Valentine's Day (የፍቅረኞች ቀን) በኢስላም‼️
===================================
«ጽሑፉን ለሌሎችም በማሰራጨት፤ ስለ ጉዳዩ በቂ ግንዛቤ የሌላቸውን ሙስሊሞች በማንቃት ከወንጀል እንታደግ‼️»
||
✍️ በእንግሊዝኛ ቋንቋ «Valentine's Day» የተሰኘውን ቀን በእኛ አማርኛ ስንመልሰው «የፍቅረኞች ቀን» የሚለው ገለፃ ይተካዋል።
በዐረብኛ ቋንቋ «عيد الحب» ይሰኛል።
ይህ ቀን በምዕራባዊቷ ቤተ ክርስቲያን በየ አመቱ ሐምሌ (አንዳንድ ሃገሮች ውስጥ July 6 እና ሌሎች ዘንድ ደግሞ July 30) ላይ ይከበራል።
የምሥራቃዊቷ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን (Eastern Orthodox Church) ግን ይህን ቀን የምታከብረው በየ አመቱ አሁን ባለንበት የየካቲት ወር (February 14) ላይ ነው።
ታዲያ ይህን ቀን አስመልክቶ ታሪካዊ አመጣጡንና ኢስላማዊ ብይኑን በተመለከተ የሚከተለውን ለማለት ወደድን።
||
1) ታሪክ፦
========
በቅድሚያ ይህ የ"ፍቅር በዓል" ወይም "የቫለንታይን ቀን" በመባል በክርስቲያኑ ማህበረሰብ በሰፊው የሚዘከረው አመታዊ ባህል መነሻው ባጭሩ ምንድነው?
ለሙስሊሙ ማህበረሰብ እውነታን በማሳወቅ ከተለያዩ ፀረ ኢስላም ተለምዶዎች እንዲጠነቀቅ ከፍተኛ ተጋድሎ ከሚያደርጉት የዳዕዋና የትምህርት ማእከላት አንዱ የሆነው በሳዑዲ ዓረቢያ ቅድስቲቷ ከተማ የሚገኘው ኡመልቁራ ዩኒቨርሲቲ "ኩሊየቱ-ዳዕዋ ወኡሱሉዲን" የጥናትና ምርምር ማዕከል ስለዚህ ጉዳይ ከምንጩ ለማወቅ ባደረገው ጥናት "ባርት" የሚባል የምዕራቡ አለም ደራሲ ስለ የዓለም በዓላት ሲዘረዝር ስለ "ቫለንታይን" የፃፈውን ወደ አረብኛ ከመለሱት እንደምንረዳው የ "ዒዱል ሁብ" ማለትም "የፍቅር በዓል" ስለሚባለው ባህል ትክክለኛ ምንነት በአራት ዋና ዋና ምክንያቶች ላይ በማንጠልጠል አብራርቷልና እንደሚከተለው ያንብቡት።☞
የ"ቫላንታይን ዴይ" መነሻ መላምት
∞∞∞∞∞=======∞∞∞∞∞
ደራሲው በሚለው መላምት
1ኛ/ ከ1700 አመታት በፊት በሮማ ላይ ጣዖታውያኑ የበላይ በነበሩበት ዘመን "ቫለንታይን" የተባለ ግለሰብ ከጣዖት አምላኪነት ወደ ክርስትና ተቀየረ። ሆኖም ሮማውያኑ ወዲያው ገደሉት። ከግዜ በኋላ ግን አብዛኞቹ ሮማውያን ወደ ክርስትና ሲቀየሩ "በቫለንታይን" ላይ በፈፀሙት ግድያ ተፀፀቱ። ስለዚህም የሞተበትን እለት ለሱ ማስታወሻ በሚል የበዓል ቀን አደረጉት። ይላል።
2ኛ/ ጥንታውያን ሮማውያኑ አንዲት "ዮኖ YoNo" የምትባል አማልክትን ያመልኳት ነበረ። እሷም የአማልክቶቻቸው ሁሉ ንግስት ናት በሚል ፌብሩዋሪ 14ን የሷ መዘከሪያ አደረጉት። እሷንም የሴቶችና የጋብቻ ተምሳሌት ናት በሚል እለቱን የ"ፍቅር ቀን" ኣሉት። ይላል።
3ኛ/ በሮማውያኑ ዘንድ አንዲት ቅድስት ናት በሚል የሚያመልኳት አማልክት ነበረች። ስሟንም "ሊሲየስ Licious" ይሏታል። የሚገርመው ነገር ይህች አማልክት ተኩላ የምትባል እንሰሳ ናት። ተኩላዋን የሚያመልኳት ለምንድነው ከተባለ ጉዳዩ እንዲህ ነው። ይህች "ሊሲየስ" የሮማ ከተማ መስራች የነበሩን ሁለቱን ሰዎች በህፃንነታቸው አጥብታቸው ነበር በሚል አመታዊ ቀንና ቦታ ወስነው የአምልኮ ቦታውንም "ፍቅር" ኣሉት። ይህም ያቺ "ሊሲየስ" የተባለቿ ተኩላ ለእነዚያ ህፃናት ታዝን ነበርና ፍቅር ሰጥታቸዋለች በሚል ይቀድሷታል።
4ኛ/ ከዘመናት በፊት በነበረው የሀገሪቱ መሪ ወንዶችን ለጦርነት ለማሰማራት ማሰባሰብና ማዘጋጀት ሲሳነው ምክንያቱን ሲያጠና ወንዶቹ ከሚስቶቻቸውና ከቤተሰቦቻቸው ላለመለየት ሲሉ ጥሪውን እንዳልተቀበሉና ከሱ ጋር መዝመትን የጠሉ መሆኑን ደረስኩበት ኣለና ለዚህ ጉዳይ መፍትሄ ይሆነው ዘንድ መንግስቱ ከዚህ በኋላ ማንም እንዳይጋባ በማለት አወጀ። በወቅቱ ሰዎች የሚጋቡትም በካቶሊካውያኑ ስርዓት በቀሳውስቱ እጅ በቤተክርስቲያናቱ ነበርና ለቀሳውስቱም ከማጋባት እንዲታቀቡ ትእዛዝ ተላለፈላቸው። ይሁንና "ቄስ ቫለንታይን" የተባለ ሰው ትእዛዙን ባለማክበር ለጋብቻ ወደ ቤተክህነቱ የመጡትን በድብቅ ያጋባ ነበርና ይህንን መንግስቱ ሲደርስበት ያንን ቄስ በፌብሪዋሪ 14/ 269ዓል ገደለው ኣሉ። ስለዚህም ከዚህ ክስተት በኋላ ይህ ቄስ ቫለንታይን ለኛ ፍቅር ሲል ሞተ በሚል ክብር ይገባዋልና አመታዊ መዘከሪያ እናብጅለት ብለው የ"ፍቅር በዓል" ፈጠሩ የሚል ነው።
==∞===∞==
ይህ እንግዲህ ስለ በዓሉ ራሳቸው ፅፈው ያስነበቡት ኣፈታሪካቸው ነው። ይሁንና ከረዥም አመታት በኋላ ቤተክርስቲያኗ የ"ፍቅር ቀን" የሚባለውን በዓሏን "ሊሲየስ" ከምትባለዋ ተኩላ ጋር የሚያያዘውን ታሪክ ትቻለሁ ኣለችና "ቅዱስ" በሚሉት "ቫለንታይን" ላይ ብቻ በማንጠልጠል የ"ቫለንታይንን" ምስሎችና ቅርፃ ቅርፆች በመላው አውሮጳ እና አሜሪካ ከማሰራጨት ጋር በዓሉን አስፋፋች። ሆኖም ለሁለተኛ ግዜ በቅርቡ በእኤአ 1969 የ"ቫለንታይን ቀን" ብላ ታከብር የነበረውንም ትቻለሁ ኣለችና በቤተክርስቲያን ደረጃ ገሸሽ አደረገችው።
በዚህም መሰረት ይህ የ"ቫለንታይን" ቀን የሚባለው በዓል መነሻው ጣሊያን ሮማ ሲሆን ባለታሪኮቹም የሀገሪቱ ቀደምት ነዋሪ የሆኑት ጣዖታውያኑና ሃይማኖት ኣለን የሚሉት ካቶሊካውያን ክርስቲያኖች መሆናቸው ግልፅ ይሆንልናል።
እንደሚታወቀው ሙስሊም ያልሆኑ ህዝቦች ባእድ አምልኮ ላይ የተመሰረቱ በርካታ በአላትን በአመት ውስጥ ያከብራሉ። ከፊሉ በቅዱሳን ስም ሲሆን ከፊሉ ደግሞ ተራ በሆኑ ሰዎች ወይም እንስሳትና ግዑዛን ጭምር ነው። ለዚህማ ማሳያ ይህን የ"ቫለንታይን ቀን" የሚባል በዓል ከተኩላ አምልኮት ጋር ሁሉ የተያያዘ መሆኑን ሙስሊሞቹ ልብ ሊሉት ይገባል። እርግጥ እያመለኩ ያሉት ቅዱስ ሚካኢል ወይም ቅዱስ ጅብሪል ወይም ነቢይን ወይም ሌላ ደጋግ ፍጡራንንም ቢሆን ለአላህ ብቻ የሚገባን አምልኮ ለፍጡር ማዋል በመሆኑ ሁሉም ባእድ አምልኮ ነውና ተቀባይነት የለውም።
እንደሚታወቀው ሮማውያኑ ጣዖታውያን ለፍቅርም፣ ለዝናብም፣ ለአዝርዕትም አምላክ፣ ለብርሃንም፣ ለጭለማም አምላክ፣ ለባህርም፣ ለወንዙም አምላክ እያሉ ለሁሉም ነገር የተለያየ አምላክ እንዳለው አድርገው አማልክትን ያምኑም ያመልኩም ነበረ። ይህንንም ባህላቸውን ወደ ክርስትናው ሲገቡ ክርስቲያናዊ ቃና አላብሰው አስፋፍተውታል።
*
በሶስተኛው ክፈለዘመን በ ሮም ውስጥ በ ከላውዲዎስ ሁለተኛ የንግስና ዘመን የኖረ ቅዱስ ቫለንታይንስ በመባል የሚታወቅ ታዋቂ ቄስ አገልጋይ ነበር። በዚያን ዘመን የነበረው ንጉስ ገላውዲዎስ ሁለተኛ ውሳኔ አስተላለፈ። ውሳኔውም ምን ነበር፤ ያላገቡ ወጣት ወንዶች ሚስት እና ቤተሰብ ካላቸው ወንዶች ይልቅ ጥሩ ወታደሮች መሆን ስለሚችሉ በ እነሱ ላይ ጋብቻን እንዳይፈፅሙ ውሳኔን አስተላለፈ። ይህ የንጉሱ ፍትሃዊ ያልሆነ ውሳኔ ያልተዋጠለት ቄስ ቫለንታይንስ ፍትሃዊ አይደለም ብሎ ያሰበውን የንጉሱን ውሳኔ ባለመቀበል በድብቅ ወጣት ፍቅረኞችን ማጋባቱን ተያያዘው። ነገር ግን ይህ ድርጊቱ በንጉስ ከላውድዎስ ሲደረስበት ንጉሱም ከላውዲዎስ እንዲገደል ትዛዝ አስተላለፈ፡፡ ተገደለ።
★
☞ጥያቄ አለኝ ቀኑ የሚከበረው ቄስ ቫለንታይን የሰሩትን መልካም ስራ ለማሰብ ከሆነ ታዲያ ለምን በቀኑ ሰዎች ትዳር አይመሰርቱም?? ምክንያቱም የቄሱ ስራ ማጋባት ነበር።
☞ቄሱ ፍቅረኛነትን አልነበረም የደገፉት የዘመናችን ሰዎች ግን ከትዳር ውጪ ያለን ጋጠወጥነት ደግፈው ቀኑን በአለም ደረጃ በሴሰኝነት ያከብራሉ።