አጭር ማስታወሻ ስለ ዱዓእ
~
ዱዓእ ተቀባይነት ያገኛሉ ተብለው በሚታሰቡ በላጭ ሰዓቶች ላይ ከፍ ላሉ ጉዳዮች ትኩረት እንስጥ።
* አላህ ቀልባችንን እንዲያስተካክልልንና ዲን ላይ እንዲያፀናን። የነብዩ ﷺ ዱዓእ በብዛት እንዲህ የሚል ነበር፦
يا مُقلِّبَ القلوبِ ثبِّت قلبي على دينِكَ
“አንተ ልቦችን ገለባባጭ ሆይ! ልቤን በዲንህ ላይ አፅናልኝ።”
* በየትኛውም ዲናዊ ጉዳይ ለተሻለው እንዲመራን። ነብዩ ﷺ የሌሊት ሶላታቸውን በዚህ ዱዓእ ነበር የሚከፍቱት
اللَّهُمَّ رَبَّ جِبْرَائِيلَ، وَمِيكَائِيلَ، وإسْرَافِيلَ، فَاطِرَ السَّمَوَاتِ وَالأرْضِ، عَالِمَ الغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ، أَنْتَ تَحْكُمُ بيْنَ عِبَادِكَ فِيما كَانُوا فيه يَخْتَلِفُونَ، اهْدِنِي لِما اخْتُلِفَ فيه مِنَ الحَقِّ بإذْنِكَ؛ إنَّكَ تَهْدِي مَن تَشَاءُ إلى صِرَاطٍ مُسْتَقِيمٍ.
“አንተ የጂብራኢል፣ የሚካኢል፣ የኢስራፊል ጌታ የሆንከው፣ የሰማያትና የምድር ፈጣሪ የሆንከው፣ የሩቁንም የቅርቡንም የምታውቀው አላህ ሆይ!ባሮችህ ሲወዛገቡበት በነበረው ነገር አንተ ትፈርዳለህ፡፡ ከሐቅ ለሚወዛገቡበት ነገር ምራኝ፡፡ አንተ የፈለግከውን ወደ ቀጥተኛው መንገድ ትመራለህና፡፡” [ሙስሊም]
* ወንጀላችንን ምሮ ከእሳት እንዲጠብቀን፣ ጀነትን እንዲያድለን:- የሙስሊም ትልቁ ሃሳብ ጭንቀቱ ይሄ ነው መሆን ያለበት።
اللَّهمَّ إنِّي أسألُك الجنَّةَ وأعوذُ بِك منَ النَّارِ
"አላህ ሆይ! እኔ ጀነትን እለምንሀለሁ። ከእሳትም ባንተ እጠበቃለሁ።"
* የአላህን ይቅርታ ለማግኘት መትጋት። እናታችን ዓኢሻህ ረዲየላሁ ዐንሃ ለነብዩ ﷺ ለይለተል ቀድር መሆኑን ካሰብኩ ምን ልበል ስትላቸው የጠቆሟት ዱዓእ ይሄ ነበር፦
اللَّهمَّ إنَّكَ عفوٌّ، تُحِبُّ العفوَ فاعفُ عنِّي.
"አላህ ሆይ! አንተ በርግጥም ይቅር ባይ ነህ። ይቅር ማለትን ትወዳለህ። ስለሆነም ከኔ ይቅር በለኝ።”
* ለዚክር፣ ለምስጋና፣ ላማረ የዒባዳ አፈፃፀም እንዲወፍቀን
اللهمَّ أعني على ذكرِك وشكرِكَ وحسنِ عبادتِكَ
"አላህ ሆይ! አንተን በማውሳት፣ አንተን በሚመስገን እና አንተን ባማረ መልኩ በመገዛት ላይ አግዛኝ።"
* ለወገኖቻችንም እንዲሁ የጠመሙትን እንዲያቀናልን፣ የሞቱትን እንዲምርልን፣ ለወላጆቻችን እንዲያዝንላቸው፣ በሃገራችን፣ በፊለስጢን፣ በሱዳን፣ በሊቢያ፣ በሌሎችም ቦታዎች መከራ ላይ ያሉትን ከፈተና እንዲያወጣልን፣ ሰላም እንዲሰጠን ዱዓእ ልናደርግ ይገባል።
* ባጠቃላይ በዱንያም በኣኺራም መልካሙን እንዲያድለን ጠቅላይ ጠቅላይ ዱዓኦችን መምረጥ መልካም ነው። ነብዩ ﷺ ያዘወትሯቸው ከነበሩ ዱዓኦች ውስጥ አንዱ እንዲህ የሚል ነበር፦
اللَّهُمَّ رَبَّنَا آتِنَا في الدُّنْيَا حَسَنَةً، وفي الآخِرَةِ حَسَنَةً، وقِنَا عَذَابَ النَّارِ.
"አላህ ሆይ! በዱንያም መልካምን፣ በኣኺራም መልካም ስጠን። ከእሳት ቅጣትም ጠብቀን።"
=
* ቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor* ፌስቡክ፦
https://www.facebook.com/Ibnu.Munewor?mibextid=ZbWKwL* ዋትሳፕ፦
https://whatsapp.com/channel/0029VaA3X1e5kg7BlsJboa2M