✞ እንወድሻለን ኪዳነምህረት ✞
ለእግዚአብሔር ታቦቱ መቅደሱ
ቀርበናል ባንቺ ወደ ንጉሡ
የክብራችን ጌጥ ሽልማት
እንወድሻለን ኪዳነምህረት
በጨለማው ላላ ብርሀንን አየ
ለርስቱ ተካፋይ እንዲሆን ተለየ
ወደ ቀድሞ ክብሩ ሊመለስ ዳግመኛ
አንቺ ነበርሽ ተስፋው ለአዳም መዳኛ
ያንሁሉ ዘመናት የፈሰሰው ደም
አለምን ከእስራት ሊፈታ አልቻለም
ወደ ሚሻል ኪዳን በደም ሊያሻግረን
ደምሽን ተዋሕዶ መድሃኒዓለም ዋጀን
አለን ብዙ ምክንያት አንችን ምንወድበት
አለም ያልተረዳው ያላወቀው እውነት
ያወቀ የተረዳ የመዳኑን ምስጢር
አያፍርም ክብርሽን ቆሞ ለመናገር
አውቃለሁ እግዚአብሔር የሰጠሽን ክብር ላመስግንሽ እኔም ሳልቀንስ ሳልጨምር
ሚባርክሽ ብሩክ ነውና እናቴ
ኪዳነምህረት ንገሽ እመቤቴ
ለእግዚአብሔር ታቦቱ መቅደሱ
ቀርበናል ባንቺ ወደ ንጉሡ
የክብራችን ጌጥ ሽልማት
እንወድሻለን ኪዳነምህረት
በጨለማው ላላ ብርሀንን አየ
ለርስቱ ተካፋይ እንዲሆን ተለየ
ወደ ቀድሞ ክብሩ ሊመለስ ዳግመኛ
አንቺ ነበርሽ ተስፋው ለአዳም መዳኛ
ያንሁሉ ዘመናት የፈሰሰው ደም
አለምን ከእስራት ሊፈታ አልቻለም
ወደ ሚሻል ኪዳን በደም ሊያሻግረን
ደምሽን ተዋሕዶ መድሃኒዓለም ዋጀን
አለን ብዙ ምክንያት አንችን ምንወድበት
አለም ያልተረዳው ያላወቀው እውነት
ያወቀ የተረዳ የመዳኑን ምስጢር
አያፍርም ክብርሽን ቆሞ ለመናገር
አውቃለሁ እግዚአብሔር የሰጠሽን ክብር ላመስግንሽ እኔም ሳልቀንስ ሳልጨምር
ሚባርክሽ ብሩክ ነውና እናቴ
ኪዳነምህረት ንገሽ እመቤቴ