ቤተ-አምሓራ ሚድያ Bete amhara media


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Политика


በሀገራችን ኢትዮጵያ በፓለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊ እንድሁም በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ትንታኔ የሚሰጥ ምርጥ የቴሌግራም ቻናል።
Offical Group @BeteamhramediaGroup
Telegram፦ https://t.me/Bete_amharamedia
Facebook፦ https://www.facebook.com/beteamharamediaa/

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Политика
Статистика
Фильтр публикаций




የላሊበላ ወጣቶች ተላላኪውን በዓዴን አሳፍረው መለሱት።

የላሊበላ ከተማ ካድሬ ዛሬ በ06/09/2015 ዓ.ም ፋኖ ይመታ የሚል የድጋፍ ሰልፍ ጠራ። በሰልፉ ላይ ብአዴን ያደኸያቸው የሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች ነበር የተገኙት።

ነገር ግን እሳት የላሰው የከተማው ወጣት በጎን የተቃውሞ ሰልፍ አደረገ። ነገሮች በተፈለገው መልኩ መሄድ ሳይችሉ ቀሩ። ካድሬ ትናንት ከኦነግ ተዘጋጅቶ የተላከለትን መልዕክት በሚዲያ አስተላለፈ። መሬት ላይ የሆነው ግን ሌላ ነበር።

በመጨረሻም ሁለቱም ሰልፍ በፖሊስና ሚኒሻዎች ተበተነ።


ዛሬ የታላቅ አማራ ሰማእት የአባታችን ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ የሰማእትነት እለት ነው ..‼️‼️

         

የአማራ ሕዝብ አባታችን ለትግል ከተነሱበት ጊዜ ይልቅ ዛሬ በከፋ የኅልውና ስጋት ውስጥ ይገኛል። በአንፃሩ ከዚያ ዘመን ይልቅ ዛሬ ለአማራነቱ ሰማእትነትን ለመቀበል በጽናት የቆመው እጅግ ብዙ ነው። ፈተናው ምንም ቢበረታ የአባታችንን የሰማእትነት አደራ ተቀብለን የሕዝባችንን የፍትኅ፣ እኩልነት እና ነፃነት ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተን የሁሉም፥ በሁሉም የሆነች ኢትዮጵያን እውን እንደምናደርግ ቅንጣት እንኳን ጥርጣሬ የለኝም።

ዘላለማዊ ክብርና ሞገስ ለታላቁ የአማራ ሰማእት ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ!
ክብር የአባታችን ቃልኪዳን ወራሽ ሆነው በጽናት በትግል ላይ ላሉ ሁሉ!


አማራ ባንክ አ.ማ ለ29 የሚሆኑ የራያ ገበሬዎች በረጅም ጊዜ ብድር ትራክተሮችን ገዝቶ አስረክቧል።


“በዓይነቱም በግዝፈቱም ወደር የማይገኝለት የዓለምን ክብረወሰንን ይሰብራልም ተብሎ የሚጠበቅ መፈናቀል በቅርቡ በኢትዮጵያ ይኖራል!”

-ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን

ጠ/ሚሩ ከአራት የማይበልጡ ቤቶችን ለማደስ ዶማ ይዘው ወጥተዋል። ምሽቱን በ10ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች በላያቸው ላይ ቤታቸው ፈርሶ ሜዳ ላይ ተጥለዋል። የአሁኑ የሚከፋው ደግሞ ቤታቸው የፈረሰባቸው ሰዎች በአከባቢው ፈጽሞ መገኘት የለባቸውም በሚል የተጀመረው እስከግድያ የሚደረስ እርምጃ ነው። ዓርብ ሌሊት በሰበታ በመንግስት ሃይሎች በተውሰደ እርምጃ የተገደሉ ሰዎች 4 ደርሷል። አራት ነፍሶች በአንድ ሌሊት።

እንደሰማሁት አሁን የተጀመረው ቤት የሚፈርስባቸው ሰዎች በአዲስ አበባም ሆነ በዙሪያዋ ቤት መከራየት አይችሉም። የሚያከራያቸው ካለ ከባድ የገንዘብ ቅጣት ይከፍላል። ወደ ሀገራችሁ ሂዱ! ነው እየተባሉ ያሉት። መሄጃ የለንም ብለው ወዳጅ ዘመድ ጋ የተጠጋ እግር በእግር ክትትል ተደርጎበት ይደበደባል፡ ይታሰራል፡ እንደነ አቶ መሀመድና ባለቤታቸው ከሆነ ደግሞ በጥይት ተደብድቦ ይገደላል። አይናችሁን ማየት አንፈልግም ዓይነት ፍጹም አረመኔያዊ ተግባር ነው መሀል ኢትዮጵያ ላይ እየሆነ ያለው። ሰውዬው ደግሞ አብራር አብዶን ያስናቁ ቲያትረኛ ወጥቷቸዋል። 10ሺዎችን በጎን ያፈናቅሉና ዶማ ይዘው ቅዳሜን ጠብቀው ሶስት ቤቶችን ሲያሳድሱ በካሜራ እይታ ውስጥ መሆናቸውን ካረጋገጡ በኋላ ረጅም ሀተታ ለቀው ይሄዳሉ። እሳቸው ጋ አመራር እንዲህ ነው። ነገም ይቀጥላል። ሌላ ቅዳሜ ይመጣል። 10 ሺዎች ይፈናቀላሉ። 10 ቤትች ይታደሳሉ። ይኸው ነው።

ይልቅስ የከፋው ግዙፉ መፈናቀል ከፊት እየመጣ ነው። ምናልባትም ይኸኛውም መፈናቀል በዓይነቱም በግዝፈቱም ወደር የማይገኝለት ይሆናል። የዓለምን ክብረወሰንን ይሰብራልም ተብሎ የሚጠበቅ ነው። አንድ ትሪሊየን የሚጠጋ ብር ይፈጃል የተባለውና ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንቅልፍ ያጡለት የቤተመንግስት ግንባታ ግማሽ ሚሊዮን የአዲስ አበባና ዙሪያዋን ነዋሪዎች እንደሚያፈናቅል እየተነገረ ነው። 500ሺህ ዜጎች በሚቀጥሉት ወራት ውስጥ ቤታቸው ይፈርሳል ተብሎ ይጠበቃል። ከወዲሁ መጀመሩንም እየሰማሁ ነው። እናቶች ተጨንቀዋል። አባቶች መላ ቅጡ ጠፍቷቸዋል። ሰዉ የት እንደሚሄድ ግራ ገብቶት እንደእብድ መንገድ ላይ እያወራ ወዲህ ወዲያ ይንከላወሳል። የአቶ አቢይ አህመድ መንግስት ይዞ የመጣው ዱብ እዳ ኢትዮጵያውያን በታሪካቸው አይተውት ሰምተውት የሚያውቁት አይደለም። ይሄ መቼም ቁጣ ነው። ፈጣሪ የተቀየመው ነገር ቢኖር እንጂ እንዲህ ዓይነት ህዝብ የሚያስለቅስ፡ ሀገር ማቅ የሚያስለብስ አገዛዝ ምን ቢፈርድበት ነው የሰጠው?

የጫካ ፕሮጀክት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ካለሟቸው ቅንጡ ፕሮጀክቶች ትልቁ ነው። የኢትዮጵያን ዓመታዊ በጀት ሁለት እጥፍ ይስተካከላል። ገንዘቡ ከየት ይመጣል የሚለው ከጠቅላይ ሚኒስትሩና ሰጪዎች በቀር የሚያውቀው ፈጣሪ ብቻ ነው። ለምክር ቤቱ አያገባችሁም ብለዋል። የኢኮኖሚ ባለሙያው ዶ/ር ዮናስ ብሩ እንዲህ ዓይነት በህዝብ የተመረጠንና ሰይሞት ስልጣን የሰጠውን ምክር ቤት አያገባችሁም የሚል መሪ የትም ሀገር ኖሮም ተፈጥሮ አያውቅም ብለዋኛል ሰሞኑን። አቶ አያልቅበት እንደልቡ ናቸው። የህዝብ ንቀት እስከአፍንጫቸው ደርሶ በአፍጢማቸው ሊደፋቸው ደርሷል። ምንም ነገር አይቀበሉም። ማንንም አይሰሙም። ከእነመንግስቱ ብሃይለማርያምና መለስ ዜናዊም ብሰው ሁሉን ነገር ፈላጭ ቆራጭ ሆነው አርፈዋል። ሀገሪቱን የግል ንብረታቸው አድርገዋታል። ሚኒስትሮቻቸውን የግል አሸከሮቻቸው እንጂ በራሳቸው የቆሙ መንግስትን የሚወክሉ አድርገው አይመለከቷቸዋም። በዙሪያቸው ሰጋጅ፡ ምንጣፍ ጎታች ሰብስበዋል። በአጭሩ ሰው ጤፉ ናቸው። ሚሊዮኖች ቢፈናቀሉ፡ ሚሊዮኖች ቢገደሉ ስሜት አይሰጣቸውም። ይህን ሁሉ መዓት ሀገሪቱን ላይ ከምረውና ቆልለው፡ ፈካ ፈታ ብለው ሲታዩ እውን ይሄ የጤና ነውን የሚል ጥያቄን ያጭራል።

እንግዲህ ይህ የጫካ ፕሮጀክት አሁን ባለው ዋጋ 850ቢሊየን ብር ወይም 15ቢሊየን ዶላር የምሚፈጅ ነው። ስራው ተጀምሮ እስኪያልቅ ከአንድ ትሪሊየን ብር ሊሻገር እንደሚችል ነው ባለሙያዎች የሚገልጹት። ይህን ብር ይዘን ሂሳቡን በተለያዩ ለኢትዮጵያውያን የህይወይትና ሞት ሽረት በሆኑ ጉዳዮች እንመንዝረው። በዶላር ያለውን ሂሳብ ወስደን ማለት ነው። 15 ቢሊየን ዶላር፥ ሶስት የህዳሴ ግድብን ይገነባል። 1ቢሊየን ዶላሩ 20 ሆስፒታሎችን በየክልሉ ማቆም ያስችላል። ሌላ 1 ቢሊየን ዶላሩ በርካታ ደረጃቸውን የጠበቁ ዩኒቨርስቲዎችን ያቋቁማል። 1 ቢሊየን ዶላር በትግራይ፡ በአማራና በአፋር ክልሎች የወደሙ ሁሉንም ትምህርት ቤቶች መልሶ በተሻለ መልኩ ለመገንባት ያስችላል። 1 ቢሊየን ዶላር የኮይሻ ሀይድሮ ኤሊክትሪክ ፕሮጀክት ግንባታን እንዲጠናቀቅ ያደርጋል። በ1 ቢሊየን ዶላር 3ነጥብ 3 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ስንዴ ይገዛል። ለ20 ሚሊየን የተራቡ ዜጎቻችን ከአምስት ወራት በላይ ቀለብ እንዲኖራቸው ያደርጋል። 1 ቢሊየን ዶላር 4ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ስኳር ለመግዛት ያስችለናል። 1 ቢሊየን ዶላር 2ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ዩሪያ ማዳበሪያ ይገዛልናል። አርስ አደሮቻችን ተንበሸበሹ ማለት ነው። እንግዲህ እስከአሁን የተጠቀምነው 6 ቢሊየን ዶላሩን ብቻ ነው። 9 ቢሊየን ዶላር ይቀረናል። እንቀጥል ይሆን?

የአብይ አስተዳደር 2ቢሊየን ዶላር ገንዘብ እንዲሰጠው የገንዘብ ሚኒስትሩንና የብሄራዊ ባንክ ገዢውን አሜሪካን ድረስ ለአንድ ሳምንት አቆይቶአቸው ደጅ ሲጠኑ ከርመዋል። ባዶ እጃቸውን ቢመለሱም ያቺን ዶላር ለማግኘት ያደረጉት ተጋድሎ መቼም የሚዘነጋ አይደለም። የዶላር ጠኔ ውስጥ ሆኖ የሚሰቃየው መንግስት ነው እንግዲህ ከየት እንደሚሸመጠጥ ግልጽ ባልሆነ 15ቢሊየን ዶላር እነኋይት ሀውስንና በኪንግሃም ቤተመንግስቶችን የሚያስንቅ ግዙፍ ቤተመንግስት ለማስገንባት እየተዘጋጀ ያለው። 98 በመቶ ከመካከለኛ ገቢ በታች የሚኖር ህዝብ ባለባት፡ 30 ሚሊዮን የምግብ እርዳታ ጠባቂ የሆኑ ዜጎች በሚኖሩባት፡ 38 በመቶ የዋጋ ግሽበት በሚያሰቃያት፡ በቀን አንድ ጊዜ ለመብላት ምጥ የሆነበት ሲሶ ያህል ህዝብ በሚርመሰመስባት ሀገረ ኢትዮጵያ ነው እንግዲህ አቶ አብይ አህመድ የሀገሪቱን የሁለት አመት በጀት በአንድ ቅንጡ ቤተመንግስት ላይ ለማባከን ቀበቶአአቸውን ታጥቀው የተነሱት።

ከገንዘቡ በላይ አፈር ከድሜ ያስጋጡት የሀገሪቱ ስርዓተ መንግስትና የህግ የበላይነት እጅግ የሚያሳስብ ነው። አያገባህም የተባለው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፉን ሎጉሞ የሰውዬውን የእብደት አካሄድ ቆሞ እያየ ነው። እንደውም አብዛኞቹ የምክር ቤቱ አባላት ''አበጀህ የእኛ ልጅ'' ዓይነት ውዳሴና ሙገሳ እያዥጎደጎዱ ናቸው። በኢትዮጵያ መሬት አንዲት ስንዝር መሬትና አንዲት ስባሪ ሳንቲም ያለምክር ቤቱ ፍቃድና እውቅና መነካት እንደሌለበት ቢታመንም ከህግ በላይ፡ ከሀገሪቱ በላይ ለመሆን በሚታትሩት ጠቅላይ ሚኒስትር መዳፍ ውስጥ ተጨብጦ የቀለጠው ምክር ቤቱ ታላቅ ታሪካዊ ስህተት እየሰራ መሆኑን አለመረዳቱ እጅግ አሳዛኝ ሁኔታ ነው ማለት ይቻላል። የኢትዮጵያ ህዝብ ይሄን ፕሮጀክት ማስቆም ይገባዋል። ምንምአይጠቅምም። ራስ ሳይጠና ጉተና እንዲሉ የኑሮ ሰማይ እንደእንቅብ ለተደፋበት 98በመቶ ለሚሆን ህዝብ የጫካ ፕሮጀክት ሸክም ሆኖ ወገቡን የሚቀነጥስ እንጂ ቀና የሚያደርገው ፈጽሞ አይሆንም።


አሁን ይሄ ግፍ እንደት አይነት ሰው መሸከም ይችላል😭😭😭

ኦሮሞ በልጅ ልጆችህ ተከፍሎ የማያልቅ ግፍ አለብህ።


ቤታቸው የፈረሰባቸው ባልና ሚስት ትላንት ማታ ተገደሉ።

በሰበታ ከተማ በኬንተሪ ደረቶ በሚባል ቦታ የአቶ መሀመድና የጎረቤቶቹ ቤቶች የፈረሱት ከትላንት በስቲያ ነበረ። ሙሉ ሰፈሩ ፈርሶ አልቋል ማለትም ይቻላል። አቶ መሀመድም እዛ ሰፈር ከገባ ወደ 18 አመት አካባቢ ሆኖታል።

ቤት ከፈረሰባቸው ሰዎች መሀከል የአቶ መሀመድ አብደላን ጨምሮ የሁለት ቤተሰብ አባላት ቤታቸዉ ከፈረሰባቸዉ በሆላ የሚሄዱበት አጥተው ተቸግረዋል። ትላንት ከሰአትም አብዛኛው እቃቸውን ወደ ገጠር ከጫኑ በኋላ ሰፈራቸዉ በሚገኝ አንድ ፊኒሽንጉ ያላለቀ የሪልስቴት ፎቅ ግራውንዱ ላይ ቦታ ያለ በመሆኑ በባለቤቱ መልካም ፍቃድ "ቤት እስክታገኙ "እዛ ግቡ" ብሎዋቸዉ ገቡ።

ማታ ፖሊሶች መጥተው እነመሀመድ የተኙበትን የህንፃውን በር መደብደብ ጀመሩ። መሀመድም ማንነታቸውን ለማጣራት በመጠየቅ ላይ እያለ በሩ በሀይል ተሰበረ። በመቀጠልም አቶ መሀመድ አብደላ እንዲሁም ባለቤቱ ለቢባ ጀማል በጥይት ተመቱ ።

ጩኸቱን ሰምታ ከመጡት ጎረቤቶች መሀል አራስ የሆነችው ሉባባ ብላቱ በጥይት ተመታ ስትሞት ባለቤቷ ደግሞ ከቆሰለ በኋላ አምልጧል።

በጻውሎስ ሆስፒታል ያደረውን አስክሬን አሁን ተቀብለናል።

ተስፋ ነዳ - ከጳውሎስ ሆስፒታል።

Emat Gurage Media


ፋኖ ምሬ ወዳጆ - ከአበበ በለው ጋር ካደረገው ቃለምልልስ ላይ የተወሰደ!

ገና ቁስላችን ሳይደርቅ በፋኖ ላይ ጦርነት ከፍተውብናል። ህዝባችን ከውድመቱ ሳያገግም ሌላ ውድመት ታውጆበታል። አማራ በህብረት ቆሞ፣ ለውጥ ማምጣት አለበት። ፋኖን መደገፍ አለበት።

የአማራ ህዝብ ህግ ያለ እንዳይመስለው። ህግ የለም። እኔ በግሌ ለመሞት ነው የተነሳሁት። የሚያሳፍረው ግን የ3 አመት ልጄ ሳይቀር ታፍኗል። ይሄ የሚያሳየው በኦነጎች ዘንድ ህግም፣ ሞራልም አለመኖሩን ነው። የሚያስከብረው ሀይል ብቻ ነው። የሚያዋጣው መደራጀቱ ብቻ ነው።

አሁን ላይ ኢትዮጵያን የሚወደው ትክክለኛው የመከላከያ ሰራዊት የለም። አብዛኛው ሰራዊት ጥቅምት 24 በህወሃት ተረሽኗል። የቀረው ባለፉት ሁለት አመታት አልቋል። የተወሰኑ የተረፉ ቢኖሩም ወደ አማራ ህዝብ አንተኩስም በማለታቸው እየተረሸኑ ነው።

አሁን የመከላከያን ዩኒፎርም ለብሶ ወረራ የከፈተብን በብሄር ጥላቻ ያበደው የኦሮሞ ልዩ ሀይል ነው።

ሌላው ጠላት ይበቃናል። ስለዚህ የአማራን አመራር አንገድልም። የአማራን አመራር መግደል ብንፈልግ፣ በህወሃት ወረራ ጊዜ ህዝቡን ለጅብ ሰጥተው ቀድመው የፈረጠጡ አመራሮችን ነበር የምንገድላቸው። መገደል ብንፈልግ ኖሮ በክፉ ቀን የፈረጠጡት አመራሮች፣ ተመልሰው ስልጣን ሲይዙ ነበር የምንገድላቸው።

እንደ ፋኖ አስተሳሰብ ገዳዩም አማራ፣ ሟቹም አማራ እንዲሆን አንፈልግም። ይሄ የእስካሁን መርሃችን ነው። የአማራ አመራሮችም ከስህተታቸው ይወጣሉ በሚል እየጠበቅናቸው ነው። ነገር ግን የአማራ አመራሮች ዝምታችንን ካለመቻል ቆጥረው ዛሬም እንደ ትናንቱ እየተላላክን፣ ፋኖን እያሳደድን፣ የህዝብ ጥያቄ እያፈንን እንቀጥላለን ካሉ መርሃችንን ልንቀይር እንችላለን።


ቀጣፊ

የአንዱን ቤት በዘሩ እያፈረሱ የአንዱን ቤት መጠገን ከማስመሰል ያለፈ ምንም አይባልም።


የህወሃት እና የኦነግ አክቲቪስቶች በመቀሌ እየመከሩ ነው!

ትግሬዎች ብቻቸውን መቆማቸው ምን ያህል ዋጋ እንዳስከፈላቸው በደንብ የተረዱት ይመስላል። ቂማቸውን በሆዳቸው ይዘው ጥላትን የመቀነስ ወዳጅን የማባዛት ስትራቴጂ እየተከተሉ ነው። “የጥላቴ ጥላት ወዳጄ ነው” በሚል ፖለቲካዊ ስሌት ከኦሮሞ ጋር ጥምረት ፈጥረዋል። መቸም በሚሊዮን የሚቆጠር የትግራይ ወጣት ያለቀው በኦሮሞ ፖለቲከኞች አመራር ሰጪነት እንደሆነ የሚጠፋው ትግራዋይ ይኖራል ብዬ አላስብም። ታሪክም እንደዛ ብሎ ነው የሚመዘግበው።

በቀደም የሀይማኖት አባቶችንና ሽማግሌዎችን ያካተተ ልዑካን ቡድን ወደ መቀሌ አቅንቶ ከነ ጌታቸው ረዳ ጋር ተወያይቶ ተመልሷል። ትላንት ደግሞ ተፅዕኖ ፈጣሪ የኦሮሞ የማህበራዊ አንቂዎች ወደ መቀሌ ጉዞ አድርገዋል። መቸም የሁለቱ ጥምረት ለአማራ ህዝብ ምን ይዞ እንደሚመጣ የሚጠፋው አማራ ያለ አይመስለኝም።

የእኛ ልጆች እርስበርሳቸው ገመድ ጉተታ ላይ ናቸው። አንዱ አንዱን ሲዘረጥጥ ይውላል። ፍፁም መግባባት አቅቶናል።


ስለምንድን ነው የምታወሩት ኧረ አማሮች በሳል ሁኑ አንድ ተላላኪ ባንዳ በሚጥለው ውዳቂ ወሬ አትነዱ‼️

ምሬ ዛሬም ምሬ ወዳጆ ፋኖ ነው‼️
ሰላም ነው‼️


አደብ ግዥ በሏት

ከብአዴን በላይ ስጋቸውን የሸጡ እኛነታችንም ለመሸጥ ሲሞክሩ ማየት ያሳፍራል።

በእርግጥ ይችን ተራ ሴት የማውቃት  እንደ ማንኛውም ሰው በሶሻል ሚድያ ነው።እዛም እዚህም ስትረግ የምናያት ድንቅ ስራ ሰርታም አይደል። ለህዝባችን አበርክቶትም ኖሯት አይደለም።

ገላዋን እየከፈተች የሰጠቻቸው  ከስሯ የሚልከሰከሱት ስጋ ፈላጊዎች ናቸው ትታይ ትታይ የሚሏት እንጅ እኛ ምንም እንደሆነች ነው እምናውቅ።

ወሎ ላይ የኬሚሴ ባህል የሚባል የለም።ወሎ አማራ ከሚሴ የአማራ እንጅ የኬሚሴ ምናምንቴ እሚባል ማንነትም ባህልም ታሪክም የለም።

አደብ ግዥ በሏት።ከኦሮሞ ወንድ ጋር ስለተጋደመች የአማራን ርስት አሳልፋ የምሰጥ እሷ ማን ስለሆነች ነው።

መልእክቱንም አድርሱላት።


ኃላፊው በቢሯቸው ውስጥ ተገደሉ!

የቂርቆስ ክፈለ ከተማ ወረዳ ሰምንት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አለባቸው አሞኘ በጥይት ተመተው ተገደሉ ።ዋና ስራ አሰፈጻሚውን በመግደል የተጠረጠረው የአካባቢው የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ ባልደረባ እንደሆነ የመረጃ ምንጮቻችን ገልጸውልናል፡፡ ተጠርጣሪው ሀላፊውን በሽጉጥ ከገደለ በኋላ ከአንድ ግብረአበሩ ጋር እንደተያዙም ታውቋል።


የዐማራን ትግል በብር፣ በሆድ የሸጡ፣ የለወጡ፣ ክብራቸውን በነውራቸው የቀየሩ፣ ትግል አጨናጋፊዎች፣ በጎንደሬነት፣ በጎጃሜነት፣ በወሎዬነትና በሻወዬነት ስር የተሸሸጉ፣ ሾተላይ የደም ነጋዴ ይሁዳዎችን ከትግሉ አካባቢ በድፍረት ገለል ማድረግ፣ መውቀስ፣ ማሸማቀቅ፣ ማጋላጥ ለነገ የማይባል ነው።


https://www.facebook.com/profile.php?id=100092607521653&mibextid=ZbWKwL


ተወዳጁት በሴም ነገዴ ህዝብ ላይ አተኩሮ የሚሰራ የተከፈተ ገፅ ነው‼️


ይሄ ነገር ምን ያክል እውነት ነው ብላችሁ ታስባላችሁ‼️?


የኦሮሚያ ብልጽግናና የህወሀት ሰዎች በአፍላ ፍቅር እፍ ብለዋል። መሬት ጠቦአቸዋል። ለረጅም ጊዜ ተለያይተው የተገናኙ ፍቅረኛሞች ይመስል ተቃቅፈው፥ ተሳስመው መጥገብ አልቻሉም። ድንበር ባያጎራብታቸው፡ ቋንቋቸው አንድ ባይሆንም፡ ለጊዜው የሚያስጨንቃቸው ሌላ ጉዳይ አይደለም። የተከዳች ኮበሌ ሌላ ፍቅረኛ ይዛ የበፊቱን ለማስቀናት የምታደርገው ብሽሽቅ ይመስላል። ደግሞም ነው። መልዕክቱ ለማን እንደሆነ ግልጽ ነውና። ንፋስ እንኳን መሀላችን አይግባ ብለው በየወንዝ ዳሩ ይማማላሉ፡ በየምክንያቱ ይፈራረማሉ። ፍቅራቸው የጤና እንዳልሆነ ያውቁታል። ከአንጀት ያልዘለቀ፡ አፍ ላይ የሚንከባለል የለበጣ እንደሆነም አልጠፋቸውም። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ፖለቲካን አስቀያሚ በማድረግ ተወዳዳሪ የላቸውም። የትላንት ወዳጃቸውን አይንህን ለአፈር በማለት የሚሽቀዳደማቸው የለም። ''ኢሱ'' በ ''ጌቾ'' ሊቀየር የወሰደው ጊዜ ከሁዜን ቦልት ጋር ክብረወሰን የሚጋራ ነው። በፖለቲካ ዘላቂ ወዳጅና ጠላት የለም የሚለው ዝነኛ አባባል ጠፍቶኝ አይደለም። የእሳቸው ፍጥነቱ አስደምሞኝ እንጂ።

የኦሮሚያ ክልል በወሰን ከማይጋራው ብቸኛ የትግራይ ክልል ጋር እንዲህ ያለ መርህና ሞራል አልባ ግንኙነት ሲመሰርት ታሳቢ የተደረገው ጊዜያዊ ጥቅም ነው። ሁለቱ ክልሎችን እንወክላለን የሚሉት ፖለቲከኞቹ ከሚያመሳስላቸው ይልቅ የሚለያዩባቸው ማህበራዊና ባህላዊ መልኮች ብዙ ናቸው። በቋንቋ ቤተሰብ አይገናኙም። በሃይማኖትም ሰፊ ልዩነት አላቸው። ስነልቦናዊ ውቅራቸውም ለየቅል ነው። ሆኖም ኢትዮጵያዊ በመሆናቸው፡ የጋራ ታሪክ ስላላቸው በጋራ ቢቆሙ ሀጢያት ወንጀል አይሆንም። ችግሩ እንዲህ ያፋቀራቸው፡ ዳመና ላይ ያንሳፈፋቸው ሰበብ ምክንያቱ ምንድን ነው የሚለው ነው። ያገናኛቸው ሌላ ምንም አይደለም። ሁለቱም ስለአንድ ወገን ያላቸው ፍጹም ጥላቻ ነው። የፍቅራቸው ቋሚ ማገር ይኸው ነው። ያስተሳሰራቸው ውልም ይኸው ክፉ ደዌ ነው። የፍቅራቸው ኮንትራት መሰረቱ ለአንድ ማህበረሰብ ያላቸው ተመሳሳይ አቋምና ስሜት ነው።


ሰሞኑን ቋንቋችንን በጋራ ለማሳደግ ብለው መፈራረማቸው ተሰምቷል። በተለያዩ የቋንቋ ቤተሰቦች የሚገኙት ኦሮሚኛና ትግርኛ እንዴት አንድ ላይ አብረው እንደሚያድጉ ከእነሱ ብዙ እንማራለን ብዬ እጠብቃለሁ። አስገራሚው ነገር ይህንንም የሚነጋገሩት በአማርኛ ቋንቋ መሆኑ ነው። ፍቅራችሁን ከአይን ያውጣውና ቋንቋችሁ አንድ ላይ አድጎ ለማየት ያብቃን የሚለው መልካም ምኞቴን እኔም በአማርኛ ቋንቋ ብሰድላቸው እንደሚገባቸው አምናለሁ። በእርግጥ መርህ አልባው ግንኙነታቸው እስከትልቅ ጦርነት ማፈንዳት ድርስ እንደሚዘልቅ ምልክቶችን እያየን ነው። በዚህ የታይታና ከአንጀት ያልዘለቀ ፍቅራቸው ተያይዘው የሚገቡበትን ጦርነት ያሸንፉት ይሆን? ጌታዋን የተማመነች አይነት እምነት ኖሮአቸው በአሜሪካን ትከሻ ጦርነቱ ውስጥ ለመግባት ወስነው ሊሆን ይችላል። አሜሪካን አታደርገውም ብዬ ልሟገትላት አልችልም። ስድስት ሀገራትን ስታፈርስ በእኔ እድሜ ያየኋት አሜሪካን ምስራቅ አፍሪካ ላይ ትናንሽ መንግስታት እንዲመጡ በሚያደርገው አዲስ የፖለቲካ አሰላለፍ ውስጥ ዋንኛ ተዋናይ መሆኗ ብዙም አይስደንቀኝም።

አስገራሚውና ቅስም የሚሰብረው ሀቅ ሁለቱ በተራገጡና በተፋቀሩ ቁጥር መከራውን የሚበላው የኦትዮጵያ ህዝብ መሆኑ ነው። ጦርነት ውስጥ ሲገቡ ለጥይት መግዢያ ኪሱ ሲበረበር የነበረው ይኸው የፈረደበት ህዝብ ነው። አሁን ደግሞ አቅር ላይ ሲሆኑ ለጥሎሽ አዋጡ ተበልው ኢትዮጵያውያን ጉሮሮአቸው ተይዟል። ሰሞኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ መቀሌ ደርሰው ሲመለሱ ለትግራይ ግንባታ የገቡትን የ500ሚሊዮን ብር ቃል እንዲሸፍኑላቸው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪን ቤት ለቤት እያስጨነቁ መሆኑ ተሰምቷል። እሳቸው በሞቅታ ለገቡት ቃል የአዲስ አበባ ህዝብ እዳ ከፋይ የሚሆንበት ነገር ነው ግራ የሚያጋባው። ህዝብ ለህዝብ ተገናኝቶ፡ የምር ሰላም ተፈጥሮ ቢሆን ኖር ከዚህም በላይ ቢደረግ ቁምነገሩ ከፍ ያለ ነው። እነሱ  ተጣልተው እነሱው ለታረቁት ሌላው ምን ቤት ሆኖ ነው መከራውን የሚበላው? ሲጣሉ ጥይት ገዝቶ፡ ሲታረቁ ለውስኪያቸው አዋጥቶ እንዴት ይቻላል?

ይሄ የመዋጮ ነገር ሲነሳ የጠቅላይ ሚኒስትሩ መጽሀፍ ኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ጎትቶ ያመጣው እዳ ትዝ አለኝ። ከተለያዩ ቦታዎች የሚደርሱኝ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የጠቅላይ ሚኒስትሩን ''የመደመር ትውልድ'' የተሰኘ መጽሀፍ መግዛት ግዴታ ሆኗል። የ2ሺህ ብር ደመውዝተኛ መጽሀፉን 1500ብር እንዲገዛ ተፈርዶበታል። ክልሎች በጠቅላይ ሚኒስትሩ ርካሽ ተወዳጅነትን ለማትረፍ ከፍተኛ ሽያጭ አስመዘገብን የሚል ሪፖርት ለመላክ በሚል የህዝቡን ኪስ እያጠቡት ነው። መጽሀፉን ያልገዛ የሚኒባስ ሹፌር መውጪያ እንደሚከለከል ከወደምስራቅ ሀረርጌ ሰማሁ። ድሬዳዋ ላይ ባለሀብቶች ከ200ሺህ እስከ1ሚሊየን ብር በነፍሰወከፍ እንዲከፍሉ ደብዳቤ ተሰጥቶአአቸዋል። በየቦታው ተመሳሳይ ነው። በአንዳንድ አከባቢዎች የሰውዬውን መጽሀፍ አለመግዛት እንደሚያሳስር ተነግሮኛል። የሚገርመው ለመጽሀፉ ገንዘብ ይከፈላል እንጂ መጽሀፉን ማግኘት አይቻልም። ደምበኛ ዘረፋ ማለት ይህ ነው። በጠራራ ጸሀይ መንግስት ህዝብን ሲዘርፍ! ከዚያ ቴሌቪዥን ላይ ዲያቆን ዳንዔል ይመጣና ''ይህ የአምስት አመት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ማስታወሻ ኢትዮጵያን ለዘመናት ከተጣባት ደዌ የሚፈውስ በመሆኑ ለትወልድ ተሰንዶ መቀመጥ አለበት'' ይለናል።


ለማንኛውም የኦሮሚያ ብልጽግናና ህወሀቶች ፍቅራችሁን በልኩ አድርጉት። የትላንቱ እርግጫችሁ ተመልሶ የማይመጣበት ምንም ምክንያት የለም። አንዳንዴ ስትጣሉም ስትፋቀሩም ራሳችሁን ብትችሉ ደግሞ ለህዝቡ ትልቅ ውለታ ነው። ለገንዘቡና ለሞቱ ጊዜ የምትፈልጉት ህዝብ የበቃው ዕለት......አልጨርሰውም።
@ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን


ጥንቃቄ ይደረግ‼️


ይድረስ ለጎጃም ህዝብ በተለይም ለጎንቻ፣ እነብሴ እና መካነ ሰላም ወጣቶች:-
"""""""""""""""""
በቀድሞ ልዩ ኃይል አባላት ከተቋቋመዉ የዓባይ ሸለቆ ዘብ የተላለፈ ጥሪ:-
--------------------------------

የልዩ ኃይሉን መበተን ተከትሎ በቆራጥ የአካባቢው ተወላጅ ልዩ ኃይል አባላት የዓባይ ሸለቆ ዘብ በሚል የተደራጀው ኃይል ከአንጎት እስከ እነ እነገሽ፣ ከጎሸራ እስከ ወረያ ባለው ቀጠና ያለውን ህዝብ በማንቃት እና በማደራጀት ላይ እያለ በወረዳ ፖሊስ እና ጉጅሊ ተደጋጋሚ ትንኮሳ ተደርጎበታል::

ለአራት ግዜያት በእነገሽ፣ በበርላይ፣ አባ ሚኒወስ እና ወረያ አካባቢ የተደረገበትን የጉጅሊ እና ፖሊስ ከበባ ሰብሮ ካድሪ የላካቸውን ጉጅሌወች ማርኳል::

የአደረጃጀቱን ዓላማ በበጎ አሳቢ ወንድሞቻችን በኩል ለወረዳ ካድሬወች ለማስረዳት በተደረገው ጥረት እና ተኩስ የከፈተው የመንግስት ኃይል ላይ ባሳየነው አቅም ምክንያት የወረዳ አመራሮች ጉዳዩን ለማቀዝቀዝ ፍላጎት ያላቸው ቢሆንም የምስራቅ ጎጃም ሸክሞች አብርሃም አያሌው፣ ኮማንደር አያልነህ ተስፋዬ እና ፀረ-ህዝቡ ጌትነት አለልኝ አባይ ድልድይ አካባቢ አድማ በታኝ በመላክ ሲያዋጉን አድረዋል::

ለአማራ ህዝብ ነፃነት የተቋቋመው የዓባይ ሸለቆ ዘብ ከሮብ ለሃሙስ አጥቢያ ዛሬ ሌሊት ተኩስ ከፍቶ ያደረውን አድማ ብተና ኃይል ተገቢውን ትምህርት ሰጥቶታል::

ይሁን የዞናችን ህዝብ እድፍ የሆኑት እነኝህ ግለሰቦች መካናይዝድ የመከላከያ ጦር እንዲገባ ለመከላከያ አመራሮች ጥሪ እያደረጉ ይገኛሉ::

በመሆኑም የአካባቢው ወጣቶች ወደ መርጡ ለማርያም የሚወስደውን መንገድ ከሁለቱም አቅጣጫ በመዝጋት እና በአካባቢው ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎችን በማድረግ የትግላችን አካል እንድትሆኑ አስቸኳይ ጥሪ እናቀርባለን:: እንዲሁም የሬሽን አቅርቦት ችግር ያለብን በመሆኑ የአካባቢው ማህበረሰብ እንዲተባበር ሁሉም በያለበት ጥሪ እንዲያደርግ እናሳስባለን::

"መጭው ታሪክ በእኛ እጅ ይፃፋል" እንዲል ዘመነ ካሴ ታሪካችንን እንፃፍ! እንተባበር! እንበርታ!

ግንቦት 03 ቀን 2015 ዓ.ም
ዓባይ ሸለቆ


መረጃ አዲስ አበባ
=============

ሰላም እንዴት ነህ ።

"እኔ የምሰራበት ተቋምና የአዲስ አበባ ፖሊስ በጋራ በመሆን በርካታ ስራዎችን እንሰራለን። በዚህም አጋጣሚ ስራችንን ለማስፈፀም ከሆነ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት ሄደን አባላቶች ተመድበዉልን ወደ ስራ ስንሄድ ከበላይ አመራሮቻቸዉ የእርስ በእርስ መገናኛ ስልካቸዉ አደገኛ መልዕክት ሲተላለፍ ሰማሁ። መልዕክቱም በዚህ ሳምነት ማጠናቀቅ ካለብን የኦፕሬሽን ስራዎች ዉስጥ፦

1ኛ. በየቤቱ እየተዞረ ድንገተኛ ፍተሻ ማድረግ። በፍተሻዉም የሚገኙ ስለታም ነገሮችና ጦር መሳሪያ ይዞ ወይም ደብቆ የተገኘ ማንኛዉንም አካል በቁጥጥር ስር ማዋል።

2ኛ. ከክፍለ ሀገር የመጡ የቀን ሰራተኞች፣ ኮንትሮባንድ ነጋዴዎች(ልብስ፣ልዋጭ....)በተለያዩ ቦታዎች በየአደባባዩ የሚታዩ ፎጣ ለባሾችን መታወቂያ በመጠየቅ የያዙት መታወቂያ የታደሰ ከሆነ ራሳቸዉን ከተለያዩ ነገሮች እንዲያርቁ ማስጠንቀቅ፣ ያልታደሰ ከሆነ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ማስገባት።

3ኛ. በሁሉም ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች በሚገኙ በርካታ ጅምር ህንፃዎች ህገ-መንግስቱን በሀይል ለመናድ የሚታገሉ ሀይሎች መሰባሰቢያና የጦር መሳሪያ ክምችት ስላለባቸዉ ከሁሉም በተለየ ሁኔታ የተጠናከረ ፍተሻ ማድረግ የሚያሰጋ ሁኔታ ከተገኘ የህንፃ ተቋራጭ፣ የህንፃዉ ባለቤትና ሰራተኞቹን በቁጥጥር ስር በማዋል አስቸኳይ እርምጃ ሊወሰድ ይገባል።

የሚል አደገኛ መልዕክት ተላልፎ ወደ ስራ ስለተገባ ጥንቃቄ እንዲደረግ ለሚመለከተዉ አድርስልን" ይላል።


የሞቀ ከተማ ጥለን ጫካ የገባነው ዝንጀሮ ልናግድ አይደለም‼️

ንፁህ ልብስ አጥተን አዳፋና የተቦጫጨቀ ያጠለቅነው ወጣትነታችንን ያጣነው ተስፋም ስለቆረጥን አይደለም። በእኛ ትውልድ ያጣነውን ተስፋ በቀጣዩ ትውልድ እንዳይደገም ብለን ነው እንጂ።

የቀመልነው የቀጨምነው የነፃነት ዋጋው ስለገባን እንጂ እንደ ማንኛውም ወጣት ጠፍቶንም አይደለም።

የተራብነው የተጠማነው የወንዝና የኩሬ ውሃ የጠጣነው ደረቅ ብስኩትና ቆሎ በልተን ውለን የምናድረው መገርጣት ፈልገን ሳይሆን ነፃነት ከዳቦ በላይ እንደሆነ ስለገባንም ጭምር ነው።

እስርን ግርፍን ሞትን የናቅነው መኖር ስላልፈለግን ሳይሆን በእኛ መንገላታት ቁስልና ሞት መዳን ያለበት እጅግ በጣም የብዙ ህዝብ ልጆች ስለሆንን ብቻ ነው::

አሁን ትግል ብለን በረሃ የወረድነው በየጫካው እንደ አራዊት በደረስንበት የምናድረው የመንግስትን ስርዓት ለማስጠበቅ ሳይሆን ለራሳችን ህልውና ትግል ለመጀመርና ነፃነታችንን በደማችንና በክንዳችን ልናውጅ ህዝባችንንም አንገቱን ቀና እንዲያረግ እኛ ሞተን ትውልድ ይዳን ከሚል ትልቅ መርህ ቃላችን ነው።

እናሸንፋለን ስንል በቃ እናቸንፋለን ማለታችንም ነው::

ኃይላችን ያለው "ፋኖ" ከሚለው ትልቁ ስማችን ላይ ነው
ሲሳይ ሳታናው

ለተጨማሪ መረጃዎቻችን👇
𝙩𝙚𝙡𝙚𝙜𝙧𝙖𝙢:-👇
https://t.me/+SLQ8WQR1oKDGWBY
𝙛𝙖𝙘𝙚𝙗𝙤𝙤𝙠፦ https://www.facebook.com/beteamharamediaa/
𝙞𝙣𝙨𝙩𝙖𝙜𝙧𝙖𝙢:-👇
https://instagram.com/beteamharamedia?
𝙩𝙬𝙞𝙩𝙩𝙚𝙧:-👇 http://twitter.com/Beteamharamedia
𝙩𝙞𝙠𝙩𝙤𝙠:- 👇 @beteamaharamedia' rel='nofollow'>tiktok.com/@beteamaharamedia
𝙮𝙤𝙪𝙩𝙪𝙗𝙚:-👇 @beteamharamedia1475' rel='nofollow'>https://youtube.com/@beteamharamedia1475

Показано 20 последних публикаций.

4 219

подписчиков
Статистика канала