላክቷል። አቶ ጥራቱ የምትክ ቦታ እንዲሰጥ ውሳኔ ቢያስተላልፉም፤ የመሬት ርክክብ ከመፈጸሙ በፊት ከኃላፊነታቸው በመነሳታቸው ጉዳዩ እርሳቸውን ለተኳቸው አቶ ጸጋዬ ተላልፏል የሚል ነበር።
ዛሬ በዋለው ችሎት ሦስቱንም የፌዴራል ፍርድ ቤት ሀዋሳ ምድብ ችሎት በነጻ አሰናብቷቸዋል ፤ ሁለተኛው ክስ በክልሉ ፍርድ ቤት የሚታይ ይሆናል ሲሉ ጠበቃ ገብረመድህን ተክላይ አስረድተዋል።
@Yenetube @Fikerassefa