Truth Revolution Ministry


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Telegram


ለማንኛውም ሀሳብና አስተያየት በውስጥ መስመር ያናግሩን @kirubel_christian

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Telegram
Статистика
Фильтр публикаций


ከላይ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ህፃን ያቤፅ ይባላል።እድሜው 14 ሲሆን ከመጀመሪያ ሲወለድ በአንድ ኩላሊት ነበር የተወለደው ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት ያለውም አንድ ኩላሊት ሙሉ በሙሉ ደክሞ የመጨረሻ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በዚህ ምክንያት ወደ ውጪ ሀገር ሄዶ እንዲታከምና በአፋጣኝ የኩላሊት ንቅለ ተከላ እንዲያደርግ በቦርድ ተወስኗል ስለሆነም ቤተሰቦቹ ከአቅማቸው በላይ ስለሆነ ከስር በተቀመጠው የባንክ አካውንትና gofund me የአቅማችሁን እንድታበረክቱ በትህትና እንጠይቃችኋለን።




እንዴት ከፖርኖግራፊ ሱስ ነፃ መውጣት እንችላለን? ክፍል 3

ፀጋና ሰላም ይብዛላችሁ ወንድማችሁ ኪሩቤል ነኝ ይህን ት/ት ሰምታችሁ ለሌሎች ሼር እንድታደርጉ በጌታ ፍቅር እጠይቃችኋለሁ።ተባረኩ!
ለማንኛውም ሀሳብና አስተያየት @Kirubel_Christian

@Amen_Maranata
@Amen_Maranata
@Amen_Maranata
❇️Join and Share❇️


እንዴት ከፖርኖግራፊ ሱስ ነፃ መውጣት ይቻላል ክፍል 3 ዛሬ ማታ ምሽት 3:00 ይለቀቃል።


እንዴት ከፖርኖግራፊ ሱስ ነፃ መውጣት እንችላለን? ክፍል 2

ፀጋና ሰላም ይብዛላችሁ ወንድማችሁ ኪሩቤል ነኝ ይህን ት/ት ሰምታችሁ ለሌሎች ሼር እንድታደርጉ በጌታ ፍቅር እጠይቃችኋለሁ።ተባረኩ!
ለማንኛውም ሀሳብና አስተያየት @Kirubel_Christian

@Amen_Maranata
@Amen_Maranata
@Amen_Maranata
❇️Join and Share❇️


ፀጋና ሰላም ይብዛላችሁ ይህን የመሰረተ-ክርስቶስ ቤተ-ክርስቲያን የዩቲዩብ ቻናል Subscribe በማድረግ በየጊዜው የሚለቀቁ መንፈሳዊ ይዘት ያላቸውን ፕሮግራሞች መከታተል ትችላላችሁ።እግዚአብሔር ይባርካችሁ!

https://youtube.com/@mkcmedia2023?si=vN5QDioQwa0jBV44
https://youtube.com/@mkcmedia2023?si=vN5QDioQwa0jBV44
https://youtube.com/@mkcmedia2023?si=vN5QDioQwa0jBV44


ፀጋና ሰላም ይብዛላችሁ ወንድማችሁ ኪሩቤል ነኝ ሰሞኑን በፖርኖግራፊ ዙሪያ ተከታታይ ትምህርት ማስተማር ከጀመርኩ ወዲህ እኚህን የመሰሉ ብዙ ቴክስቶች በውስጥ መስመር ይደርሱኛል።ቴክስቶቹን ሳነብ ያስተዋልኩት ነገር ቤተክርስቲያን እና ወላጆች እዚህ ነገር ላይ ተገቢውን ትኩረት ማድረግ እንደሚገባቸው ነው።በጀመርነው ትምህርት ብዙ ሰዎች ከዚህ ሱስ ነፃ እንዲወጡ እኔንም ጌታ እንዲረዳኝ ፀልዩ።ተባረኩ መልካም ምሽት!


#አንደራደርም
#አትደራደሩ
{ይነበብ፦ሮሜ 8÷28-39}
ሁላችንም በህይወታችን የምንደራደርባቸው አልያም ደግሞ ከሚገጥመን ሁኔታ አንፃር አቋማችንን/ውሳኔያችንን የምንቀይርባቸው ብዙ ነገሮች አሉን።ነገር ግን በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ብናልፍ አቋማችንን የማንቀይርበት ወይም የማንደራደርበት አንድ ነገር አለ ይህም ከአምላካችን እግዚአብሔር እንዲሁ በነፃ የተቀበልነው የዘላለም ህይወት ስጦታ ነው።ይህን ስጦታ የተቀበልነው በነፃ ቢሆንም ዋጋው ግን እጅግ ውድ ነው ምክንያቱም በጌታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ የመስቀል ስቃይ የተገኘ ነውና።ስለዚህ ይህ ታላቅ ስጦታ ሊቀልብን አይገባም።እንደ ሙሴ ምቾትን ትተን ብንሰደድ፣እንደ አብርሃም የፀሎት መልሳችን ቢዘገይ፣እንደ ይስሐቅ ሰዎች ቢገፉን፣እንደ ዮሴፍ የቅርብ በምንላቸው ሰዎች ብንገፋ፣እንደ ኢዮብ ብንታመም፣እንደ ዳንኤል በአንበሳ ጉድጓድ ውስጥ ብንጣል፣እንደነ ሲድራቅ ሚሳቅና አብደናጎ በእቶን እሳት ውስጥ ብንጣል፣እንደ ዲያቆን እስጢፋኖስ በድንጋይ ብንወገር፣እንደ ሐዋሪያቱ ብንገረፍና ብንታሰር፣ልጆቻችን ቢታመሙ፣በጣም የምንወዳቸው ሰዎች በሞት ቢለዩን፣ቢርበን፣በማጣት ውስጥ ብናልፍ፣ነገሮች/ሁኔታዎች እንዳሰብነው ባይሆኑልን፣በአጠቃላይ ብዙ መከራና ችግር ውስጥ ብናልፍ ባገኘነው የዘላለም ህይወት አንደራደርም።እኚህ ከላይ የተዘረዘሩት ነገሮች በሙሉ ከጌታ እቅፍ ወጥተን ወደ ኋላ እንድናፈገፍግ(ልባችን እንዲሸፍት) ምክንያት ሊሆኑን አይገባም።በዚህ ሁሉ ግን ሐዋሪያው ጳውሎስ እንደተናገረው(2ተሰ 3÷3) በእምነታችን የሚያጸናን ከክፉውም የሚጠብቀን ጌታ የታመነ ነው።አሜን!✍ #Kirubel

@Amen_Maranata
@Amen_Maranata
@Amen_Maranata
❇️Join and Share❇️


እንዴት ከፖርኖግራፊ ሱስ ነፃ መውጣት ይቻላል? ክፍል 1

ፀጋና ሰላም ይብዛላችሁ ወንድማችሁ ኪሩቤል ነኝ ይህን ት/ት ሰምታችሁ ለሌሎች ሼር እንድታደርጉ በጌታ ፍቅር እጠይቃችኋለሁ።ተባረኩ!

@Amen_Maranata
@Amen_Maranata
@Amen_Maranata
❇️Join and Share❇️


#ይነበብ #ይነበብ #ይነበብ
#ለሀገራችን_ኢትዮጵያ_አጥብቀን_እንፀልይ

ትላንት ማታ ያየሁትን ራዕዪ ከተመለከትኩ በኋላ መልሼ ለመተኛት ብዙ ተቸግሬ ነበር።ያየሁት ምን መሰላቹ ቦታው አዲስ አበባ ሲሆን ጊዜው ደግሞ ቀን አከባቢ ነበር። #ከሰሜን_አቅጣጫ_ከሀገር_ውጪ የሚነሱ ዘመናዊ የጦር ጀቶችን ተመለከትኩ።እነዚህ የጦር ጀቶች የሚጥሏቸውን ቦምቦች ይዘው ወደ አዲስ አበባ ከተማ ይመጡ/ይበሩ ነበር።ወዲያውም የያዟቸውን ቦምቦች መጣል ጀመሩ፤ከተማዪቱም ከወደቁባት ቦምቦች የተነሳ መፈራሪስ ጀመረች፣የከተማዪቱም ነዋሪዎች ህይወታቸውን ለማዳን ወዲህና ወዲያ ማለት ጀመሩ።ይህን ራዕዪ እንደተመለከትኩ በመደንገጤና በመፍራቴ ወዲያውኑ ከእንቅልፍ ነቃሁኝ።ወንድሞችና እህቶች እባካችሁ አጥብቀን እንፀልይ፤በሀገራችን የእግዚአብሔር ፈቃድ ብቻ እንዲሆን አጥብቀን እንፀልይ።ወንድማችሁ ኪሩቤል ነኝ ተባረኩ።

@Amen_Maranata
@Amen_Maranata
@Amen_Maranata
❇️Join and Share❇️


ዘመን ተሻጋሪ የእምነት አቋማችን
እኔ ሁሉን በሚችል ሰማይንና ምድርን በፈጠረ በእግዚአብሔር አብ አምናለው።ደግሞም በአንድ ልጁ፣በመንፈስቅዱስ በተፀነሰ፣ከድንግል ማሪያም በተወለደ፣በጴንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን መከራን በተቀበለ፣በተሰቀለ፣በሞተና በተቀበረ፣በሶስተኛውም ቀን ከሙታን በተነሳ፣ወደ ሰማይም በወጣ፣ሁሉን በሚችል በእግዚአብሔር አብ ቀኝ በተቀመጠ፣ከዚያም በሕያዋንና በሙታን ሊፈርድ በሚመለስ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምናለው።ደግሞም በመንፈስቅዱስ፣በአንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን፣በሃጢአት ስርየት፣በስጋ ትንሳኤ፣በዘላለም ህይወት አምናለው።አሜን!

         @Amen_maranata
         @Amen_maranata
         @Amen_maranata
        ❇️Join and Share❇️


#እውነተኛ_ወዳጅ
ይሁዳ በሠላሳ ብር አሳልፎ እንደሚሰጠው ጴጥሮስ ደግሞ ሦስት ጊዜ እንደሚክደው ኢየሱስ ቢያውቅም ለእነርሱ የነበረው ፍቅር ግን አልቀነሰም/አልተለወጠም።ይህ ሁሉ ከመሆኑ በፊት የሁለቱንም እግር በማጠብ ፍቅሩንና ትህትናውን ገልጦላቸዋል።ወደፊት እንደምንደክም እያወቀ ዛሬ ግን በፍፁም ፍቅሩ የሚወደን እውነተኛ ወዳጅ አለን።መልካም ምሽት! ✍️ #Kirubel

@Amen_maranata
         @Amen_maranata
         @Amen_maranata
        ❇️Join and Share❇️


ምን አይነት ዝማሬ ነው🔥

ይህን ድንቅ መዝሙር ጋበዝኳቹ ሁላችሁም ስሙት።ፀጋና ሰላም ይብዛላችሁ!

         @Amen_maranata
         @Amen_maranata
         @Amen_maranata
        ❇️Join and Share❇️


ከፖርኖግራፊ ሱስ እንዴት መውጣት ይቻላል?
How to overcome Pornography?

የክርስቶስ ፀጋና ሰላም ይብዛላችሁ ኪሩቤል ነኝ ከላይ ባለው ርዕስ ትምህርት እያዘጋጀሁኝ ነው።ጌታ ቢፈቅድና ብንኖር ከጥቂት ቀናቶች በኋላ ትምህርቱን የማካፍላችሁ ይሆናል።ተባረኩ!

         @Amen_maranata
         @Amen_maranata
         @Amen_maranata
        ❇️Join and Share❇️


ክርስቶስን ከተውከው ከቀንህ ላይ ፀሀይን እንደማውጣት፤ከለሊትህም ላይ ጨረቃን እንደማንሳት፤ከባህር ውስጥ ውሃን እንደማጥፋት፤ከወንዝ ውስጥም ጓርፍን እንደመተው፤ከእርሻህ ላይ ሰብልን እንዳለመሰብሰብ፤ከስጋ ውስጥ ነፍስን እንደማውጣት፤ከመንግስተ ሰማያት ውስጥ ሃሴትን እንደማጣት፤ሁሉን ተዘርፎ እንደማጣት ነው።
ቻርለስ ስፐርጅን

      @Amen_maranata
         @Amen_maranata
         @Amen_maranata
        ❇️Join and Share❇️


#ሉዓላዊ_አምላክ!
እግዚአብሔር ጻድቅ አምላክ ነው፤
ለምን? አይባልም።የጠየቅነውን ሲሰጠን ልክ ነው ሲነሳንም ደግም ልክ ነው።እርሱ በስራው የማይሳሳት፤በነገር ሁሉ ትክክል የሆነ ቅዱስ አምላክ ነው።መልካም ምሽት! ✍️ #Kirubel

        @Amen_maranata
         @Amen_maranata
         @Amen_maranata
        ❇️Join and Share❇️


#ታማኝ_አምላክ!
እግዚአብሔር መቼ ኪዳኑን አፈረሰ? አብርሃም እይደል እንዴ ኪዳኑን ዘንግቶ በሚስቱ ምክር ወደ አጋር የገባው? እግዜር ግን ታማኝ ስለሆነ ዳግመኛ እድልን ሰጠው፤የገባለትን ኪዳን እስከመጨረሻው አፀናው።የእግ/ርን ቀን በትዕግሥት መጠበቅ ምነኛ መታደል ነው! መልካም ምሽት ✍️ #Kirubel

@Amen_maranata
         @Amen_maranata
         @Amen_maranata
        ❇️Join and Share❇️

Показано 17 последних публикаций.