መዝሙር በግጥም


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Религия


መዝሙር 147:7
ለእግዚአብሔር በምስጋና ዘምሩ፤ ለአምላካችንም
በመሰንቆ ምስጋና አቅርቡ።

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Религия
Статистика
Фильтр публикаций


🔗 መንፈሳዊ ቻናል ለማሳደግ ሲባል የተዘጋጀ መንፈሳዊ ቻናልና የሚሳተፉበት ልዩ wave ተዘጋጅቷል በ አጭር ጊዜ ብዙ ሜንበር ያገኙበታል


✍ ለመመዝገብ 👉
@oparina2


✞ አቡነ አረጋዊ ✞

አቡነ አረጋዊ
ጻድቁ ባሕታዊ
የወንጌል መምሕር
የሾመኽ እግዚአብሔር ፪


አቡነ አረጋዊ        ዘንዶውን ረግጠኽ
አቡነ አረጋዊ        እንደ አ
ምደ ክርስቶስ
አቡነ አረጋዊ        ወጣኽ ተራራው ላይ
አቡነ አረጋዊ        ሥሙን ለመቀደስ
አቡነ አረጋዊ        ግሩም የአምላክ ሥራ
አቡነ አረጋዊ        እጹብ የእርሱ ነገር
አቡነ አረጋዊ        በአንተ ጽኑ ዕምነት
አቡነ አረጋዊ        በቃን ለመከበር
           አዝ=====
አቡነ አረጋዊ        ዳሞም መሠከረች
አቡነ አረጋዊ        መምሕር ይኸው ብላ
አቡነ አረጋዊ        ሐይቅም አሞገሰች
አቡነ አረጋዊ        ጸጋን ተቀብላ
አቡነ አረጋዊ        እነ ኢየሱስ ሞዓ
አቡነ አረጋዊ        ከአንተ ሥለ ወጡ
አቡነ አረጋዊ        በኢትዮጵያ ምድር
አቡነ አረጋዊ       ትልቅ ለውጥ አመጡ
           አዝ=====
አቡነ አረጋዊ        በዕምነት የጸናኽ
አቡነ አረጋዊ        የወንጌል ምሥክር
አቡነ አረጋዊ        የሠራዊት ጌታ
አቡነ አረጋዊ        የቃኘኽ በክብር
አቡነ አረጋዊ        አቡነ አቡነ
አቡነ አረጋዊ        ብዬ ሥጠራኽ
አቡነ አረጋዊ        ቶሎ ድረስልኝ
አቡነ አረጋዊ        ርዳኝ በምልጃኽ


#አቡነ_አረጋዊ
አቡነ አረጋዊ
ጻድቁ ባሕታዊ
የወንጌል መምህር
የሾመህ እግዚአብሔር


ዘንዶውን ረግጠህ--- አቡነ አረጋዊ
እንደ አምደ ክርስቶስ--- አቡነ አረጋዊ
ወጣህ ተራራው ላይ--- አቡነ አረጋዊ
ስሙን ለመቀደስ--- አቡነ አረጋዊ
ግሩም የአምላክ ሥራ--- አቡነ አረጋዊ
እጹብ የእርሱ ነገር --- አቡነ አረጋዊ
በአንተ ጽኑ እምነት --- አቡነ አረጋዊ
በቃን ለመከበር --- አቡነ አረጋዊ

ዳሞም መሠከረች--- አቡነ አረጋዊ
መምህር ይኸው ብላ --- አቡነ አረጋዊ
ሐይቅም አሞገሰች ---- አቡነ አረጋዊ
ጸጋን ተቀብላ --- አቡነ አረጋዊ
እነ ኢየሱሰ ሞዓ --- አቡነ አረጋዊ
ካንተ ስለወጡ --- አቡነ አረጋዊ
በኢትዮጲያ ምድር ላይ---- አቡነ አረጋዊ
ትልቅ ለውጥ አመጡ ----- አቡነ አረጋዊ

በእምነትህ የጸናህ --- አቡነ አረጋዊ
የወንጌል ምስክር --- አቡነ አረጋዊ
የሠራዊት ጌታ --- አቡነ አረጋዊ
የቃኘህ በክብር --- አቡነ አረጋዊ
አቡነ አቡነ --- አቡነ አረጋዊ
ብዬ ስጠራህ --- አቡነ አረጋዊ
ቶሎ ድረስልኝ --- አቡነ አረጋዊ
እርዳኝ በምልጃህ --- አቡነ አረጋዊ


https://t.me/maedot_ze_orthodox


𓆩 አቡነ አረጋዊ 𓆪

ኧኸ   ክበር /ተመስገን/(፪)

በዚያች ተራራ ደብረ ዳሞ
ዘንዶ በገላው ተጠምጥሞ
ከማንም በፊት የደረሰው
አረጋዊ ነው ጻድቁ ሰው


የእዚአብሔር ታማኝ አገልጋይ
በትር የሚያፀድቅ ድንጋይ ላይ
በእምነቱ ጽኑ ባሕታዊ
የአሮን ምሳሌ አረጋዊ

የጻድቁ አባት መቀመጫ
ከኃጢአት ሁሉ ነጻ መውጫ
የጽድቅ ቦታ ነች ፈጽሞ
አምሳለ ገነት ደብረ ዳሞ



┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
  @maedot_ze_orthodox
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


🕯 .... ቅዱስ ሚካኤል.... 🕯

ክብር ለሚገባው ክብርን እንሰጣለን
ንጉሥ ለወደደው እንሰግድለታለን
እንኳን ለሚካኤል ለሚቆም ጌታ ፊት
ክብርን እንሰጥ የለ ለምድር ሹማምነት


✝️ሚካኤል አባታችን አማላጃችን☦️


♡ አሳዳጊዬ ♡


አሳዳጊዬ ማይልህ አንተ ያላሳደግከው
ማን አለ ሚካኤል ከፍ ያላደረግከው
የሕይወቱ ነህ ከፍታ ክብርና ማዕረጌ
አልረሳም ሥራህን በቤትህ አድጌ


ከልጆቹ መሐል አንዷ ምስክር ነኝ
ሚካኤል አባቴ እርሱ እየጠበቀኝ
መጠበቅን ያውቃል መሰወር ከክፉ
አለው እየረዳኝ ከልሎኝ በክንፉ
መልካም
ን ያደርጋል ወዳጅ ለወዳጁ
ድንቅ አድርጎልኛል ሚካኤል ለልጁ

አዝ= = = = =
ይሰምራል የልቤ ጠይቄው አላፍርም
እርሱ ከእኔ ጋር ነው ብቻዬን አልቆምኩም
የትላንት ታሪኬ መዝገቡ ቢከፈት
በነገሬ ሁሉ ሚካኤል አለበት
መልካምን ይደርጋል ወዳጅ ለወዳጅ
ድንቅ አድርጎልኛል ሚካኤል ለልጁ

አዝ= = = = =
መገኛዬ ደጁ ሌላ አድራሻ የለኝ
የሚካኤል ልጅ ነኝ በፍቅሩ ያደኩኝ
በመላኩ ምልጃ አጊጧል ሕይወቴ
ለኔ ያላረገው ምን አለ አባቴ
መልካምን ያደርጋል ወዳጁ ለወዳጁ
ድንቅ አድርጎልኛል ሚካኤል ለሌጁ

አዝ= = = = =
ከኔ አልተለየም ዛሬም በሕይወት
አየዋለሁ ቀድሞ ሁልጊዜ ከፊቴ
ይሄ ነው ምስጢሬ ወጥቶ የመግባቴ
ሚካኤል ይመስገኔን ኃያሉ አባቴ
መልካም ያደርል ወዳጅ ለወዳጁ
ድንቅ አድርጎልኛል ሚካኤል ለልጁ

አዝ= = = = =
መገኛዬ ደጁ ሌላ አድራሻ የለኝ
የሚካኤል ልጅ ነኝ በፍቅሩ ያደኩኝ
በመላኩ ምልጃ አጊጧል ሕይወትቴ
ለኔ ያላደረገው ምን አለ አባቴ
መልካምን ያደርጋል ወዳጅ ለወዳጁ
ድንቅ አድርጎልኛል ሚካኤል ለልጁ

መዝሙር
ዘማሪት ሊዲያ ታደሰ

┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
   @maedot_ze_orthodox
   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


ይለይብኛል ሚካኤል


ጠብቆ አሳድጎ ከ
ልጅነቴ
አባት እየሆነኝ ሚካኤል አባቴ
ይለይብኛል ሚካኤል ይለይብኛል(2)
በክንፉ ሸፍኖ በቤቱ አሳድጎኛል (2)

አያምርብኝ ብዘነጋ
ው ታሪኬን
ሚካኤል ነው ያስጌጠልኝ ህይወቴን
አረሳብኝ እርሱ አትርሳብኝ ያልኩትን
ለካስ ሰምቶኝ ኖሯል የልጅነት ጸሎቴን

ሚካኤል ያን ሁሉ ዘመን የታገሰኝ
ሚካኤል===ፍሬ ጠብቆ ያልቆረጠኝ
ሚካኤል===የከፍታዬ መሰላል
ሚካኤል===መነሻዬ ሆነሀል


እንዳይከፋኝ እንዳልደፋ አንገቴን
እንዳላለቅስ እንዳለፈስ እንባዬን
እንዳይርቀኝ ደስታ በመንፈሴ እንዳልዝል
ካጠገቤ አይርቅም ያሳደገኝ ሚካኤል

ሚካኤል ቀኔም ቀን አይሆን ሳልጠራህ
ሚካኤል===ና ድረስልኝ ሳልልህ
ሚካኤል===እንዳስጀመርከኝ ጅማሬዬን
ሚካኤል===አሳምረው ፍፃሜዬን


ውድቅ አረገው የጠላቴ ክፉ እቅድ
አራመደኝ በከፍታዬ መንገድ
ሊያስቀረኝ አልቻለም ሊጎትተኝ ባላጋራ
ተጥሎ ስላለ በእግዚአብሔር ድንቅ ስራ

ሚካኤል===እሳታዊ ነው ነበልባል
ሚካኤል===ጠላቴ ፊትህ ይቀልጣል
ሚካኤል===ለኔ አይኔ ነው መከታዬ
ሚካኤል===የዘለዓለም ጠባቂዬ

እንዳይከፋኝ እንዳልደፋ አንገቴን
እንዳላለቅስ እንዳለፈስ እንባዬን
እንዳይርቀኝ ደስታ በመንፈሴ እንዳልዝል
ካጠገቤ አይርቅም ያሳደገኝ ሚካኤል

ሚካኤል ቀኔም ቀን አይሆን ሳልጠራህ 
ሚካኤል===ና ድረስልኝ ሳልልህ
ሚካኤል===እንዳስጀመርከኝ ጅማሬዬን
ሚካኤል===አሳምረው ፍፃሜዬን


♡ ብዙ ልጆች አሉት ♡

ብዙ ልጆች አሉት ለሥሙ ምሥክር
በዙሪያው ያሉትን አብቅቷል ለክብር
ስለ ፍጹም ምልጃው ለእኔ ግን ይለያል
መልዓኩ ሚካኤል ስለው ደስ ይለኛል


ከመላዕክት ክብሩ ከፍ ከፍ ብሎ
በአምላኬ ተሾመ ዘንዶውንም ጥሎ
አሳዳጊዬነው ሆኖ እናት አባቴ
ሚካኤል በአለበት ይሸሻል ጠላቴ

ከሚታየው ሁሉ ልቤ ከሚፈራው
ካላየሁት ነገር ጠላት ከሰወረው
ያድነኛል ፈጥኖ በመንገዴ ወቶ
ሚካኤል ሀያሉ ክንፎቹን ዘርግቶ

በባሕራን ታሪክ በነተላፊኖስ
በአፎምያ መትረፍ በነ ዱራታኦስ
በነብዩ ዳንኤል መች ይፈጸምና
የሚካኤል ስራ ይቀጥላል ገና

በጉዞ የረዳችሁ በባሕር በየብሱ
ፈጥኖ ደርሶላችሁ ዕንባን ስታፈሱ
ስለታችሁ ሰምሯል ቁሙ ለዝማሬ
በሚካኤል ምልጃ የቆማችሁ ዛሬ


ክብር ለሚገባው ክብርን እንሰጣለን
ንጉሥ ለወደደው አንሰግድለታለን
እንኳን ለሚካኤል ለሚቆም ጌታ ፊት
ክብርን እንሰጥ የለ ለምድር ሹማምንት

መዝሙር
በሊቀ መዘምራን ቴዎድድሮስ


✞ የኛ አባት ሚካኤል

ሲያርፍ ያመሰግናል ሲያመሰግን ያርፋል
ሲያርፍ ያመሰግናል ሲያመሰግን ያርፋል
የኛ አባት ሚካኤል/2/ምሕረት ይለምናል


በቅድመ ሥላሴ በጉልበቱ ሰግዶ
ምስጋናን ያቀርባል የውዳሴን ነዶ
ምሕረትን ይዞ ከአምላክ ዘንድ ተላከ
ለማኑሄ ድ
ርሳን ምስራች ሰበከ

አዝ___
ችግርን አልፋለሁ ይረሳል ሀዘኔ
በሕይወቴ ሠልፎች ስላለ ከጎኔ
ከአምላኬ ተልኮ የታደገኝ ከሞት
መርቶ ያደርሰኛል ከሠማዩ መንግስት

አዝ___
የአምላክ ስም በላዩ ስላለ ታትሞ
ከፊቴ ይወጣል በመንገዴ ቀድሞ
ያድናል ሚካኤል ጭንቀትን አርቆ
የወህኒውም መዝጊያ ይከፈታል አውቆ

አዝ___
ልጄ ነህ ብሎኛል አባቴ እለዋለሁ
ለአምላኬ ዘመርኩኝ ሲዘምር ስላየሁ
አይደክምም ልሳኑ አያውቅም ዝምታ
ምስጋና ምግቡ ነው ዘውትር ጠዋት ማታ

አዝ___
ስለህዝቡ ልጆች የሚነሳው መልዓክ
አንተነህ ሚካኤል የመረጠህ አምላክ
ዝማሬ ጸሎቴ አይሁንብኝ ከንቱ
ከእጣኑ ጢስ ጋር ይውጣልኝ በፊቱ


ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ


♡ አሳዳጊዬ ♡


አሳዳጊዬ ማይልህ አንተ ያላሳደግከው
ማን አለ ሚካኤል ከፍ ያላደረግከው
የሕይወቱ ነህ ከፍታ ክብርና ማዕረጌ
አልረሳም ሥራህን በቤትህ አድጌ


ከልጆቹ መሐል አንዷ ምስክር ነኝ
ሚካኤል አባቴ እርሱ እየጠበቀኝ
መጠበቅን ያውቃል መሰወር ከክፉ
አለው እየረዳኝ ከልሎኝ በክንፉ
መልካም
ን ያደርጋል ወዳጅ ለወዳጁ
ድንቅ አድርጎልኛል ሚካኤል ለልጁ

አዝ= = = = =
ይሰምራል የልቤ ጠይቄው አላፍርም
እርሱ ከእኔ ጋር ነው ብቻዬን አልቆምኩም
የትላንት ታሪኬ መዝገቡ ቢከፈት
በነገሬ ሁሉ ሚካኤል አለበት
መልካምን ይደርጋል ወዳጅ ለወዳጅ
ድንቅ አድርጎልኛል ሚካኤል ለልጁ

አዝ= = = = =
መገኛዬ ደጁ ሌላ አድራሻ የለኝ
የሚካኤል ልጅ ነኝ በፍቅሩ ያደኩኝ
በመላኩ ምልጃ አጊጧል ሕይወቴ
ለኔ ያላረገው ምን አለ አባቴ
መልካምን ያደርጋል ወዳጁ ለወዳጁ
ድንቅ አድርጎልኛል ሚካኤል ለሌጁ

አዝ= = = = =
ከኔ አልተለየም ዛሬም በሕይወት
አየዋለሁ ቀድሞ ሁልጊዜ ከፊቴ
ይሄ ነው ምስጢሬ ወጥቶ የመግባቴ
ሚካኤል ይመስገኔን ኃያሉ አባቴ
መልካም ያደርል ወዳጅ ለወዳጁ
ድንቅ አድርጎልኛል ሚካኤል ለልጁ

አዝ= = = = =
መገኛዬ ደጁ ሌላ አድራሻ የለኝ
የሚካኤል ልጅ ነኝ በፍቅሩ ያደኩኝ
በመላኩ ምልጃ አጊጧል ሕይወትቴ
ለኔ ያላደረገው ምን አለ አባቴ
መልካምን ያደርጋል ወዳጅ ለወዳጁ
ድንቅ አድርጎልኛል ሚካኤል ለልጁ

መዝሙር
ዘማሪት ሊዲያ ታደሰ

┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
   @maedot_ze_orthodox
   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


ከሚካኤል በቀር


ከሚካኤል በቀር የሚያጽናናኝ የለም
ረዳቴ እርሱ ነው በመከራዬ ቀን



ሃዘኔ እጅግ በዝቶ - ከሚካኤል በቀር፣
የየሚረዳኝ ሳይኖር በስደ
ቴ ዘመን፣
ሰላም ከእኔ ርቆ - ከሚካኤል በቀር፣ ጭንቀት አስጠብቦኝ በዙሪያዬ ከቦኝ፣
ዛሬ ግን አጽናኜ - ከሚካኤል በቀር፣
ሚካኤል ደረሰ ጠላቴ አፈረልኝ።
ሚካኤል ነው - የዳዊት ረዳት ከጎልያድ ያዳነው፣
ሚካኤል ነው - መንፈሳዊ ብርታት ኃይልንም የሠጠው

ቃልኪዳኑ ግሩም - ከሚካኤል በቀር፣
ዝክሩን ለዘከሩት ስሙንም ለጠሩት፣
አጋንንት አይቀርቡም - ከሚካኤል በቀር፣
ስዕሉ ባለበት ድርሳኑን ቢደግሙት፣
በረከት ይገኛል - ከሚካኤል በቀር፣
በእርሱ ቢማጸኑት ከለመኑት በእውነት።
ሚካኤል ነው - በትረ መስቀል ይዞ የሚጠብቀኝ፣
ሚካኤል ነው - ከአንበሶች መንጋጋ የሚታደገኝ


በኑሮአችን ሁሉ - ከሚካኤል በቀር፣
እርሱ ይመራናል ፈጥኖ ይረዳናል፣
ፈርኦንን ድል ነስቶ - ከሚካኤል በቀር፣
ከግብጽ አውጥቶናል በብርሃን መርቶናል፣
የኤርትራን ባሕር - ከሚካኤል በቀር፣
ከፍሎ እንዳሻገረን ከነዓን ገብተናል፣
ሚካኤል ነው - ከበለአም እርግማን እስራኤልን ያዳነው፣
ሚካኤል ነው - ዛሬም በአዲስ ኪዳን ስሙ የገነነው


በሕብረት የተዘመረ

@z_mezmur

748 0 18 1 10

♡ አዝላው ወረደች ♡


አዝላው ወረደች ወደ ግብፅ(፪)
ስደተኛዋ የአምላክ እናት
ይህ ዓለም ለእርሷ መች ተገባት


ዓለም በምኗ ታስተናግዳት
የፍቅር ምንጯ ተሟጦባት
እነ ኮቲባን እየላከች
የአምላክን እ
ናት ተሳደበች
እነ ሄሮድስን እየላከች
ህፃኑን ልትገድል አሳደደች
       
አዝ= = = = =
የክብርን ጌታ ተሸክማ
ውርደት ለበሰች እንደ ሸማ
የሀብቱን ጌታ በጀርባ አዝላ
ሰው ተዘከራት ተቸግራ
      
አዝ= = = = =
በቃሉ ትዕዛዝ ምድርን ሠርቶ
ተንከራተተ ማደሪያ እጥቶ
ጌታ ሲወለድ የምሥራች
በረት ሰጠችው ዓለም ታካች
      
አዝ= = = = =
ግና መላእክት በሰማያት
ሃሌ ሉያ አሉ በፍርሃት
ወልድን በአብ ቀኝ ከላይ አይተው
ደግሞም በምድር ከድንግል ክንድ
ከላይም ሳይጎድል ተመልክተው{፪}
      
አዝ= = = = =
ዓለም በምኗ ታስተናግዳት
የፍቅር ምንጯ ተሟጦባት
እነ ኮቲባን እየላከች
የአምላክን እናት ተሳደበች
እነ ሄሮድስን እየላከች
      
አዝ= = = = =
ህፃኑን ልትገድል አሳደደች
በቃሉ ትዕዛዝ ምድርን ሠርቶ
ተንከራተተ ማደሪያ እጥቶ
ጌታ ሲወለድ የምሥራች
በረት ሰጠችው ዓለም ታካች

          መዝሙር
        ይልማ ኃይሉ

┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@maedot_ze_orthodox
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


🌸 ሰንበተ ክርስትያን 🌸

በኩር ናት የበዓላት
ኑ ከፍ ከፍ እናድርጋት
በእሷ ደስ ይበለን
በሰንበተ ክርስቲያን

በዝማሬ እንበርታ በገናውን እንያዝና
መልካም ስራ የሚሰራባት
ሰንበት ቅድስት ናት እና
ከጨለማ ብርሀን ከመገዛት ነፃነት
እግዚአብሔር ይህን ሰጠን
ደስ ይበለን በሰንበት

ለአብርሃም ተገልጣለች
ለሙሴም በደብረ ሲና
በነቢያት የታወቀች
ሰንበት ዳራዊት ናት እና
በሳምንቱ ሰለጠነች
ተሰበከች በሐዋርያት
ሃሌ ሉያ ዕለተ ሰንበት
ተሰጠችን ልናርፍባት

በእልልታ እንሞላ እንደ ነቢዩ አሳፍር
በከበረች የሰንበት ቀን ኑ ለቅኔ እንሰለፍ
በመቅደሱ ናቸው እና ቅዱስነትና ግርማ
ውዳሴያችን ይሰማልን
ከምድር እስከ እዮር እራማ

እግዚአብሔር አብ የባረካት
እግዚአብሔር ወልድ የቀደሳት
ከእለታት ሁሉ መርጦ
መንፈስ ቅዱስ ከፍ ያደረጋት
በእርሷ ሀሴት እናድርግ
እናክብራት እንድንከብር
የደጀሰላሙ ታዛ በመቅደሱ እንሰብሰብ



ሰናይ ዕለተ ሰንበት 💝


♡ እውነተኛ ስላም ♡

እውነተኛ ሰላም ያለው ከቤትህ ነው
እውነተኛ ሰላም ያለው ከቤትህ ነው
እርዳኝ አልናወጽ እለምንሀለሁ{፪}

ሀጢያቴን ሳስበው ልቤ ይጨነቃል
ከአንተ መለየቴ ነፍሴን አድክሟታል
ወደ አንተ መልሰኝ እኔ እመለሳለው
እውነተኛ ሰላም ያለው ከቤትህ ነው

ለቅዳሴ ፆሎት ዘውትር እንዳልተጋሁ
በአደባባይ ቆሜ ስምህን እንዳልጠራሁ
ተሰነካክዬ ወድቄ አለሁና
እርዳኝ አማኑኤል በሀይማኖት ልፅና

አይኔ እንባን ያምንጭ ላልቅስ ስለ ሀጢያቴ
የንስሀ ትሁን ቀሪዋ ህይወቴ
በመዳኔ ሰአት በዛሬዋ ለት
ፍቅርህን አስቤ መጣሁ ከአንተ ፊት


ጌታ ሆይ ፀፀቴን እንባዬን ተቀበል
አባትሽ ነኝ በለኝ እኔም ልጅ ነኝ ልበል
ዘይት ሳላዘጋጅ ድንገት መተህብኝ
በርህን በመዝጋት ከደጅ አታስቀረኝ


✣ ስለማይነገር ሥጦታው ✣


ስለማይነገር ሥጦታው እግዚአብሔር ይመስገን
ቸል ያላለን አምላክ ስንጓዝ ማዕበሉን አቋርጠን
ስለማይነገር ሥጦታው እግዚአብሔር ይመስገን።


የሕይወት እስትንፋስ ዘራብን ሕያው እንድንሆን
ይህን ያደረገ አምላካችን እግዚአብሔር ይመስገን
ስለማይነገር ሥጦታው እግዚአብሔር ይመስገን


ነፋስን ገስጾ ማዕበል አቆሞ የሚያሻግር
የዓለም ፈተና ቢበዛ እርሱ መጠጊያችን
ስለማይነገር ሥጦታው እግዚአብሔር ይመስገን

ዳግም እን
ዳንሞት በሞቱ ሞትን የረታልን
የምንመካበት ትንሣኤን ሰላምን ለሰጠን
ስለማይነገር ሥጦታው እግዚአብሔር ይመስገን

ከሲኦል እስራ
ት ተፈተን ነጻ የወጣንበት
መስቀሉን ለሰጠን ለአምላካችን እንዘምር በእውነት
ስለማይነገር ሥጦታው እግዚአብሔር ይመስገን
               
         መዝሙር
በዘማሪ ቸርነት ሠናይ


♡ መስቀል ላይ ያየሁት ፍቅር ♡


መስቀል ላይ ያየሁት ፍቅር (፪)
ይቀሰቅሰኛል ለስሙ እንድዘምር (፪)

ፊቱን እያጣፉት እየተንገላታ
በጦር እየወጉት ይሰጣል ይቅርታ
እነርሱ እየጠሉት እርሱ ይወዳቸዋል
አስረው ሲጎትቱት ይከተላቸዋል


ፃድቁን ኃጥዕ ነው እውነቱን ሐሰት
እያሉ ሲጮሁ ይሰቀል ይሙት
እየመረመረው ፍጡር ፈጣሪን
ክርስቶስን አስሮ ፈታው በርባንን

ጀርባውን ሲገርፉት በሚያቃጥል ጅራፍ
በምህረት ያዛቸው በይቅርታው እቅፍ
ጨክነው ሲያጠጡት መራራ ሐሞት
ደም ውሃ ፈሰሰ ጎኑን ሲወጉት


ግምጃን አለበሱት ቀሚሱን ገፈው
በራሱም አኖሩ እሾህ ጎንጉነው
የአይሁድ ንጉስ ሆይ እያሉ ዘበቱ
ለህይወት ሆናቸው የኢየሱስ ሞቱ


           መዝሙር
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ


┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
   @maedot_ze_orthodox
   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


♡ ፍቅርን ከክርስቶስ ትሕትናን ከማርያም


ፍቅርን ከክርስቶስ ትሕትናን ከማርያም ያልተማረ አገልጋይአይሆንም ምሣሌ ይውረድ ከአትሮኖስ ላይ/፪/


ሥለ ሚአሳድዱት እርሱ ካልጸለየ
በምንስ ተለየ የሚናገረውን በተግባር
ካልኖረ ምኑን አስተማረ


የሚያምነውን ጌታ በሕይወት ከአልገለጠ
መቼ ተመረጠ እየተበደለ ካላለ ይቅርታ
አያውቀውም ጌታ

ልቡ ሣይሰበር ወንጌሉን ቢዘራ
አንዳች አያፈራ ከእኔ ይልቅ ወንድሜ
ካላለ ብርቱ ነው ድካሙ ከንቱ ነው


ክፉውን ተጠይፎ ከአልቆመ ለእውነት
ሥብከቱ ነው ሐሰት ብርሐንን ሠብኮ
በጨለማ ከአለ ራሱን አታለለ

እርስ በርሷ መንግስት ከተከፋፈለች
መቼ ትጸናለች አባቶች ታረቁ ብኩርናን
ትታችሁ አንድ ይሁን መንጋችሁ


ፍቅርን ከክርስቶስ ትሕትናን ከማርያም
ያልተማረ አገልጋይ አይሆንም ምሣሌ
ይውረድ ከአትሮኖስ ላይ።

በጸጋ ሥጦታው ራሱን ከካበ
የጌታ ባርያው ነኝ ብሎ ካላሰበ
አምላክን ጸንሳ ጌታን የወለደች
ለፍጹም ትሕትና ማርያም ምሣሌ ነች


ለፍጹም ትሕትና ማርያም ምሣሌ ነች
ለፍጹንም ትሕትና ማርያም ምሣሌ ነች

ፍቅርን ከክርስቶስ ትሕትናን
ከማርያም ያልተማረ አገልጋይ
አይሆንም ምሳሌ ይውረድ ከአትሮኖስ ላይ አይሆንም ምሣሌ ይውረድ ከአትሮኖስ ላይ አይሆንም ምሣሌ ይውረድ ከአትሮኖስ ላይ


🌿 በዘንባባሽ ባርኪኝ 🌿
✝️ ✝️ ✝️

በዘንባባሽ ባርኪኝ አርሴማ/2/
የተጋድሎሽ ዜና በአለም ተሰማ

🌿 አዝ 🌿

በረከትሽ ብዙ ቃልኪዳንሽ ሀያል
ስምሽን ጠርቼ ልቤ መች ይረካል
በጨለማ
ዉ ልሂድ ቢበዛ መከራ
ሁሉን አለፈዋለዉ ስምሽን ስጠራ

🌿 አዝ 🌿

ገድልሽን ስሰማ ደነቃት ሂወቴ
ዘንባባሽን ይዘሽ ግቢልኝ ከቤቴ
ፀሎቴ ደረሰ ስለቴ ተሰማ
ሞገሴ ሆነሻል እናቴ አርሴማ

🌿 አዝ 🌿

አጋንት ወደቁ ሲጠራ ስምሽ
ልዩ ክብር አለሽ አምላክ የሰጠሽ
ነይ ተመላለሺ ግቢ ከቤታችን
የሂወትን ፅዋ ይዘሽ ለነብሳችን




“የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው፤ የኀጥኣን ስም ግን ይጠፋል።”
— ምሳሌ 10፥7

🥰እንኳን ✝⓹ለታላቁ አባታችን ለአቡተ ገብረ መንፈስ ቅዱስ✝️⓹ አመታዊ መታሰቢያቸው በአል በሰለማ አደረሳቹ አደረሰን

❤️አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ከክፉ ሁሉ ይጠቡቋቹ 🙏




✝️⓹ አሜን ⓹✝️

Показано 20 последних публикаций.