...
... የሠፈር ሳተና ብላቴና ሳለን፤
... ያኔ በልጅነት በየዋሁ ዘመን
... ድብድብን እንጂ ጥላቻን መቼ አውቀን?
...
... "እችለዋለሁኝ" እየተባባልን፤
... ስንቱ ጋር ጀግነን እየተጋጠምን
... ኮሌታ ጨምድደን እየተናነቅን፥
... በማግስቱ በፍቅር እንዳልተቃቀፍን፥
... በቀጣዩ ቀን ግን...
... አባረን... አባረን... አባረን ካቃተን
ድንጋዩን ወርውረን - ከኋላ ፈንክተን - ደም እያፈሰስን፥
ቤትም ስንገባ... "ጠግበሐል" ተብለን - እየተገረፍን፤
...
... ደግሞ በማግስቱ ተፈንካችን አቅፈን...
... አብረን ባንድ ቡድን
... አኩኩሉ፣ አባሮሽ እየተጫወትን፤
...
... ደግሞ በሳምንቱ...
... ቦቸራ አለቃችን ኳስ ሜዳ ሰብስቦ...
... "ትችለዋለህ!?" ሲል - አንዱን ልጅ አስቁሞ፥
... "ባ'ናቱ ይዘቅዘቅ" እንዳላላን ከርሞ
... አጅሬ... ካቅማችን በላይ ሆኖ እየተገኘ፥
... በቴስታ ነርቶን ቢፈሰንም ነስር፥
... ባ'ናታችን ቆመን ብንወድቅም ከስር
... በንዴትና እልህ እያለቃቀስን
... "ሰኔ 30" እንገናኝ - ብለንም ብንቀጥር፥
... በንፁህ ልባችን መቼ ቂም ቀበርን?
...
... ብንችልም ባንችልም
... በፍቅር ውስጥ ነው .. የተደባደብን።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
------------ (ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ)
...ደማቅ ቀን ይሁንልን!!💚💛❤
💚 https://t.me/Asresee
💛 https://t.me/Asresee
❤ https://t.me/Asresee