አንዳንድ ጊዜ...በሰው ሰውኛው ስናስበው መሆን የሚገባው ቀርቶ መሆን የማይገባው ሲሆን እናያለን... ጉዳዩ ከአቅማችን በላይ ይሆንና ከመገረምና ከመደነቅ አልፈን የምንፈጥረው ምንም ነገር አይኖርም
ሰው ሆነን የተፈጠርን ቀን ከሀቁ ጋር ተሳስረናል፡፡
የእኔና ያንት ገዢ መሬት /common ground/ ሰውነት ይባላል፡፡
ህግ የምናወጣውም፤ ህግ የምንሽረውም እሱ ላይ ቆመን ነው፡፡ ክፋት፣ ደግነት፣ ትክክል፣ ስህተት፣ ተበዳይ፣ በዳይ የምንባባለውም እሱ ላይ ቆመን ነው፡፡ ወደድንም ጠላንም፤ ከሳንም፣ ወፈርንም ሁላችንም ሰው በሚባል ቁና እኩል ተሰፍረናል፡፡
መበላለጡ የመጣው ከዛ በኃላ ነው፡፡
ስለዚህ እሱ ላይ ቆመን እናውራ ….. በየትኛውም የሰው ገበያ መነፅር ከዓይን በላይ ዋጋ ኖሮት አያውቅም፡፡
ቆዳችን የተሰራው ከልብሳችን በፊት ነው፤ ጭንቅላት ኮፊያን ይበልጠዋል ፤ ጫማ የተሰራው ከእግር በኃላ ነው.
*
#ሰው_መሆን_ይበልጣል✌️
"እንከባበር" ብሏል ዘፋኙ😉
@be_your_selffff