Фильтр публикаций


በብርሸለቆ ጊዚያዊ መሰረታዊ ዉትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት 129ኛዉ የአድዋ ድል በአል በድምቀት ተከብሯል።

በስልጠና ላይ የሚገኙ የ33ኛ ዙር ምልምል ፖሊሶች 129ኛውን የአድዌ ድል መታሰቢያ በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች አክብረዋል።
ዕለቱን አስመልክቶ በተሰናዳው ዝግጅት ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአማራ ፖሊስ ኮሌጅ ምክትል ዋና ዳሬክተርና የ33ኛ ዙር የስልጠና አስተባባሪ ኮማንደር አብዩት ሽፈራዉ አባቶቻችን የጣሊያንን ወራሪ ያምበረከኩት በአንድነትና በነደደ ሀገራዊ ፍቅር በመሆኑ ለጥቁር ህዝቦች ኩራት የሆነውን ድል ያስመዘገቡበትን መንገድ ለመከተል አንድነታችንን በማጠናከር ሊሆን ይገባል ብለዋል።
የዝግጅቱ ተሳታፊ ሰልጣኞች በበኩላቸው በክልላችን የተፈጠረውን የዘረፋና የዉብድና ሀገር አፍራሽ ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አከርካሪውን በመስበርና በማስወገድ ታፍራና ተከብራ የምትኖረዉን ታላቋን ሀያል ሀገር ኢትዮጵያን ለማፅናት የሚጠበቅብንን ታሪካዊ ኀላፊነት እንወጣለን ብለዋል።

በአዓሉ በተለያየ ትሪዒት ድራማና ስነ ፅሁፍ በድምቀት ተከብሯል።

ዘገባው ፦ የአማራ ፖሊስ ኮሌጅ የህዝብ ግንኙነት ነው።

ከብርሸለቆ


በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ወገራ ወረዳ ነፍጥ አንስተው ሲዋጉ የነበሩ ታጣቂዎች የመንግስትን የሠላም ጥሪ ተቀብለው ወደማህበረሰቡ ተወላቅለዋል።

የወገራ ወረዳ ሠላምና ደህንነት ኃላፊ አቶ ደሴ አስናቀው በምህረት የገቡ ተዋጊዎችን በተቀበሉበት ወቅት እንዳሉት መገዳደል ይብቃ ህዝባችን ስቃዩ በዝቷል ሰላሙን አግኝቶ በሙሉ አቅሙ ወደ ልማት ሊገባ ይገባል ያሉ ሲሆን ይህ የሚሆነው ደግሞ ጫካ የገቡት ሁሉም አካላት መንግስት እያቀረበ ያለውን የሰላም ጥሪ ተቀብለው መምጣት ሲችሉ ነው ብለዋል፡፡

ይህ እንዲሆን የፀጥታ አካላትና የሀገር ሽማግሌዎች ጥረት ከፍተኛ ነበር ያሉት ኃላፊው በዚህም አስራ ስምንት(18)የሚሆኑ ታጣቂዎች በሰላም ወደ ማህበረሰቡ የገቡ ሲሆን ከዚህ ውስጥ አስራ ሦስት የሚሆኑት እስከ ሙሉ ትጥቃቸው ተቀላቅለዋል ነው ያሉት።

አሁንም ሌሎች ተዋጊዎችም የመንግስትን የሠላም ጥሪ በመቀበል ምህረት እንዲገቡ ነው ኃላፊው ጥሪ ያቀረቡት ።

መረጃው፦የወገራ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን ነው።


"ወረዳዎች እና ከተሞች ዘላቂ ሰላማቸውን እንዲያሰፍኑ እየተሠራ ነው" አሕመዲን መሐመድ (ዶ.ር)

በደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር እና በሰሜን ሸዋ ዞን ያለውን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ለማጽናት ያለመ ምክክር በደብረ ብርሃን ከተማ እየተካሄደ ነው።

በውይይቱ ላይ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ዘርፍ አስተባባሪ እና የአማራ ክልል የከተማ እና መሠረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አሕመዲን መሐመድ (ዶ.ር) አካባቢው በጸጥታ ሥራው ራሱን በመቻል ምዕራፍ ላይ የሚገኝ መኾኑን ተናግረዋል።

"ወረዳዎች እና ከተሞች ዘላቂ ሰላማቸውን እንዲያሰፍኑም እየተሠራ ነው" ብለዋል። ክልሉ ቀደም ሲል ባከናወናቸው ተግባራት የጸጥታ መዋቅሩን በማጠናከር ሰላም የማስፈን ሥራ በሰፊው ሠርቷል ነው ያሉት።

በሀገር መከላከያ ሠራዊት የኮማንዶ እና አየር ወለድ እዝ አዛዥ እና የማዕከላዊ ሸዋ የሰላም ካውንስል ሰብሳቢ ሌተናል ጀኔራል ሹማ አብደታ በጸጥታ አካላት ጠንካራ ቅንጅታዊ አሠራር እየተተገበረ መኾኑን ገልጸዋል።

በውይይቱ የመከላከያ መኮንኖች፣ የዞን፣ የከተማ አሥተዳደር እና የወረዳ መሪዎች ተገኝተዋል።(አሚኮ)


በሰሜን ጎንደር ዞን የፅንፈኛው አመራሮች እና ታጣቂዎች የሰላም አማራጭ በመምረጥ እጃቸውን ሰጡ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በሰሜን ጎንደር እና በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ዳባት ፣ወገራ ወረዳና አካባቢው ራሳቸውን በብርጌድ አደረጃጀት ሰይመው ሲንቀሳቁሱ የነበሩ የፅንፈኛው ቡድን አመራሮች እና አባላቱ ለሰሜን ምዕራብ ዕዝ ኮር የሠራዊት አባላት እጃቸውን ሰጥተዋል።

አበበ ገዳሙ እና አዲሰ አዘዘው የተባሉ አመራሮች ከነ አባላቶቻቸው በሰላም እጃቸውን ለሠራዊቱ የሰጡት በማዕከላዊ ጎንደር በአካባቢው ኮማንድ ፓሰት ከህግ ማስከበር ተልዕኮው ጎን ለጎን ሰላምን ለሚፈልጉ ሃይሎች ምህረቱ የሰጠውን የሰላም ጥሪ በጊዜው እንዲጠቀሙ በፈጠረው ምቹ የሰላም መንገድ መሆኑን ገልፀዋል ።

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ተሰማርቶ የሚገኘው ክፍለጦር በአካባቢው የሚገኘውን ፅንፈኛ ሀይል እየደመሰሰ የአካባቢውን ሰላም እያረጋገጠ ይገኛል ሲሉ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ክፍለጦር አዛዥ ኮሎኔል ስንታየሁ ሰይድ ተናግረዋል።

ክፍለ ጦሩ በተሰጡት የግዳጅ ቀጠናዋች ሁሉ ህዝባዊ ፍቅሩን ሳያላላ ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ተናቦ በመሰራት ፅንፈኛ ሀይሉን የገባበት ገብቶ በመምታት እና እጅ የሰጡትን በሰላም በመቀበል ግዳጅን በብቃት እየተወጣ እንደሚገኝ ዋና አዛዡ አሰረድተዋል።

ህዝቡ በቡድኑ በየጊዜው የሚደርስበትን የመብት ጥሰት እየተረዳን ሲመጣ እና ህዝቡ ከእኛ እየራቀ ድጋፍ አልባ መሆናችን ሲገባን የሰላም ጥሪውን ተቀብለን ከህብረተሰባችን ጋር በይቅርታ ተቀላቅለን ለመሰራት በሰላማዊ መንገድ እጃችንን ሰጥተናል ነው ያሉት።


በአባድራ አካባቢው ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የፅንፈኛ ቡድኑ አባት በቁጥጥር ሥር ውለዋል።

ራሱን ፋኖ ብሎ የሚጠራው የፅንፈኛው ቡድን በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞኖ ዳንግላ ወረዳ በተለያዩ ቀጠናዎች በመንቀሳቀስ የህዝብን ንብረት ከማውደሙ በተጨማሪ የህብረተሰቡን ሰላም በማወክ እረፍት እያሳጣ የነበረው ሃይል የመከላከያ ሰራዊትና የአካባቢው የፀጥታ ሀይል ባደረሰበት ጥቃት እየተደመሰሰ እና እጅ እየሠጠ ይገኛል።
ሰራዊቱ በአባድራና አካባቢው በአካሄደው አሰሳ በርካታ የፅንፈኛ ቡድኑ አባላት ከወረዳው ተቋማት የዘረፋቸውን ቁሣቁሶችን ጨምሮ ልዩ ልዩ የጦር መሣሪያዎን ከፅንፈኛ ቡድኑ መማረክ ችላል።
ፅንፈኛ ቡድኑ የኔ በሚለው ህዝብ ላይ ያደረሰው ግፍና በደል ታሪክ የማይሽረው ጠባሳ በመሆኑ ቡድኑ ወደ ሰላም እንዲመጣና የወረዳው ህዝብ የሰላም አየር እንዲያገኝ ሁሉም አበክሮ ሊሰራ ይገባል።
መረጃው፦የአዊ ብሄረሰብ ዞን ፖሊስ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ነው።


የሰላም አማራጭን አልቀበልም ባለው ጽንፈኛ ቡድን ላይ አስፈላጊው እርምጃ ተወስዷል!

በደቡብ ወሎ ዞን "አካባቢያችንን ከጽንፈኛ አጸዳለሁ የአማራን አንድነት በማስቀጠል ኢትዮጵያን አጸናለሁ በሚለው" ህግ የማስከበር ዘመቻ ውጤት እየተመዘገበ ይገኛል።

በደቡብ ወሎ ዞን በደላንታ ወረዳ ፀሀይ መውጫ በተባለው አካባቢ በጥምር ጦሩ በተወሰደው ህግ የማስከበር ዘመቻ ሰላም ጠል በሆነው ጽንፈኛ ቡድን ላይ የማያዳግም እርምጃ መወሰዱን በሀገር መከላከያ ሰራዊት የ801ኛ ኮር ምክትል አዛዥ ኮሎኔል አዲሱ በድሩ ገልጸዋል።

የ801ኛ ኮር ምክትል አዛዥ ኮሎኔል አዲሱ በድሩ በጥምር ጦሩ በተደረገው ህግ የማስከበር እርምጃ በርካታ የጽንፈኛ ቡድን ሙት እና ምርኮኛ ሲሆን ዲሽቃ፣ ብሬን፣ ስናይፐር፣ ክላሽ፣ የቃታ መሳሪያና በርካታ ጥይቶች እንዲሁም ቦንብ ጭምር መማረኩን አስታውቀዋል።

መንግስት የሰጠውን የሰላም አማራጭ አንቀበልም በሚሉ ሰላም ጠል ጽንፈኛ ቡድኖች ላይ በጥምር ጦሩ ህግ የማስከበር ዘመቻ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አስታውቀዋል።

አሚኮ


"ምስራቅ ዕዝ በጎጃምና በደቡብ ጎንደር የፅንፈኛውን ሃይል አከርካሪ በመስበር አስተማማኝ ሰላም አሥፍኗል!" ሌተናል ጄኔራል መሃመድ ተሰማ

ምስራቅ ዕዝ አገራዊ ተልዕኮውን አንግቦ በአማራ ክልል ፅንፈኛውን ሽባ በማድረግ ሰላም እያስፈነ ያለና በኢትዮጵያ ምስራቅ ቀጠናም የሸኔን እና የአልሸባብን ሴራ በማክሸፍ ግዳጁን በውጤት እየፈፀመ እንደሚገኝ የምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል መሐመድ ተሠማ አረጋግጠዋል።

የምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ፣ሰሞኑን በባህርዳር ከተማ ከዕዝ ኮማንድ ፣ ከኮር አዛዦች ፣ከክፍለጦር አመራሮች እና ስታፍ ከፍተኛ መኮንኖች ጋር በነበረ መድረክ ላይ እንደተናገሩት ፣ ዕዙ የፅንፈኛውን አከርካሪ በመስበር በክልሉ ተደቅኖ የነበረውን አገር የማፍረስ ተግባር ቀልብሶታል።

ዕዙ በአሁኑ ሰዓት በፅንፈኛው ላይ ከፍተኛ ምት በማሳረፍ ሰብዓዊና ማቴሪያላዊ ኪሳራ በማድረስ በክልሉ ህግን የማስከበር ተልዕኮውን በውጤት እየተወጣ ይገኛልም ሲሉ ገልፀዋል።

ዕዙ በፈፀማቸው ገድሎች የፅንፈኛውን ሴልና ሃብት በመያዝ ፣ የመስተዳድር አካላት እግር አንዲተክሉ በማድረግ የፀጥታ ሃይሉን በማሰልጠንና በማደረጀት ጥሩ ውጤት አስመዝግበናል ብለዋል።

ጄኔራል መኮንኑ የፀረ-ሽምቅ የውጊያ ስልቶችን በመጠቀም ፅንፈኛውን ሃይል አሰላለፍ በማዛባት ቆሞ የመዋጋት አቅሙን አሳጥተነዋል ነው ያሉት።

ምስራቅ ዕዝ በአገሪቱ ምስራቃዊ አካባቢዎች ላይም ተሰማርቶ የሸኔን ድርጊት በንቃት እየተከታተለና በቦርደር አካባቢዎችም አልሸባብ ሾልኮ ወደ ዉስጥ እንዳይገባ በማድረግ ግዳጁን እየተወጣ መሆኑን ጠቁመው በቀጠናው ህገ-ወጥ የሰዎችና የጦር መሳሪያ ዝውውርን በመቆጣጠር አመርቂ ተግባራትን ፈፅሟል።

አመራሩ ሠራዊቱን በሰላም ጊዜ በማዘጋጀት፣ የዕለት ከዕለት ግዳጁን ለሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ በመጠቀም ለቀጣይ ግዳጅ ሠራዊቱን የበለጠ በማዘጋጀት ሃላፊነቱን መወጣት እንደሚገባውም አሳስበዋል።

አመራሩ ያልተቋረጠ የሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ በማድረግ ሰራዊቱ አካላዊ፣ ቴክኒካዊና ሙያዊ ብቃቶችን በማጎልበት ከሁኔታዎች ጋር ተጣጣፊ በመሆን ድልን የበለጠ ማጎልበት እንደሚገባ ማስገንዘባቸውን መከላከያ ሰራዊት በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስነብቧል።





Показано 9 последних публикаций.