የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ይዞ ሲጓዝ የነበረ መኪና የትራፊክ አደጋ ደርሶበት የሁለት ተማሪዎች ሕይወት አለፈ፡፡
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ወደ ቤተሰቦቻቸው ይዞ በመሄድ ላይ የነበረ መኪና በመገልበጡ 2
ተማሪዎች ሲሞቱ በ22 ተማሪዎች ላይ ደግሞ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደረሰባቸው።
አደጋዉ የደረሰዉ በምሥራቅ ጎጃም ዞን ደጀን ወረዳ ጢቅ የትኖራ ቀበሌ ዛሬ ሌሊት 8፡00
ላይ ነው፤ ከዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ ወደ ደቡብ ጎንደር ተማሪዎችን ይዞ በመሄድ ላይ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ መኪና ነው የትራፊክ አደጋ ያጋጠመው።
አደጋው በ2 ተማሪዎች ላይ ሞት፣ በ18 ተማሪዎች ቀላልና በ4 ተማሪዎች ላይ ከባድ
የአካል ጉዳት አድርሷል።
ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች በደጀን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እና በደብረማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል የሕክምና ዕርዳታ የተደረገላቸው ነው።
የአደጋዉ መንስኤ በመጣራት ላይ መሆኑን የምሥራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ የመንገድ
ትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ክፍል ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ጎበዜ ይርሳው ተናግረዋል።
Via AMMA
@zena24now