Фильтр публикаций


ህንድ ውስጥ 234 ብሔሮች፤ቻይና ውስጥ 499 ብሔሮች፤ፓኪስታን ውስጥ 404 ብሔሮች ይገኛሉ።እያንዳንዳቸው ብሔሮች የራሳቸው ቋንቋ፤ባህል፤ታሪክ፤ማንነት አላቸው ግን ሁሉም ለሀገራቸው ልዩ ፍቅር አላቸው።በመተሳሰብ፤በአብሮ መኖር፤በፍቅር ያምናሉ!የሁሉም ነገር ማሰሪያ ውሉ ፍቅር ነው የሚለውኔ በማመን ይተገብራሉ

📘ርዕስ፦በኢያሪኮም ጩኸት በዛ
✍️ደራሲ፦አዘርግ

📚 @Bemnet_Library

4.5k 0 18 12 131

#PaidPromotion

🚀 IAT Student Event Alert! 🚀
🎤 Hosted by In Africa Together (IAT)

✅ Licensed in 🇺🇸 Michigan, USA & 🇪🇹 Addis Ababa, Ethiopia 

Exclusive Offer for High School Students!✨ 
🎉 Enjoy a 10% discount just bring your High School ID!

📅 Date: Sunday, February 9
📍 Venue: Kaleb Hotel (Next to Harmony Hotel) 
Time: 2:00 AM – 8:00 AM (Local Time) 
 
🎓 No Pre-Payment Required
📜 No English Proficiency Exam
✅ 100% Admission Guarantee


🇺🇸 USA – 66% Scholarship + 34% Covered by Student Loan
🇨🇳 China – Full Scholarship + Pocket Money Allowance

🎯 Apply for: 
- Bachelor’s Degree 
- Master’s Program 
- PhD Programs 

📦 Our Packages Improve Your Visa Chances!

🔗 Secure Your Spot – Register Now!👇🏾 
https://forms.gle/aWzxNFkQJS8ozaLU7


ሙና ሕይወት አይደለችም። የሕይወት አንድ ክፍል ናት። ሕይወት እንደ ሀገር ብትሆን ...... ፍቅረኛ፣ ስራ፣ ትምህርት፣ መዝናናት፣ ሃዘን፣ ደስታ፣ ቤተሰብና የመሳሰሉት ብሔር ብሔረሰቦች ናቸው።

አገርን ለማቆም እኩል ድርሻ ካላቸው ነገሮች እንቅልፍም አንዱ ነው። ሙና የምትባል ብሔር እንቅልፍ ለሚባል ብሔር ክብር ሊኖራት ይገባል።

📚ርዕስ፦ ዙበይዳ
✍️ፀሃፊ፦ አሌክስ አብረሃም

📖 @Bemnet_Library


የእኔ ልጅ ወጣት እያለሁ አንዲት ፊያት መኪና ነበረችኝ።እዚያች መኪና ውስጥ ስገባ እና መሪዋን ስይዝ በቃ ዓለም የእኔ የሆነች ትመስለኝ ነበር።የእኛ ሀገር ሴቶች ደግሞ መኪና የሚነዳ ወንድ ሲመለከቱ አይናቸው ይጎለጎላል፤የግራ ቂጣቸው ይንቀጠቀጣል፤ሀብታም ወንድ ብቻ መኪና የሚነዳ ይመስላቸዋል እና በዚያች ፊያት መኪና ስንቷን የደብረማርቆስ ቆንጆ ጨረስኩ መሰለሽ? አይ ወጣትነነት! ወጣትነት ካላወቅሽበት ሬት ካወቅሽበት ደግሞ ማር ነው።

📘ርዕስ፦ኤጭ
✍️ደራሲ፦አዘርግ

@Bemnet_Library

7.2k 1 20 15 129

ለሴቶች ክብር ቢኖርህ ኖሮ ከማንም ሴት ጋር አትተኛም!አንተ ፈሪ ወንድ ነህ።ደፋር ወንድ አንዲት ሴት ብቻ ይመርጣል።ከእርሷ ጋር በደስታ ይኖራል!ፈሪ ወንድ ግን ባለው ብር፤ዝና እየተጠቀመ ከተለያዩ ሴቶች ጋር ይማግጣል።እኔ ደግሞ ፈሪ ባል እንዲኖረኝ ከቶ አልፈልግም።ለሴት ክብር ያለው ወንድ ከተለያዩ ሴቶች ጋር አይማግጥም!አንተ ደግሞ ለሴት ክብር የለህም!!ስለዚህ በጭራሽ ለሴት ክብር የሌለው ወንድ ባሌ እንዲሆን አልፈልግም።በዚያ ላይ አንዲት ሴት ላንተ ዝና እና ችሎታ ወይም ምላስ በቀላሉ የምትንበረከክ ከሆነች ልክ እንደ አንተ ምላስ፤ዝና፤እና ችሎታ ላለውም ለሌለውም ወንድ ትንበረከካለች ማለት ነው።ስለዚህ ይቺ ሴት የሁሉም ናት ማለት ነው።የሁሉም የሆነ ነገር ደግሞ አስጠሊታና ርካሽ ነው!

እኔ እኮ ቆንጆ ነኝ! በጣም ውብ ከሚባሉት መካከል ነኝ ብፈልግ ስንቶችን ወንዶች እያተራመስኩ መኖር እችላለሁ።ግን ያ ተራነት..ያ ፈሪነት ነው።ያ ራስወዳድነት ነው።እኔ ደግሞ ተራም! ፈሪም! ራስ ወዳድም መሆን አልፈልግም።በዚያ ላይ ለወንዶች ትልቅ ክብር አለኝ።ስሜቴን መቆጣጠር እችላለሁ!ወሲብ በጣም እወዳለሁ ቢሆንም ወሲብ እጅግ በጣም ደስ የሚለው እና ጣፋጭ የሚሆነው ከአንድ ሰው ጋር ብቻ ስታከናውን እና የፈጣሪን ህግ የጠበቀ ሲሆን ነው

📚ለሚስቴ ባል ፍለጋ
✍️ አዘርግ

@Bemnet_Library

7.2k 0 56 16 219

አንድ ጊዜ እየዘለለ መጣ።

ምን አገኘህ? አልኩት

"አቤት የእግዚአብሔር ድንቅ ስራ!እንዴት ያለች ውብ ቺክ ጠበስኩ መሰለህ?"

"የት?"

አየር መንገድ ያሬድን ሸኝቼ ስመለስ አንዲት የእግዚአብሔርን ድንቅ ስራ ተመልክቼ  በመሄድ "አገራችሁ በጣም ይሞቃል" በማለት ጠጋ አልኳት....እሷም እንደ እኔ ሰው ሸኝታ እየወጣች ነበር፤ኦ ፈጣሪ እንዴት ታምራለች መሰለህ?"

"ከዚያስ?'

የት አገር ነበርክ አለችኝ"

"ስፔን ነበርኩ"

"የት?"

"ባርሴሎና"

"Spanish ትችላለህ'

"ያ"

"እስቲ የሆነ ነገር በል"

"ሉኔስ ማርቴስ ማርኮሌስ ሁየቬክ ቪየርኔስ ዶሚንጎ" አልኳት

"ምን ማለት ነው" አለችኝ

"እስከዛሬ እንዳንቺ ውብ አላየሁም" ስላት ክትክት ብላ ነው የሳቀችብኝ።ከዚያ በጎን እያየችኝ "አሪፍ ውሸታም ይወጣሀል።ለማንኛውም Spanish ቋንቋ ተናጋሪ ነኝ።አሁን ያወራህው እኮ ሰኞ..ማክሰኞ ርዕቡ ሐሙስ አርብ ቅዳሜና እሁድ ነው" ብላኝ እርፍ.......

"ቅሌት ተከናነብካ?" ስለው

"በቃ ለዚህ ውሸቴ ጁስ ልጋብዝሽ አልኳትና እያሳሳኳት ጁስ ጋበዝኳት!ስልኳን ተቀበልኩ!አየህ ውብ ሴቶችን ብዙ ወንዶች በተለይ መኪና እና ገንዘብ ከሌሏቸው ስለሚፈሯቸው አንተ መፍራት የለብህም!በዚያ ላይ ውብ ሴቶች ቀለል አድርጎ የሚቀርባቸውን ወንድ ይወዳሉ።

📘 ለሚስቴ ባል ፍለጋ
✍️አዘርግ

✈️ @Bemnet_Library

7.1k 0 32 4 145

"ከሟቹ ጋር የነበራችሁን ግንኙነት ብትገልፅልኝ"

"ሟች በሕይወት በነበረበት ጊዜ የነበረን ግንኙነት ያስተናጋጅ እና የተስተናጋጅ ነበር!"

"ሟች በሞተበት ቀን የነበረውን ሁኔታ ትገልፅልኛለህ?"

"ወደ ካፊያችን መጥቶ ውሃ አዘዘ፤አቀረብኩለት።በአጠገቡ ተቀምጠው ሻይ ሲጠጡ የነበሩ ሰዎች እንደነገሩኝ ወዲያው ከኪሱ ብዙ ክኒኖች አውጥቶ ባቀረብኩለት ውሃ እያወራረደ ዋጣቸው።አይ የቀን ጎዶሎ......ምነው ውሃውንም እንደ ክኒኑ ከቤቱ ይዞት በመጣ....."

"በጊዜው በሟች ፊት ላይ ላይ የተስፋ መቁረጥ ስሜት አንብበሃል?"

"ንባብ ላይ ያን ያህል ነኝ፤ጌታዬ"

"አልገባህም፤ስትመለከው ተስፋ ቆርጧል ብለህ ገምተህ ነበር?"

"መቼስ በርገር በሚቀረጠፍበት፤ኮካኮላ እንደ ውሃ በሚፈስበት ካፌ ውስጥ አንድ ሰው የቧንቧ ውሃ ብቻ ካዘዘ ተስፋ ቢቆርጥ ነው! ግን መልሶ እጁን ቦርሳው ውስጥ ሲከት ሳይ፤የምሳ ዕቃ ሊያወጣ ነው ብዬ ተዘናጋሁ"!

"ከዚያስ?"

"ከዚያ ልቤን ሲያወልቀው ለነበረ ተስተናጋጅ ስቴክኒ አድርሼ ስመለስ፣ያ ወጣት ወንበሩ ላይ ዘፍ ብሎ ተኝቷል።አይ ምስኪን! ይሄኔ ሮንድ አድሮ ይሆናል ብዬ ቸል አልኩት"

"የመጀመሪያ ርዳታ አላደረክለትም?"

"አድርጌለታለሁ፤ተኝቷል ብዬ ስላሰብኩ ዘፈኑን ቀነስኩለት፤በተጨማሪም አንገቱን ወደ ወንበር መደገፊያው አቃናሁት።በእኔ ቤት በስነስርዓት ማስተኛቴ ነበር።ለካ አጅሬ በሥነ-ሥርዓት እየሞተ ኖሯል"

"ሟች ከመሞቱ በፊት የተናገረው ነገር አለ?"

"ሰው ሲኖር መናገሩ መች ይቀራል!"

"አባባሌ አልገባህም፤ከመሞቱ ጥቂት ደቂቃዎች በፊት የተናገረው ነገር አለ ወይ?"

"የለም።ባይሆን ከጎኑ የተቀመጠ ተስተናጋጅ ተናግሯል'

ፖሊሱ በረጅሙ ተንፍሶ ወደ ወንበሩ መደገፊያ ተንጋሉ ሲያስብ ከቆየ በኃላ "አቶ አባተ፤ለማንኛውም ሟች ለነገይቱ ኢትዮጵያ ብዙ ምርምሮችን ያበረክታል ተብሎ የታሰበ ወጣት ነበር።ምን ያደርጋል፤ብዙ የእንቅልፍ ክኒኖችን በመውሰድ ራሱን አጥፍቷል፤" ብሎ በረጅሙ ተነፈሰ።

አባተ አንገቱን ደፍቱ ትንሽ ካሰበ በኃላ "ከእናንተ ባላውቅም......ብሎ ጀመረ.....ሟች የዋጠው የእንቅልፍ ክኒን ከሆነ ጊዜው ይርዘም እንጂ መንቃቱ አይቀርም፣ቁርጡ እስኪታወቅ ድረስ መንግስት አስክሬኑን መቅበር ትቶ በወዶገባ ዘበኛ ቢያስጠብቀው ይበጃል ባይ ነኝ"

መርማሪው ፖሊስ አባተን በንቀት ለጥቂት ደቂቃ ካተኮረበት በኃላ መሄድ እንደሚችል ገለፀለት።

📘 ርዕስ፦መግባት እና መውጣት
✍️ደራሲ፦በእውቀቱ ስዩም

✈️ @Bemnet_Library

8.4k 0 58 14 236

Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
በእጅ የተፃፈ የፍቅር ደብዳቤ ለሴቶች የአእምሮ ጨዋታ ይሰጣቸዋል።እኔ ደብዳቤ ስጽፍ ቁልጭ አድርጌ አልጽፍም።ጥቂት ዐረፍተ ነገሮችን ሆን ብዬ እሰርዛለሁ፤እደልዛለሁ።ሄለን የተደለዙ ዐረፍተ ነገሮችን ለማንበብ ከመጓጓቷ የተነሳ ሁለት የራስጌ መብራት እና አንድ ትልቅ ጣፍ አስተባብራ እንደምትጠቀም አውቃለሁ።በመጀመሪያ ከልቡ የወጣው ቃል ምንድን ነው? በኋላ ለምን ሰረዘው? በሁለቱ ሐሳቦች መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው? እያለች መመራመሯ አይቀርም።አንዲት ሴት ከተሰረዘ ዐረፍተ ነገር ጀርባ ያለውን ሀሳብ ለማወቅ የምታደርገው ጥረት በጎረቤት መታጠቢያ ቤት ውስጥ ወንድን አጮልቆ እንደ ማየት ያለ ደስታ ይሰጣታል።"ብቻ ምን ልበልህ?" በእጅ የተፃፈ ደብዳቤ ብዙ ምትኋት አለው።

📘 ርዕስ፦መግባት እና መውጣት
✍️ደራሲ፦በእውቀቱ ስዩም

✈️ሼር ለማድረግ፦ t.me/Bemnet_Library/5075

9k 0 7 9 164

ትኩሳት.pdf
8.0Мб
📚 ርዕስ፦ትኩሳት
✍️ ደራሲ፦ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር

ተጨማሪ መጽሐፎች እንዲለቀቁ ሪያክት👍 አድርጉ

📚 @Bemnet_Library

8.9k 0 30 10 58

📚 ርዕስ፦ትኩሳት
✍️ ደራሲ፦ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር

ተጨማሪ መጽሐፎች እንዲለቀቁ ሪያክት👍 አድርጉ

📚 @Bemnet_Library


ሁላችሁም ሁለት ታላላቅ ስጦታዎች አሏችሁ፤ጊዜና አእምሯችሁ።በሁለቱም የሚያስደስታችሁን መስራት የእናንተ ምርጫ ነው።ወደ እጃችሁ በምትገባው እያንዳንዱ ገንዘብ ላይ  የፈለጋችሁትን በመወሰን ዕጣፋታችሁን ለመወሰን ነፃ ናቸሁ።

ዕዳ በሚያመጡ ነገሮች ላይ ካዋላችሁት መካከለኛ ገቢ ያላቸውን ሰዎች ትቀላቀላላችሁ።በአእምሮሯችሁ ላይ ካዋላችሁት እና ንብረትን ማካበት ከተማራችሁበት ግን የወደፊት ህይወታችሁ በሀብት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን እየመረጣቸሁ ነው።

ምርጫው የእናንተና የእናንተ ብቻ ነው።በእያንዳንዱ ቀን በእያንዳንዱ ብር አማካኝነት ሀብታም፤ባለመካከለኛ ገቢ፤ወይም ደሀ ለመሆን ምርጫ እያካሄዳችሁ ነው።

📚ርዕስ፦ሀብታሙ አባትና ደሀው አባት
✍ደራሲ፦ሮበርት ኪዮሳኪ

✈️ @Bemnet_Library


በ1960ዎቹ መጀመሪያ ላይ የፎኒክስ የገንዘብ አቅም በጣም አስጊ ነበር።ወደ ክስረት የሚያመራ አካሄድ ውስጥ የተዘፈቀ ነበር ማለት ይቻላል።አንድ ቀን "Good morning America" የተሰኘውን ፕሮግራም በቴሌቪዥን ስመለከት ገንዘብን ከማካበትና ከማጣት ጋር አያይዞ የሙያው ተንታኝ እየተናገረ ነበር።

እርሱም 'ገንዘብ ቆጥቡ" ካለ በኋላ "በወር 100 ዶላር ብታስቀምጡ ከ40 አመት በኋላ ሚሊየነር ትሆናላችሁ" አለ።ተመልከቱ በየወሩ የተወሰነ ገንዘብ ማስቀመጥ መልካም ነው።አንዱም አማራጭ ሊሆን ይችላል።

ችግሩ ግን ገነንዘቡን የሚቆጥበው ሰው፤ገንዘብ ማስቀመጡን እንጂ በአገሩና በአለም አቀፍ ደረጃ የሚካሄደውን የገንዘብ ልውውጥ የመውጣትና የመውረድ ሁኔታን ሳያገናዝብ በየወሩ በማስቀመጥ ብቻ ነው ለዕድገቱ ተስፋ የሚያደርገው..ለዛም ነው ገንዘብን መቆጠብ ብቻ ሳይሆን  የፋይናንስ እውቀት ሊኖረን የሚገባው።

📚ርዕስ፦ሀብታሙ አባትና ደሀው አባት
✍ደራሲ፦ሮበርት ኪዮሳኪ

✈️ @Bemnet_Library


ሁለት አባቶች ነበሩኝ።አንደኛው ጠንክሬ አጥንቼ ጥሩ ውጤት በማምጣት ጥሩ ክፍያ የሚያስገኝልኝ ስራ እንድፈልግ ሲመክረኝ ሌላኛው ደግሞ ሀብታም መሆን የምችልበትን መንገድ እንዳጠና፣ገገንዘብ የሚሰራበትን መንገድ እንድገነዘብና ገንዘብን የማሰራበትን መንገድ እንዳውቅ ይጎተጉተኛል።ደጋግሞ የሚለኝ "ለገንዘብ አልሰራም፤ገንዘብ ለእኔ ይሰራል" የሚለውን አባባል ነው።

📚ርዕስ፦ሀብታሙ አባትና ደሀው አባት
✍ደራሲ፦ሮበርት ኪዮሳኪ

📚 @Bemnet_Library


እየሰራው ነው ያላቹህ? "የራሳችሁን ስራ ነው የምትሰሩት" ወይንስ "ተቀጥራችሁ ነው የምትሰሩት"
Опрос
  •   የራሴን
  •   ተቀጥሬ
302 голосов


አሁን በምን ሁኔታ ውስጥ ናችሁ? "እየሰራችሁ ነው?" ወይንስ "እየተማራችሁ?"
Опрос
  •   እየተማርኩ!
  •   እየሰራው!
  •   ሁለቱንም እያስኬድኩ!
  •   ትምህርቴን አቋርጫለሁ፤ስራም የለኝም
239 голосов


The Person You will be in five years is based on the Books You Surround yourself with Today.

በሚቀጥሉት 5 ዓመታት ውስጥ የምትሆነው ሰው ዛሬ ባነበብካቸው መጽሃፎች እና በዙሪያህ ባሉህ ሰዎች ላይ የተመሰረተ ነው።

📚 @Bemnet_Library


አንዳንድ ነገሮችን መቀየር አልችልም።ለምሳሌ አንቺን ማፍቀሬ ስዕተት መሆንን እያወኩ እንኳን ፍቅሬን ማስቆም አልቻልኩም ነበር።ምክንያቱም ከባዷ እጣፋንታዬ በአንቺ ህይወት መካካል አቅም-አጥታ ወደቃ ነበር.......

ጓደኞቼ ጠየቁኝ.....ቤተሰቦቼም በደምብ ጠየቁኝ....ሁሉም ወዳጆቼ የምር እንዳፈቀርኩ ማመን ፈልገው ነበር......ያ ዝምተኛው ሰው፤ያ ከክፍሉ የማይወጣው ሰው፤ያ አይናፋሩና ሴቶችን ማውራት በጣም የሚከብደው ሰው ያፈቅራል ብለው አላሰቡም ነበር።

ግን የሆንኩትን የማውቀውና የምረዳው እኔ ብቻ ነበርኩ።ማንም ሰው ማፍቅር ስለፈለገና ስላልፈለገ እንደማያፈቅር ተረድቻለው።በሌሎች ማፍቀር የሚስቀው ሁሉ ነገ እሱም ተረኛ እንደሆነ አውቂያለው።ፍቅር ባልጠበቅነውና ባላሰብነው ጊዜ የሚመጣ ከባድ ነገር መሆኑንም በደምብ ተገንዝቢያለው......ስለዚህ ፍቅር ወደደንም ጠላንም እኛ ስለፈለግንና ስላልፈለግን የሚሆን ሳይሆን እንደ ድንገት የሚከሰት ምትሃታዊ ሀይል ነው።

(ከአንቺ ፍቅር እንደማይዘኝ ያጣጣልኩት እኔ አንቺን ያፈቀርኩበት የማይታመን ጊዜ)

(Unreal)
✍️ Bemni Alex


አንዳንድ ሴቶች ፍቅረኛቸው እንቅልፍ የመንሳት መብት ያላቸው ይመስላቸዋል። ድምፃቸው ፍራሽ፣ ሹክሹክታቸው አንሶላ፣ ሳቃቸው አንቅልፍ ሆኖ እረፍት እንደሚሰጥ። የምንሰለቻቸው አይመስላቸውም። ከተፈጥሮ በላይ የመሆን አቅም ያላቸው ይመስላቸዋል? ልካቸውን አያውቁም!!

📚ርዕስ፦ ዙበይዳ
✍️ፀሃፊ፦ አሌክስ አብረሃም

📖 @Bemnet_Library

12.4k 0 32 12 104

📢"ተቋርጦ የነበረው የማስታወቂያ ስራችን ተመልሷል!

➡️ Training Centers
➡️ የቴሌግራም ቻናል ማስታወቂያ
➡️ የትምህርት እቃዎች ሽያጭ
➡️ ትሪትመንቶች
➡️ የቡቲክ ልብሶች ማስታወቂያ
➡️ Consultancy
➡️ የሞባይል እና አክሰሰሪ
➡️ እናም ሌሎችም ማስታወቂያዎችን

በቀን/daily ፣ በሳምንት/weekly ፣ በ 2 ሳምንት/ bi weekly እንዲሁም በ ወር/Monthly እንሰራለን።

🗣ለማናገር- @Bemni_Alex


እጅግ ደሀ የሚባሉ ሰዎች ህልም የሌላቸው ሰዎች ናቸው። ውድቀትን በመፍራት ፈፅሞ ከመሞከር አትቆጠቡ፡፡ ራሳችሁን አንድ ነገር ጠይቁ፡፡ ውድቀት አንድ አጋጣሚ ነው፡፡ ከውድቀት የበለጠ ሌላ ነገር አለ  ከዚያ ውድቀት በስተጀርባ ጥልቅ የሆነ ስኬት አለ፡፡ ውድቀት ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ እንደገና ሀ ብሎ የሚጀመርበት አጋጣሚ ነው፡፡ ውድቀት ማጋጠሙ እንደገና ለመጀመር ታላቅ አጋጣሚ ነው፡፡ ከውድቀታችሁ ትምህርት ቀስማችሁ ወደፊት መጓዛችሁን ቀጥሉ፡፡ ውድቀት ከጥረታችሁ እንዲገታችሁ አትፍቀዱ፡፡

📚የእምቅ ክህሎትን ሀብት መረዳት
✍️ማይለስ ሙንሮ

💬 @Bemnet_Library

Показано 20 последних публикаций.