TGStat
TGStat
Введите текст для поиска
Расширенный поиск каналов
  • flag Russian
    Язык сайта
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Вход на сайт
  • Каталог
    Каталог каналов и чатов Поиск каналов
    Добавить канал/чат
  • Рейтинги
    Рейтинг каналов Рейтинг чатов Рейтинг публикаций
    Рейтинги брендов и персон
  • Аналитика
  • Поиск по публикациям
  • Мониторинг Telegram
channel 0

5 Jan 2020, 21:54

Открыть в Telegram Поделиться Пожаловаться

ወደ አላህ እንሺሽ‼
============
✍ አቡ ሁረይራህ እንዲህ ብለዋል፦ "ከጎጆዋ ውስጥ ያለች አሞራ በበዳይ በደል ምክንያት ትሞታለች።" ሙጃሂድ የተባሉ ዐሊምም እንዲህ ብለዋል፦ "እንስሳት ድርቅ በበረታ ጊዜ፤ የሰውን ልጅ ይረግማሉ። 'ይህ ሁሉ የሆነው በአደም ልጅ ጥፋት ነው!' ይላሉ።" ዒክሪማህም እንዲህ ብለዋል፦ "የምድር እንስሳትና ነፍሳት፤ እባብና ጊንጥ እንኳ ሳይቀሩ \በአደም ልጅ ጥፋት ምክንያት ዝናብ ተከለከልን!' ይላሉ።"
||
አውስትራሊያ የብዙ ፈሳድ መነኻሪያ ናት።
ለሙስሊሞችም አትመችም።
የህዝቧ ወንጀል መዘዙ ለዱር አራዊቷም ተርፏል።
በአውስትራሊያ ሰደድ እሳት እየተሰቃዩ ያሉ እንስሳት በጣም ያሳዝናሉ።
ሸሽተው ሸሽተው ሲደርስባቸው ያሳርራቸዋል።
እናት ልጇን ታቅፋ ለራሷ እየተቃጠለች፤ ከደቂቃዎች በኋላ እርሷንም ይጨምራታል።
ብቻ ያሳዝናሉ።
♠

ወንድሜ ሆይ! አደራ ስውር ወንጀልን ተጠንቀቅ። በውጭ ስትታይ መልካም መስለህ፤ በውስጥ ግን እኩይ አትሁን። ሁልጊዜም አላህ በእውቀቱ ከአንተ ጋር መሆኑን አስብ፤ ያይሀል፣ ይሰማሀል። አቡ ደርዳዕ እንዲህ ብለዋል፦ "አላህን እንደምታዩት አድርጋችሁ ተገዙት። ራሳችሁን ከሙታን ቁጠሩ። ከሚያበላሻችሁ ብዙ ሐብት ይልቅ የሚበቃችሁ ጥቂት በላጭ ነው። በጎ ሥራ እንደማይጠፋ፣ ወንጀል እንደማይረሳ እወቅ።" [አሕመድ ዘግበውታል።]
ሱለይማን አት-ተሚሚ እንዲህ ይላሉ፦ "አንድ ሰው በሚስጥር ወንጀል ሲፈጽም፤ ውርደቱ ከርሱ ላይ የተገለጸ ሁኖ ያነጋል።"
ዘኑን የተባሉ ዐሊምም "አላህን በሚስጥር የከዳ፤ ሚስጥሩን አላህ ይፋ ያወጣበታል!" ብለዋል። በአጠቃላይ ሐቢቢ "በድብቅ ወንጀል ስትሠራ፤ ገልጦ የሚያይህ አምላክ እንዳለ አትዘንጋ።" በቃ! የትም አታመልጠውምና ፍራው። "ወንጀል" የእውቀትን ችሎታ ይጋርዳል፣ ግንዛቤን ይዘጋል፣ ሲሳይን ያቅባል፣ ደስታን ያሳጣል፣ ከሰዎች ጋር ያቃቅራል፣ ነገሮችን ይቆላልፋል፣ መነገዶች እንዲዘጋጉና እንዲውሰበሰቡ ያደርጋል፣ ቀልብን ጽልመት ያወርሳል፣ ከበጎ ሥራ ያቅባል፣ እድሜን ያሳጥራል፣ አካልንም ልብንም ያደክማል፣ ሌላ ወንጀልንም ይወልዳል፣ ያዋርዳል፣ አዕምሮንና ቀልብን ይበክላል፣ ለእርግማን ይዳርጋል፣ በመጪው አለም ያስቀጣል፣ ይሉኝታን ያሳጣል፣ አላህን የማላቅ ስሜትን ያሟኣሽሻል፣ ከአላህ ጋር ያጣላል፣ ጸጋን ያስወግዳል፣ ብቀላን ያሰንፋል፣ የሰይጣንና ከንቱ ስሜት ምርኮኛ ያደርጋል። ስለዚህ ወንድሜ! አደራህን ከወንጀል ራቅ። ዛሬ በአለም ላይ በሙስሊሞች ላይ እየደረሰ ባለው ስቃይና መከራ የኔና ያንተ ወንጀል የፈጠረው ውጤት ሊሆን እንደሚችል አስብ። ምክንያቱም የወንጀል ቅጣት ለወንጀል ሠሪው ብቻ ላይሆን ይችላል።
||
በመልካም ዱዓችን አንርሳቸው።
ወደ አላህም እንሽሽ።
በኛ ላይ ለሚደርሱብን ጥቃቶች ዋናው መነሻ የራሳችን ወንጀልና ከአላህ ትዕዛዝ ማፈንገጥ ነው።
መፍትሄው ደግሞ ወደ አላህ መመለስ ብቻና ብቻ ነው።

አላህ በቁርኣን ላይ እንዲህ ይለናል፦
(وَمَا أَصَابَكُم مِّن مُّصِيبَةٍ فَبِمَا كَسَبَتْ أَيْدِيكُمْ وَيَعْفُو عَن كَثِيرٍ)
«ከመከራም ማንኛውም ያገኛችሁ ነገር፣ እጆቻችሁ በሰሩት (ኀጢያት) ምክንያት ነው፤ ከብዙውም ይቅር ይላል።»
[አሽ-ሹራ፡ 30]
*
✔️ የሚያገኘን መከራ ሁሉ መንስኤው እጃችን የከሰበችው ወንጀል ከሆነ፤
መከራው ይነሳ ዘንድ እጃችን ከወንጀል መሰብሰብ አለባት ማለት ነው። ይህን የነገረን እውነተኛው አምላካችን አላህ ነው። መቀበል እንጂ ቅንጣት ማመንታት አያስፈልግም።
||

Murad Tadesse

638 0 0
Каталог
Каталог каналов и чатов Подборки каналов Поиск каналов Добавить канал/чат
Рейтинги
Рейтинг каналов Telegram Рейтинг чатов Telegram Рейтинг публикаций Рейтинги брендов и персон
API
API статистики API поиска публикаций API Callback
Наши каналы
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Почитать
Академия TGStat Исследование Telegram 2019 Исследование Telegram 2021 Исследование Telegram 2023
Контакты
Справочный центр Поддержка Почта Вакансии
Всякая всячина
Пользовательское соглашение Политика конфиденциальности Публичная оферта
Наши боты
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot