ኢየሱስ ክርስቶስ በአሮግው ፍጥረት መጨረሻ እና የአዲሱ ፍጥረት መገኛ ምንጭ ነው
Christ Jesus is the last Adam and the second (New) Man.
መፅሐፍ ቅዱስ በ 1ቆሮንቶስ መልዕክት 15፡45 እና 47
ለኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት ስሞችን ይጠቀማል .
1, ኃለኛው አዳም the last Adam
2, ሁለተኛው ( አዲሱ) ሰው the second or New Man
✍️ ሁለቱን መጠሪያዎች በመጠቀም ትልቅ ቁም ነገር መማር እንችላለን።
▸ ኢየሱስ ኃለኛው አዳም( the last Adam) የሚለው መጠሪያው የምድር ቆይታውን፣በመስቀሉ እና በሞቱ የመጀመሪያው አዳም መጨረሻ እና በአዳም የገባው ሃጢአት እና የሀጢአት ውጤቶች ፋፃሜ ያገኙበት ማለት ሲሆን
ሁለተኛው (አዲሱ) ሰው (the New Man) የሚለው መጠሪያው በትንሳኤ የአዲሱ ፍጥረት መገኛ ምንጭ በመሆን አዲሱ ፍጥረት ወደ ህልውና እንዲመጣ አድርጓል።
▸እንዲሁም በ 2 ቆሮንቶስ 5፡17 (2 Corinthians)
ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።
▸በማስተዋል ስናጠናው ማንም በኢየሱስ ሳይሆ ቃሉ የሚለው ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው ይላል ክርስቶስነቱን ደግሞ አብ በሙላት ያረጋገጠው በትንሳኤው ነው። ሐሥ 2፡36..
▸የኢየሱስ መስቀል የአሮጌው ፍጥረት መጨረሻ ሲሆን የክርስቶስ ትንሳኤ የአዲሱ ፍጥረት መጀመሪያ ነው። 2ቆሮ 5፡17.
▸ የኢየሱስ መስቀል ከአሮጌው አዳም እና ከሙሴ ህግ ጋር ላንገናኝ በሞት የተለያየንበት ሲሆን የክርስቶስ ትንሳኤ ከክርስቶስ ጋር ህይወት አግኝተን የአካል ክፍሎቹ የሆንበት ነው።ሮሜ 6, ሮሜ 7፡1-4, አፌ 2፡4-, ኤፌ 5፡30 KJV.
▸ የኢየሱስ መስቀል ሃጥያት የተቀጣበት ሲሆን የክርስቶስ ትንሳኤ ፅድቃችን የተረጋገጠበት እና በእግዚአብሔር ፊት ሃጢአት አልባ የሆንበት ነው።2ቆሮ 5፡21
▸የኢየሱስ መስቀል እርግማን የተወገደበት ሲሆን የክርስቶስ ትንሳኤ በመንፈስ እና በስጋ የተባረክንበት ነው። ገላ 3፡13 , ኤፌ 1፡4
የኢየሱስ መስቀል በሽታ የተወገደበት ሲሆን የክርስቶስ ትንሳኤ የክርስቶስ ጤና ለኛ የተቆጠረበት ነው።ኢሳ53 , 1ጴጥ 2፡24-25.
▸ የኢየሱስ መስቀል ከአዳም ግዛት ጊዜያዊ ከሆነ ከምድር ተስፋ ነፃ የወጣሁበት ሲሆን የክርስቶስ ትንሳኤ ግን ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት ብቁ የሆንኩበት ነው። 1 ጴጥሮስ 1፡3-5፤
▸ የኢየሱስ መስቀል አለቅነት እና ስልጣናት የተሻሩበት ሲሆን። ቆላስይስ 2፡15 የክርስቶስ ትንሳኤ በጠላት ሀይል ሁሉ ላይ ባለስልጣን ለመሆን ስልጣን የተቀበልንበት ነው። ማቴ 28፡18-20,ሉቃ 10፡19
▸ የኢየሱስ መስቀል አባት ከልጁ ከኢየሱስ ፊቱን ያዞረበት የተወው ሲሆን። መዝ 22፡1 የክርስቶስ ትንሳኤ አባት እኛን የተቀበለበት እና አለቅህም ከቶም አልተውህም ያለበት ነው። ዕብ 13፡5
▸ የኢየሱስ መስቀል ኢየሱስ አምላኬ አምላኬ ብሎ የጮኅበት ሲሆን።/ መዝ 22፡1/የክርስቶስ ትንሳኤ አባ አባት ብለን የምንጮህበት የልጅነት መንፈስ የተቀበልንበት ነው። ሮሜ 8፡14-17
ገላ 4፡5-7
▸ የኢየሱስ መስቀል የዘር፣ የነገድ እና የቋንቋ ልዩነት የጠፋበት ሲሆን
የክርስቶስ ትንሳኤ አማኝ ሁሉ አዲስ ፍጥረት እና ሰማያዊ ዜጋ የሆንበት ነው። ራዕ 5፡10-, ፊሊ 3፡20
1 ጴጥሮስ 2፡9-19 (1 Peter)
እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤ እናንተ ቀድሞ ወገን አልነበራችሁም አሁን ግን የእግዚአብሔር ወገን ናችሁ፤ እናንተ ምሕረት ያገኛችሁ አልነበራችሁም አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋል።
ፀጋ እና ሰላም ለሁላችን ይብዛ።
ለሌሎች አካፍሉ
Telegram:
https://t.me/Hiyaw_qalFacebook :
https://m.facebook.com/103351765227313