"... ድምፅሽ ሲርቅ ከጆሮዬ
መጠውለጉን ባየሽልኝ
ያ ገራገር ሰውነቴ..."
... እጁን ከትከሻዋ ላይ አኑሯል የሚያቋርጡትን አስፓልት እየተገላመጠ ከመንገድ የተቀበለውን የጎሳዬን ለቅሶ ያስተጋባል...
የተለያየ ንፋስ እንደሚነፍስባቸው አልታየውም...
ከደስታው ጋር ናፍቆት ይነፍሳል...
ከደስታዋ ጋር ስጋት ይበርዳታል...
መች ነው ማገኛት ይላል...
ልቤ እሺ በለኝ ይቅርብኝ ትላለች...
አንድ አይነት ናፍቆት የላቸው
አንድ አይነት ስጋት አይሰጉም
"... የኔ ማር ወለላ
አልመኝም ካንቺ ሌላ
ፍፁም ልጅ ነሽ አንቺ
መቼም የማትሰለቺ..."
ይህን ፊቱ እያበራ አይኗን እያየ ነው ያዜመው
"... ይሄን ዘፈን ትወደዋለህ..."
"... ህመሙ ደስ ይለኛል...መለየትን ታመመው... አያምርም?..."
" ማጣት ትፈራለህ?"
"... አያስፈራም?”
ጥያቄዋን በጥያቄ መለሰው...
አይኖቿን መለሰች...
መለያያቸው ደርሶ ሊሰናበታት ነው...
ዛሬን ልታልፍ አልፈለገችም... " የውሸት ከማግኘት የእውነት ማጣት አይሻልም?”
ያልጠበቀው ጥያቄ ነው... አይኖቿ ውስጥ ማብራሪያ ይፈልጋል... ልቡ ውስጥ ያለውን ናፍቆት አይኗ ላይ አላገኘም... አልተግባቡም... ጥያቄዋ ለርሱ ይሁን ለራሷ ግልፅ አልሆነላትም... ዳግም እንደማታገኘው ያህል ተሰናበተች...
|ዘካሪያስ|
°•.• @yenie_kal •.•°
@yenie_kal
○○○○○○○