👆👆
Rabiya said, “I have lost my needle.”
One amongst the people said, “Well, the sun is setting now and it will be very difficult to find the needle. Where has it fallen? That’ll help us narrow down the area on this big road. If we know the exact place, it will be easier to find it.”
Rabiya told them, “It is better not to ask me that question — because, actually, it has not fallen on the road at all. It has fallen inside my house.”
Everyone started giggling as if she was joking. Then a skeptic says out loud, “We always knew that you were a little insane! If the needle has fallen inside the house, then why are you searching for it on the road?”
“For a very simple reason: inside the house there is no light and on the outside a little light is still there,” Rabiya replied.
The people laughed and started dispersing. Rabiya called them back and said, “Listen! That’s exactly what you are doing: I was just following your example. You go on seeking bliss in the outside world without asking the most fundamental question: where exactly have I lost it?”
After a pause, she continues, “You have lost it inside, and yet you are looking for it on the outside for the very same reason — your senses are outward bound, your ears hear sounds on the outside, your hands touch things on the outside. That’s the reason why you are searching outside. For a very long time, I was also just searching on the outside. But the day I searched inwards, I was surprised. That is where I lost it and that is the only place it can be found.”
Source | Osho, Joy: The Happiness that Comes from Within
ከእለታት አንድ ቀን
ታዋቂዋ ሱፍይ ራቢያ “መርፌ ጠፋብኝ” ብላ ትቀውጠዋለች አሉ ። ከሰዎቹም መካከል አንዱ፣ “እሺ አሁን ምን እናድርግልሽ እንደምታይው ፀሀይዋ እየጠለቀች ነው እናም መርፌውን ለማግኘት በጨለማ በጣም ከባድ ነው። ቆይ ግን አንቻ አታስታውሽም የት ነው የወደቀው በዚህ ትልቅ እና ሰፊ መንገድ ላይ ቆይ የቱጋ ብለን እንፈልግ ባይሆን የጣልሽበትን ባታ አስታውሰሽ እገሪን በእርግጥም ባታውን አውቀን እንፈልግ ዘንድ ለኛም ለመፈለግ ቀላል ይሆንልናል ካለበለዝያ እንዲሁ ዝም ብለሽ አታድክሚን ይላታል ።
እሷም “ይህን ጥያቄ ባትጠይቁኝ ጥሩ ነው አለችም እሱም በመገረም ቆይ ለምን አላት ምክንያቱም ፣ እውነቱ ለመናገር በዚህ መንገድ ላይ ጨርሶ አልወደቀብኝም ። ቤቴ ውስጥ ነው የወደቀው አለችው :: ይሄኔ እሱም ከእሱ ጋርም የነበሩ ሁሉ በጣም መሳቅ ጀመሩ። ከዚያም አንድ ድሮም ነገርኛ የሆነ ሰውዬ ጮክ ብሎ “ትንሽ ነካ እንደሚያደርግሽ ድሮም እናውቅ ! ነበር አሁን ደግሞ ባሰብኝ እንዴ ቆይ ምን ነክቱሽ ነው መርፌው ቤት ጥለሽው ታድያ እንደ እብድ መንገድ ላይ ወተሽ አንቻም የምትፈልጊው እኛንም የምታስፈልጊናለሽ ስራ ፈት አላት
እሷም " ጥሩ በጣም አሳማኝ ምክንያቴን ልንገራችሁ እየው እንደምታውቁት በቤቴ ውስጥ ምንም ብርሃን የለም እና ደግሞ እንደምታዬት ውጭው ትንሽ ወገግ ያለ ስለሆነ ነው " ብላ ራቢያ መለሰች ሰዎቹም ከቀድሙው በበለጠ በጣም እየሳቁ ወደ ጉድ ለየላት ማለት ነው ብለው ባለችበት ጥለዋት ወደ ጉዳያቸው መሄድን ጀመሩ ። ራቢያም መልሳ ኑ ኑ “ስሙ! ብላ በጩኸት ጠራቻቸው ። በእርግጥም እኳ እናንተ እየሰራችሁ ያለው ይህንኑ ነገር እኳ ነው። እኔም የእናንተን ምሳሌ እየተከተልኩ ነበር እኳ አለቻቸው ። በጣም መሠረታዊ የሆነውን ጥያቄ መጅመሪያ እራሳችሁን ሳትጠይቁ ከውጭው ዓለም ደስታን መፈለጋችሁን ትቀጥላላችሁ
በትክክል የት ነው የጠፍው ?” ሰላሜ ፣ ደስታዬ ፣ ሀሴቴ
ከጥቃት ዝምም በኋላ ቀጠለች፣ “ውስጣችሁ ነው ያጣችሁት ( ደስታችሁን፣ ሰላማችሁን፣ ሀሴታችሁን ) ነገር ግን እናንተ ውጭ ውጭውን ነው የምትፈልጉት በዚህም ምክንያት የተነሳ - ስሜታችሁ እና አትኩሮታችሁ ጠቅላላ በውጭያዊው ነገሮች ታስሯል ፣ ተወጥሮል እኔም በጣም ለረጅም አመታት ፣ ልክ እንደ እናንተ ነበርኩ ውስጤ የጠፍውን ሰላሜን ፣ ሀሴቴን ፣ ደስታዬን ውጪ ላይ ብቻ እየፈለግኩ ነበር ። ነገር ግን ፣ በእውነት ውስጤን የፈተሽኩ ቀን ተገረመኩ ። ለካ ያጣሁት የምፈልገው ነገር እዚኸው እኔ ጋር ብቻ ነበር የሚገኘው።
💚ውብ አሁን!!
ምንጭ |ኦሾ፣ ደስታ፡ ከውስጥ የሚመጣው ደስታ
@All_WeHaveIsNow@All_WeHaveIsNow