የማንነትህ መለኪያ፡- አንዳንድ ሰዎች የማንነታቸውን ዋጋ ካለፈው ታሪካቸው፣ ከወቅቱ ኑሯቸው፣ ሰዎች በእነሱ ላይ ካላቸው አመለካከትና ከመሳሰሉት ሁኔታዎች በመነሳት ይወስኑታል፡፡ የማንነታችን ዋጋ ግን ሊጨምርም ሆነ ሊቀንስ የማይችል ጉዳይ ነው፡፡ በማንነቴ ዋጋና በተለጠፈብኝ ተመን መካከል ልዩነት ሲኖር የማንነት ቀውስ ያስከትላል፡፡ ይህ መጽሐፍ በጉዳዩ ላይ ጥልቅ ግንዛቤን ያስጨብጣል፡፡
ከመጽሐፉ የተቀነጨበ . . .
አንተንና ሁኔታህን አስመልክቶ ሁለት ጽኑ ምክሮች
በባህሪህ እንጂ በኑሮህ ደረጃ አትፈር
ሰው ሊያፍርበት ወይም ደግሞ ሊኮራበት የሚገባው ዋነኛ ነገር የባህሪው ሁኔታ እንጂ የኑሮው ደረጃ ሊሆን አይገባውም፡፡ የሰዎች የኑሮ ደረጃ የመበላለጡ ሁኔታ ሊካድ የማይቻል እውነታ ነው፡፡
አንዳንዱ ሰው በገንዘብ የበለጸገ ሲሆን ሌላው ደግሞ የገቢው ምንጭ አናሳ ነው፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ግን፣ ከባለሃብቱም ሆነ ባለሃብት ካልሆነው ሕዝብ መካከል የባህሪይ ድኃም አለ፡፡
በአንጻሩ፣ ከባለሃብቱም ሆነ ባለሃብት ካልሆነው ሕዝብ መካከል የባህሪይ ባለጸጋ ደግሞ ይገኛል፡፡ ስለዚህም ሰው አንገቱን ሊያስደፋውም ሆነ ቀና ብሎ እንዲሄድ ሊያደርገው የሚገባው የባህሪው ጥራት ጉዳይ እንጂ የንብረቱ ብዛት ሊሆን አይገባውም፡፡ የድህነት ሁሉ ድህነት የባህሪይና የስነ-ምግባር ድህነት ነውና፡፡
ምንም ነገር ቋሚ እንዳልሆነ አትዘንጋ
ዛሬ በቁመናው የተመሰከረለት ሰው ብዙም ሳይቆይ የቁመናውን ጊዜአዊነት ወደማወቅ መምጣቱ አይቀርም፡፡ የትናንት ሃብታም የዛሬ ድኃ፣ የትናንት ድኃ ደግሞ የዛሬ ኃብታም ሲሆን እንዳየህ እርግጠኛ ነኝ፡፡ የዛሬ ዝነኛ ወይም ኃይለኛ ነገ ስሙም ላይነሳ ይችላል፡፡ ይህንን የማይለወጥ የሕይወት ሂደት ያልተገነዘበ ሰው አለኝ የሚለውን ነገር ሲያጣ ራሱንም አብሮ ያጣዋል፡፡ የማንነቱን ዋጋ የተመነበት ሁኔታ ሲጎድል፣ ማንነቱም የጎደለ ይመስለዋል፡፡
ሁሉም ነገር ሲለዋወጥ፣ ሲመጣና ሲሄድ፣ አብሮን የሚቆየውና ሁል ጊዜ የምናገኘው ራሳችንን ነው፡፡ ይህንን ማንነታችንን በጥሩ አመለካከትና ብሩህ በሆነ ራእይ በማገዝ ወደ ፊት ካልዘለቅን እንደ ሁኔታው የሚለዋወጥና የትም የማይደርስ ማንነት ይዘን እንቀራለን፡፡
Join us.....
@Ab_book