አፋልጉኝ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ



Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций


Репост из: Natnael Mekonnen
የ15ዓመቱ ህፃን ጓደኛውን "ከዛፉ ጋር እጇን አስሬ አንቄ ገድያታለሁ" ቢልም ቤተሰቦቿ አሁንም ፍለጋ ላይ ናቸው።

ከላይ በምስሉ የምትመለከቷት የ14 ዓመት ታዳጊ ዊንታ አስመሮም ትባላለች። በትምህርቷ ጎበዝ፣ በጓደኞቿ የምትወደድ ለእናትና አባቷ የመጀመሪያ ልጅ ስትሆን የስካውትም አባልና አሰልጣኝ ነበረች።

እሁድ ግንቦት13  ላንቻ ከሚገኘው ቤታቸው ጠዋት 1:00ሰዓት አካባቢ ወደ አደይ አበባ ት/ቤት ትሄዳለች፤ እንደተለመደው እስከ 4:00ሰዓት የስካውት ስልጠና ለተማሪ ጓደኞቿ ከሰጠች በኋላ ከት/ቤት ብትወጣትም ወደ ቤት ሳትመለስ የት እንደሄደችም ሳይታወቅ ለቀናት ደብዛዋ ይጠፋል።

እናትና አባት ወዳጅ ጎረቤት ለፍለጋ ቢሰማሩም አየናት የሚል ሰው ያጣሉ። ቤተሰብ ሲጨንቀው የቅርብ ጓደኛዋ ነው የተባለ አንድ ተማሪ ህፃን ልጅ ሲጠይቁት "እኔ አላውቅም ግን ከጠፋች በኋላ በቴሌግራም እንዳወራትና ደህና እንደሆነች ነግሮና አረጋግቶ የተፃፃፉትንም መልዕክት ያሳያቸዋል።

ከቀናት በኋላ ግን ቤተሰብ ስለተጠራጠረና በጣም ስለተጨነቀ ፖሊስ ይዘው በመሄድ እንደገና ተማሪው ጓደኛዋን አጥብቀው ይጠይቁታል።

ለመጨረሻ ጊዜ ከሱ ጋር እንደነበረችና አንድ ወጣት አስፈራርቶ እንደወሰዳት ልጁም እጁ ላይ ንቅሳት ያለበት እንደሆነ ምልክቱን ተናግሮ ቤተሰብ ከፖሊስ ጋር ሆኖ እንደገና ዊንታን ፍለጋ ይጀምራል፤ ግን "እዚህ አየናት"የሚል ሰው ይጠፋል።

የ15 ዓመቱ ህፃን ተማሪ በፖሊስ ቁጥጥር ውስጥ ሆኖ እንደገና ምርመራ ሲደረግበት "የስካውት አባላት ተማሪዎች ልብስ የሚያሰሩበትን የተሰበሰበ ገንዘብ ዊንታ ጋር እንደነበር ያስረዳል።

ያንን ብር ስለተቀበላት ብሩን መልስ እንዳትለው፤ እሁድ አሰልጥና ስትወጣ ደውሎ ቀጥሯት እጇን ከዛፉ ጋር አስሮ በስካርቭ አንቆ እንደገደላት በማግስቱም ቦታው ላይ ተመልሶ ሲሄድ ማስኳንና ሹራቧን ብቻ እንዳየ ይናገራል። በቴሌግራም ተፃፃፍን ብሎ ያሳያቸውም ሁለቱም ስልክ እሱ ጋር ስለሆነ በሁለቱም ፅፌ ነው ይላቸዋል።

ቤተሰብና ፖሊስ ወዲያውኑ ቦታው ላይ ሲደርሱ ለብሳው የነበረ ሹራቧንና ማህተቧን (ከነመስቅሏ) መሬት ላይ ያገኙታል። እናትና አባት ልባቸው ቆስሎ ወዳጅ ጎረቤት መሞቷን አምኖ "ዊንታዬ ብለው እያነቡ ጥቁር ለብሰው ለቅሶ ተቀመጡ። ፖሊስም መሬት ላይ የነበረውንም ትንሽ አጥንት ሰብስበው ይዘው ሄደው ለምርመራ ሰጡ።

ቤተሰብ ተስፋ ቆርጦ ለቅሶ ከተቀመጡ ከ3ቀናት በኋላ ፖሊስ የምርመራው ውጤት እንደደረሰና "አጥንቶቹ የእንስሳት እንጂ የሷ እንዳልሆነ" ተናገሩ። በአነፍናፊ ውሻ ቢፈለግም ምንም አይነት የመሞቷ ማስረጃ ቦታው ላይ ይታጣል።

እናትና አባት ሀዘኑን ረገብ አድርገው ልጃቸውን ፍለጋ በተስፋ እንደገና መንከራተት ጀመሩ፤ አንዴ "ለሰው ሰጠኋት አንዴ ገድያታለሁ" የሚለው ህፃን ተማሪ ጓደኛዋ፥ በፖሊስ ቁጥጥር ውስጥ ሆኖ ምርመራ ላይ ቢሆንም የአይን ማረፊያ ልጃቸውን ያጡት እናትና አባት "በህይወት እናገኛታለን"በሚል ተስፋ ሀዘናቸውን ዋጥ አድርገው በፀሎትና ልመና 16ቀናት ዊንታን ፍለጋ ላይ ናቸው።

ከገደላትስ አስክሬኗን የት አደረገው?

ለፈላጊ ቤተሰቦቿ ጥቆማ ለመስጠት፦

0911873116 - አስመሮም                       
0980441768 - ዛፋ                          
0911760048 - ሚካኤል

(መረጃው ከባይሽ ኮልፌ በጎ አድራጎት ማኅበር ገጽ የተገኘ ነው።)


Репост из: YeneTube
❗️የአፋልጉን ማስታወቂያ❗️
በምስሉ የምትመለከቷት ወጣት እየሩሳሌም ከተማ የምትባል ሲሆን በትላንትናው እለት ግንቦት 06' 2015 ከመኖሪያ ሰፈሯ ቄራ ጎፋ ጀርመን፤በተለምዶ ገና ትምህርት ቤት፤ አካባቢ ጠዋት ላይ ቸርች ለመሄድ እንደወጣች አልተመለሰችም።
ልጃችንን እንድታፋልጉን በእ/ር ርህራሄ እንለምናቹሃለን።
ልዩ ምልክቶች
1_ ቁመት፡ 1:50
2_መልክ፡ ቀይ
3_እድሜ፡ 25
4_ከላይ የለበሰችው፡ ሮዝ ባለ ኮፍያ ጃኬት
5_ከታች፡ ጅንስ ሱሪ
6_ጫማ፡ ጥቁር ሸራ ጫማ
7_ከፊት ጥርሷ አንዱ የወለቀ ነው
8_የአእምሮ እድገት ውስንነት ስላለባት እራሷን በደንብ አትገልፅም
የቤተሰብ ስልክ ቁጥር
1_አቶ ከተማ፡ 0911627318 (አባት)
2_ወ/ሮ አለም፡ 0911059346(ቤተሰብ)
ማንኛዉንም መረጃ በመደወል አሳዉቁን።
በማህበራዊ ድረገፆቻቹህ ሁሉ አጋሩልን።


የስራ መኪናዬን አፋልጉኝ 🤲

ትላንት እለተ ሐሙስ 28 -07- 2015 ዓ.ም ከምሽቱ 3:30 ላይ ገላን ኮንዶሚኒየም አካባቢ ሁለት የፀጥታ አስከባሪ ደንብ ልብስ የለበሱ እና አንድ ሲቪል ልብስ የለበሰ ሦስት ሰዎች ለፍተሻ በሚመሰል መልኩ አስቆሙኝ ። በር ከፍተው በመግባት ፤ ስለት በማውጣት አስፈራሩኝ ። በመቀጠል ከኋላ አንገቴን በገመድ አነቁኝ ። መኪናዬን ሲቪል የለበሰው እያሽከረከረ ወደ ዩኔሳን ጋር በማዞር ገላን እስር ቤቱ ፊለፊት ባለው ፒስታ መንገድ ይዘውኝ ገቡ ። ዉስጥ ባለው እሾክማ አካባቢ ስፍራ ሲደርሱ አፌን አፍነው ፤ እጄን እና እግሬን በማሰር መሬት ላይ ወረወሩኝ ። በመቀጠል የራይድ አገልግሎት የምሰጥባትን የስራ መኪናዬ የሆነቺው ሱዚኪ ዲዛየር ፤ የቀለም አይነት -አይጥማ ፤ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 -B50994 አዲስ አበባ የሆነቺውን ተሽከርካሪን ይዘዋት ተሰውረዋል ።

እናም ወገኖቼ ሆይ አፋልጉኝ ። ማንኛውንም መረጃ ያላችሁ በሚከተሉት የስልክ ቁጥሮች ደውሉልኝ ። አመሰግናለሁ 🙏

👉 0919096819 -ፉሲል በየነ

👉 0913611627 -ብሩክ አቦነህ

👉 0910326269 -ቤዛዊት አባተ

👉 0929098465 -ሙሉቀ በየነ


#ሳራ_ፈይሳ የ15 ዓመት ታዳጊ ናት!ትላንት መጋቢት 21 ቡልቡላ ማሪያም ኮንዶሚኒየም ከሚገኘው ቤቷ 11ሰዓት አካባቢ ወደ ጨፌ ት/ቤት እንደወጣች አልተመለሰችም።
ስትወጣ ነጭ በቀይ ስኩዌር ሸሚዝ፣ ጎመኔ ከለር ጅንስ ሱሪ እና ነጭ በሰማያዊ ስኒከር ጫማ አድርጋ ነበር።
#ሼር በማድረግ አፋልጉን🙏0911822748 /0911024747


ፓስፓርቴን አፋልጉኝ ~ የእናታችሁ የተማጽኖ ድምፅ

#Ethiopia | የተከበራቹ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ!

ሰኞ እለት፣ መስከረም 23 ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ሲልቨር ከለር ቪትስ ከመሻለኪያ ወደ ካሳንቺስ ራይድ አስቁመን ሄደን ነበር።

እኔ እናታችሁ ~ ወ/ሮ አበባ ቦጋለ ኢዶሳ የጣሊያን የመኖሪያ ፍቃድ እና ፖስፖርት ከኋላ ወንበር ጥለን ወረድን።

ይህንን ጉዳይ በሰአቱ ለ6ኛ እና 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ አመልክተናል ::

ይህንን ዶክሜንት ያገኛችሁ ከታች ባለው ስልክ ቁጥሮች እንድታሳውቁን ስንል በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን::

በእነዚህ ስልክ ቁጥሮች ይደውሉልን

ወረታ እንከፍላለን
+251-911-941242 +251-994-462598 +251-911-162801

ትኬት ቆርጬ የምጓዘው ነገ ነበር። ይህንን የእናታችሁ የተማጽኖ መልእክት ሼር በማድረግ አፋልጉኝ።


ተማሪ ለይኩን ብርሃኑ በቦሌ ክፍለ ከተማ በሻሌ ት/ቤት የ10ኛ ክፍል ተማሪ ሲሆን ግንቦት 09/09/2014 ዓ.ም ት/ቤት ልሂድ ብሎ ወጥቶ አልተመለሰም። ወገኖቼ! ይህን post share በማድረግ እንዲሁም
ከታች ያለውን ፎቶግራፍ በመመልከት ያለበትን ቦታ ያያችሁና የሰማችሁ ወገኖች በዚህ ስልክ ቁጥር ደውላችሁ ብታስታውቁኝ ወሮታ ከፋይ ነን።
መ/ር ብርሃኑ መንግሥቱ ፡- 0913582718 /
ፀደይ ደመቀ 0911556811


Репост из: ፊቅር ብቻ ነው መልሴ
አረ ፋልጉልኝ እህቴን


Репост из: ፊቅር ብቻ ነው መልሴ


Репост из: ፊቅር ብቻ ነው መልሴ


Репост из: Dr. Seife | ዶ/ር ሰይፈ
➕➕ የእርዳታ ጥሪ➕➕

🖲 ከላይ በምስሉ የምትመለከቷት ዶ/ር ሰገን ትባላለች፣ በዳግማዊ ሚኒሊክ ፣የህፃናት ስፔሻሊስት ሀኪም። ያቀፈችው የ8አመት ልጇ ሚካኤል ዳንኤል ይባላል

ታሪኩ በጣም የሚያሳዝን ነው

🖲ልጇ በህክምናው( ALL, acute lymphoblastik leukemia )በሚባል የደም ካንሰር ተጠቂ ነው፣ ላለፉት 2 አመት ህክምናውን በሚገባ ሲከታተል  የማገገም ተስፋ ሁሉ እየታየበት ነበር።

🖲ከሁለት ሳምንት በፊት ነው አዲስ የካንሰር እብጠት በዘርፍሬው ላይ ተገኝቶ የካንሰር መጠኑ በአዲስ መልኩ እየተስፋፋ መሆኑ የተነገራት

🖲አሁን ያለው አማራጭ ፣ከጨረር እና ከፀረካንሰር  ህክምና ዉጪ፣ አስቸኳይ የአጥንት መቅኔ ነቀሎተከላ አስፈልጎታል (bonemarrow transplant ይባላል)

🖲ህይ ህክምና ታዲያ አይደለም በሀገር ውስጥ ሊሰራ ይቅርና በውጭ ሀገራት ራሱ በጣም ውድ የሆነ ህክምና ነው ፣በመንግስት ሰራተኛ አቅም የሚቻል አደለም

🖲የቻልነውን ያህል ለመርዳት እየተረባረብን ስለሆነ የተቻላችሁን እንድትረዱን በፈጣሪስም እንጠይቃለን

ፈጣሪ ያክብርልን።

0911862592 ዶ/ረ ሰገን


Репост из: 🎉ሜዳ ሺ🎉
🙏እንኳን ወደ 🎉ሜዳ ሺ ቦት በደህና መጡ. ይህንን ቦት ለዘመድ አዝማድ እና ለጓደኛዎ ሼር በማድረግ በCBE BIRR / ሞባይል ባንኪግ እና በ AIR TIME / ሞባይል ካርድ ገንዘብ መስራት ይችላሉ!

♻️1 ሰው ሲጋብዙ 5.00Birr ያገኛሉ

🔻የእርስዎ መጋበዣ ሊንክ⏬

▶️ https://t.me/Meda_Chat_Bot?start=r0022427902




"ቅቤ፣ ቅቤ።……ቅቤ"

"ባለ ቅቤ"

"አቤት"

"ሁለት ኪሎ ቅቤ ለቅዳሜ አምጣልኝ"

"ኧሺ"

"አደራህን"

"ኧረ ግዴለም፣ ደንበኝነት ለመቼ ነው?"

"አደራህን፣ አደራህን"

"ምን ሆነዋል? ግዴለም ኧያልኮት"

"አደራህን ያልኩህ ለምን ኧንደሆነ አላወከውማ"

"ለምንድነው?"

"ሙዙን ጠቃጠቆ አድርገው"



"ውልብታ" በዓለማየሁ ገላጋይ

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብረሐነ-መስቀሉ ክብረ-በዓል አደረሳችሁ። በዓሉ የሠላም፣ የጤና፣ የደሰታ እንዲሆን ልባዊ ምኞቴ ነው።
መልካም በዓል!


" Inni garuu balleessaa keenyaaf in waraaname, sababii yakka keenyaafis reebamee in caccabsame; nuyi nagaa akka argannuuf inni in adabame, madaa'uu isaatiinis fayyinni nuuf in argame;"
(Isa. 53: 5)

" ንሱ ግና ብሰሪ ገበንና ቘሰለ፡ ብሰሪ ኣበሳና ድማ ተኸትከተ፡ ንሕና ሰላም ምእንቲ ኽንረክብ፡ መቕጻዕቲ ናብኡ ወረደ፡ ንሕናውን ብስምብራቱ ሓዌና።"
(ትንቢት ኢሳይያስ 53: 5)


" But he was wounded for our transgressions, he was bruised for our iniquities: the chastisement of our peace was upon him; and with his stripes we are healed."
(Isaiah 53: 5)

" እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።"
(ኢሳ 53: 5)

የማውቃቹ የምታውቁኝ ውድ የሀገሬ ልጆች መልካም በአል ይሆንላቹ ዘንዳ ተመኘሁ
ከ ሄኒ መሃናይም


Репост из: YeneTube
አፋልጉኝ!!

ስም: ሂወት እንደገና
እድሜ: 13
ሚያዚያ 12 ቀን 2013 ዓ.ም ባህር ዳር ዙሪያ ወረብ ቀበሌ ከቤት እንደወጣች አልተመለሰችም በእለቱ ለብሳው የነበረው ጥቁር ስስ ጃኬት ከላይ ለብሳ የነበረ ሲሆን ፀጉሩዋን ተላጭታለች ቤተሰቦቿ በጣም ተጨንቀናል አባቷ በሽተኛ ሊሆንብን ነው። እባካችሁ አፋልጉን ወረታውን እንከፍላለን
0918004371, 0918585005, 0918340645, 0909857747


☞በፈጣሪ ስም ይዣችሆለሁ ውደ ሁሉም ግሩፕ ላይ #Share ሼር ያድርጉት!
ለቃሊቲ እና አከባቢው ነወሪዎች ይህች ህጻን ጺዮን እድሜዋ የአራት አመት ልጅ ኢትዮ ብሔራዊ ት/ቤት ትምህርት የመጀመሪያውን ቀን ትላንት ጥዋት እንደወጣች አልተመለሰችም፡፡ ያለችበትን የሚያቅ ካለ ህፃኗን ከቤተሰቦቿ በመቀለቀል 'የበኩላችንን እንወጣ ፡፡ መረጃ ካላችሁ በ 0118233880 ይደውሉልን ወይም ትምህርት ቤት አድርሱልን ፡፡ ሼር ሼር


Negash weldesemayat ybalal abate new afalgugn /1983 lay enen weldo new yetfaw yet endale alakm gn bechmchmta yesemahut debrebrhan endehone new 0922121772 yemiyakew kale




አስቾኳይ የእርዳታ ጥሪ ለ እህታችን !!
★ በቅንነት ሼር ሼር ሳያድርጉ እንዳያልፉ

የሕይወት አድን ጥሪ ወገን ለወገን ደራሽ ነውና

#ETHIOPIAN || ሀያት ኢብራሂም ኡመር ትበላለች የ 11class ተማሪ ነች በ ባሌ ጎባ ነዋሪ ስትሆን በደረሰበት ከፍተኛ በሆነ የኩላሊት ህመም ሁለት #ኩላሊቶቹዋ ከጥቅም ውጪ ሆነው ዲያለሲስ እየተደረገላት በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ ትገኛልች ።

ውድ ወገኖች ለእህታችን በሃኪሞች በተነገረው የቀድሞ ጤንነቱ እንዲመለስ ያለው አማራጭ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማድረግ ብቻ እንደሆነ #የኩላሊት ንቅለ ተከላ ለማድረግ ወደ ውጭ ሃገር መሄድ ይኖርበታል ለህክምና በጠቅላላ 2,000,000(ሁለት ሚሊዮን ብር)ያስፈልጋታል ውድ ወገኖች ወገን ለወገን ደራሽ ነውና ለህታችን #ህይወት ለመታደግ የእርዳታ እጆቻቹ እድትዘረጉለት ዘንዳ በፈጣሪ ስም እንማፀናለን መርዳት ባትችሉ እንኳን ለሚረዱ ሰው ሼር በማድረግ እድተባበሩን በአክብሮት እንጠይቃለን!

የበለጠ መረጃ ለማግኘት በስልክ ቁጥር
+251925386501

እንዲሁም ቤተሰቡዋ ጋር

0920942369
0912823605

በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ !! በቅንነት ሼር ያድርጉ

Bank account

ንግድ ባንክ :1000353443147 hayat ebrahim

አዋሽ ባንክ :01425853981500 hayat ebrahim

ኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ባንክ :1000089014135 hayat ebrahim

@PharmacyRxplus


አፋልጉኝ

share አድርጉልኝ

አማን እባላለሁ። ገና ልጅ ነበርኩ 14 አመቴ ከቤት ለመጥፋት አደለም ወጦ ለማደር ጊዜ አልነበረም በዛ በለጋ እድሜየ በቤተሰብ ምክንያት ከደብረ ማርቆስ ወደ አ.አ ቤተሰቦቸን ጥየ ለመሰደድ የሞከርኩት።
ሁሉም ነገር አዲስ ነበር በጣም ያስፈራል ሆድ ባሰኝ ድንገት ባስ ዉስጥ አጠገቤ የተቀመጠች ወይዘሮ አናገረችኝ አላዉቃትም የደብረ ታቦር ነዋሪ ናት አፅናናችኝ ብዙ ነገር ብላ ብር ሰጣ አስተሳሰቤን እና ፍርሀቴን ቀይራ አድራሻዋን ሰጣ ተለያየን ታሪኩ እንደዚህ ነዉ። እና ስልኳ ጠፍቶብኛል እንዳገኛት ብትረዱኝና በአካል አግኝቸ እንዳመሰግናት ብትረዱኝ ወረታዉን እከፍላለሁ።
ዙርያነሽ ትባላለች ደብረ ታቦር ሰፈር 3 አበዉ የሚባል አ.አ አኒሜሽን የሚሰራ ልጅ እና አረብ ሀገር ሴት ልጅ አላት።
የማቀዉ ይሄን ብቻ ነዉ የደብረ ታቦር ልጆች እባካችሁን እርዱኝ

ልትረዲኝ የምትፈልጉ @Heniamann በዚህ መልክት አስቀምጡኝ
ስለምትረዱኝ አመሰግናለሁ

@Afalegugn

Показано 20 последних публикаций.

136

подписчиков
Статистика канала