ለመረጃ ያህል‼️
ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ግብር የማስከፈያ ምጣኔዎች‼️
በፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 979/2008 መሰረት ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ግብር የማስከፈያ ምጣኔዎች እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የሚከተሉትን ይላል፡-
👉 ከግብር ነፃ ከሆነው በስተቀር ቀጣሪው ለተቀጣሪው በሚከፍለው ማንኛውም የገንዘብ መጠን ላይ ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ግብር ይከፈልበታል፡፡
👉 ቀጣሪ ማለት ተቀጣሪን የቀጠረ ወይም ለተቀጣሪው ደመወዝ የሚከፍል ሰው ነው፡፡
👉ተቀጣሪ ማለት ደግሞ ራሱን ችሎ የሚሰራን የስራ ተቋራጭ ሳይጨምር በሌላ ሰው /በቀጣሪው/ መሪነትና ቁጥጥር ስር ሆኖ አገልግሎት ለመስጠት በቋሚነት ወይም በጊዜያዊነት የተቀጠረ ግለሰብ ሲሆን የድርጅት ዳይሬክተር፣ ወይም በድርጅቱ አመራር ውስጥ ኃላፊነት የተሰጠውን ሌላ ሰው እንዲሁም ተሿሚንና የህዝብ ተመራጭን ጨምሮ የመንግስት ስራ ኃላፊን ያጠቃልላል፡፡
• ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ የሚከተሉትን ይጨምራል፡-
👉 ከሰራተኛው ቅጥር ጋር በተያያዘ ሰራተኛው የተቀበለው የደመወዝ ምንዳ፣ አበል፣ ጉርሻ፣ ኮሚሽን፣ የመልካም ስራ አፈፃፀም ማበረታቻ ስጦታ ወይም ሌላ የአገልግሎት ክፍያ፣
👉 ሰራተኛው ከቅጥር ውሉ ጋር በተያያዘ በዓይነት የሚቀበለው ማንኛውም ጥቅማጥቅም ዋጋ፣
👉 ተቀጣሪው ከስራ ሲቀነስ ወይም ከስራ ሲለቅ ወይም ስራን እንዲለቅ ለማግባባት የሚከፈል ገንዘብን ጨምሮ የስራ ውል በመቋረጡ ምክንያት በፈቃደኝነት፣ በስምምነት ወይም በዳኝነት ውሳኔ መሠረት የተቀበለ ሰው ማንኛውም የገንዘብ መጠን፣
• ቀጣሪው ለተቀጣሪው ከተከፈለው የገንዘብ መጠን ላይ ግብሩን ሳይቀንስ ከራሱ ግብሩን የከፈለ እንደሆነ የተከፈለው ግብር በተቀጣሪው ደመወዝ ላይ ተደምሮ ግብሩ ይሰላል፡፡
ለምሳሌ፡- የ4ሺ 500 ብር ተቀጣሪ ግብር ተቀንሶበት የተጣራ ደመወዙ ይህ ነው፡፡
ይህ ደመወዝ ተራ ቁጥር 4 ላይ የሚያርፍ ሲሆን ስሌቱ፡-
ተቀናሽ ግብር = የወር ደመወዝ x የማስከፈያ መጣኔ - ተቀናሽ ብር
ተቀናሽ ግብር = 4,500 x 20% - 302.50
ተቀናሽ ግብር = 597.50
የተጣራ ደመወዝ = አጠቃላይ ደመወዝ - ተቀናሽ ግብር
የተጣራ ደመወዝ = 4,500 – 597.50
የተጣራ ደመወዝ = 3ሺ 902 ብር ከ50 ሳንቲም (ይህ የጡረታ ተቀናሽን አያካትትም)።
ገቢዎች ሚኒስቴር
@Addis_Reporter @Addis_Reporter