Bule Hora University


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Образование


Bule Hora University Official telegram

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Образование
Статистика
Фильтр публикаций


Call for Paper


ሚያዚያ 08/2016 ዓ.ም
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የግብርና ልማት ማዕከል በ2016 ዓ.ም የምርት ዘመን የተለያዩ ሰብሎችን መዝራት መጀመሩን ገለፀ፡፡
የዩኒቨርሲቲዉ ግብርና ልማት ማዕከል በ2016 ዓ.ም ለ2017 የምርት ዘመን ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ ምርጥ ዘርና ግብዓት በመጠቀም ስንዴና ሌሎች ሰብሎችን ለመዝራት ባቀደዉ መሰረት ሚያዚያ 05/2016 ዓ.ም በ20 ሄክታር መሬት ላይ ‹‹ቀቀባ›. የተባለ ምርጥ የስንዴ ዘርና በ10 ሄክታር ላይ ደግሞ ‹‹መልካሳ 2›› የተባለ ምርጥ የቦቆሎ ዘር መዝራት መጀመሩን የግብርና ልማት ማዕከሉ ዳይሬክተር መ/ር ቀመር ይማም አሳዉቀዋል።
የእርሻ ሥራዉ በሁለት ዙር ተከፍሎ ከ88 ሄክታር መሬት በላይ በዘር የመሸፈን ሂደት የሚከናወን መሆኑንና በተጨማሪም ጤፍ፤ቦሎቄ፤እና ድንች የሚያካትት እንደሆነም ተናግሯል፡፡
ግብርናን ማዕከል ተደርጎ የሚከናወኑ ተግባራት ለተቋሙ በገቢ ምንጭነት ከማገልገሉም በላይ ለመማር ማስተማሩና ለምርምር ስራ እንዲሁም ለማህበረሰብ አገልግሎት የሚዉሉ መሆናቸዉን ጠቅሰዉ በተለይም ዩኒቨርሲቲዉ ከማህብረሰብ አገልግሎት ጋር ተያይዞ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ በመሆኑ ለአካባቢዉ አርሶ አደሮች እንደ ሠርቶ ማሳያ እና የቴክኖሎጂ ሽግግር የሚያገለግል መሆኑንም የማዕከሉ ዳይሬክተር አሳዉቀዋል፡፡
በአጠቃላይ በሁለት ዙር ተከፍሎ ለሚዘሩ ሰብሎች ከ60 ኩንታል በላይ NPS እና UREA ማዳበሪያ ጥቅም ላይ የሚዉል መሆኑንና እንዲሁም ለአካባቢዉ አርሶ አደሮች ከሁለቱም ማዳበሪያ ዓይነቶች አስር-አስር ኩንታል እንደተሰጣቸዉ የማእከሉ ዳይሬክተር ያስረዱ ሲሆን በቀጣይ የተፈጥሮ ማዳበሪያን ጥቅም ላይ ከማዋል አንፃርም በስፋት የሚሠራ ስለመሆኑ ተናግሯል፡፡

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ


Hordoftoonni Amantaa Muslimaa Yuunivarsiitii Keenya keessa jirtan Barattoonni,Barsiissootni, Hojjattoonni Bulchiinsaa fi Haawaasa Muslimaa biyya alaa fi keessa jirtan hundi baga ayyaana Iid Al-Faxirii kan Bara 1445ffaan nagayaan geessan jechaa
Jinii Soomaa kan guyyaa soomaan, halkan immoo waaqa kadhachaa waliif yaadaa, kan beela’e nyaachisuufi kan harkaa qaban waliin qooddachuun, kan daare uffisuufi kan dhibame gaafachuun, nagaa fi nageenya buusuuf, qaamaa fi qalbiin wal bira dhaabbachuun kan itti dabarsan ji’a guddaa fi jaallatamaa ture.
Hordoftoonni Amantaa Muslimaa ji’a kabajamaa kana ilaalchisnee irra deebi'uun baga nagayaan geessan, baga waliin geenye jechuun barbaada.
Ayyaanni Sooma Hiikaa waggaan 1445ffaan yeroo nagaa fi araara itti labsinudha.Nageenyi bu'uura waan hundaa waan ta'eef.
Doktor Birhaanu Lammaa
(Pireezidaantii Yuunivarsiitii Bulee Horaa)


ውድ የዩኒቨርሲቲያችን መምህራን፣ የአስተዳደር ሠራተኞችና ተማሪዎች እንዲሁም በሀገር ዉስጥና ዉጪ ለምትገኙ መላው የሙስሊም እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1ሺ 445ኛዉ ኢድ ኣል ፈጥር በዓል በሠላም አደረሳችሁ እያልኩ፣ በዓሉ የሠላም፣ የፍቅር፣ የመቻቻልና የአብሮነት እንዲሆንልን ከልብ እየተመኘሁ ቀደም ሲል በአብሮነት፣በመቻቻልና በፍቅር በዩኒቨርሲቲያችን ትምህርታችሁን በሰላምና በመረጋጋት በመከታተል እንደቆያችሁ ሁሉ ከዚህ በኋላም ለሚጠብቃችሁ የትምህርት ጊዜና የመዉጫ ፈተና ጥንክራችሁ እንድትሰሩ አባታዊ ምክሬን እለግሳለሁ።
በድጋሜ እንኳን አደረሳችሁ!
ዶክተር ብርሃኑ ለማ
(የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት )


ሴቶችን እናብቃ፣ ሰላምና ልማትን እናረጋግጥ "በሚል መሪ ቃል ለ48 ጊዜ በኢትዮጵያ የሚከበረውን የአለም የሴቶች ቀን በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲም ነገ በ06/07/2016ዓ.ም ይከበራል። ሁላችሁም እንድተገኙ ተጋብዛችኋል።


የካቲት 24/2016 ዓ.ም
የሃዘን መግለጫ
ወይዘሮ መሰረት አለሙ ከእናቷዋ ከወይዘሮ ጣይቱ ቢሎ እንዲሁም ከአባቱዋ ከአቶ አለሙ በዳሶ በ1980 ዓ.ም በምዕራብ ጉጂ ዞን በቡሌ ሆራ ወረዳ በሙሪ ቱርቁማ ቀበሌ ተወለዱ። ወይዘሮ መሰረት አለሙ እስከ ህልፈተ ህይወታቸው ድረስ በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በላይብረሪና ዲክመንቴሽን ዳይሬክቶሬት ክፍል ውስጥ አቴንዳንት በመሆን በታማኝነትና በቅንነት ያገለገሉ ሲሆን፣ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ትላንት የካቲት 23/2016 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በወ/ሮ መሰረት ሞት የተሰማውን ሀዘን እየገለፀ ለመላው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ፣ ለወላጅ ዘመድ እንዲሁም ለጓደኞቿ መጽናናትን ይመኛል።

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ


የካቲት 24/2016 ዓ.ም

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ከተሾሙት ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ ጋር የትውውቅ ሥነ-ሥርዓት ተካሄደ፡፡

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በመንግስት የተሠጠውን አዋጅ ተከትሎ ማናቸውንም በዩኒቨርሲቲው የሚከናወኑ ተግባራትን በቦርድ አፅድቆ እያከናወነ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ቀደም ሲል የዩኒቨርሲቲው ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ዶ/ር ስዩም መስፍን በመልቀቃቸው ምክንያት በምትክ የዩኒቨርሲቲው ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ከተሾሙት የሠላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ ጋር አዲስ አበባ ካፒታል ሆቴል ስብሰባ አዳራሽ ከቦርድ አባላትና ከዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ጋር የትውውቅ ሥነ-ሥርዓት ተከናዉኗል፡፡

የትውውቅ ስነ-ሥርዓት ከተካሄደ በኃላ የዩኒቨርሲቲው የ2016 ዓ.ም የግማሽ ዓመት የሥራ ክንውን ሪፖርት በዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃኑ ለማ አማካኝነት ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን በዋናነትም የመማር ማስተማሩን ተግባር ጨምሮ በማህብረሰብ አገልግሎት፣በጥናትና ምርምር፣ በመልካም አስተዳደርና በአለም አቀፋዊነት ዙሪያ በስፋት ውይይት ተደርጓል:: የቦርዱ ሰብሳቢ ዶ/ር ከይረድን ተዘራም ቀጣይ ሥራዎች ተጠናክሮ በሚቀጥሉበት ሁኔታ ላይ የሥራ መመሪያ ሰጥቷል፡፡

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ


የካቲት 19/2016 ዓ.ም

የ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት የቀሪ ስድስት ወራት በተከለሰው ዕቅድ ዙሪያ ውይይት ተደረገ።

ዩኒቨርሲቲው በቅርብ ጊዜ የ2016 ዓ.ም የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ በማካሄድ በቀጣይ ስድስት ወራት ትኩረት ተሰጥቶ መከናወን ባለባቸዉ ሥራዎች ዙሪያ አቅጣጫ ማስቀመጡን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ራሱን የቻለ ኮሚቴ ተዋቅሮ ከባለፈው ዕቅድ ግምገማ በመነሳት በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶ መከናወን ባለባቸው ሥራዎች ዙሪያ ዕቅዱን ክለሳ በማድረግ የበለጠ ላማዳበር ለውይይት የቀረበ ስለመሆኑ የዕቅድና በጀት ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መሰለ አለማየሁ ተናግሯል፡፡ የዕቅድ ክለሳው የተቋሙን ነባራዊ ሁኔታ በቅድሚያ የዳሰሰ እና በዋናነት የመማር ማስተማሩን ተግባር ማዕከል በማድረግ ከበጀት ጋር በሚጣጣም መልኩ በዋና ዋና ግቦችና ስትራቴጅክ ዓላማዎች ተዘርዝሮ የቀረበ መሆኑንም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

አቶ መሠለ አያይዘውም ተከልሶ የቀረበው ዕቅድ አዲሱን የሰው ኃይል ምደባና የሥራ ዘርፎችን ታሳቢ በማድረግ የተዘጋጀ መሆኑንና እያንዳንዱን የሥራ ክፍልም ያካተተ ስለመሆኑ አስረድተዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃኑ ለማ ተገኝተው በቀሪ ወራት ትኩረት ተደርጎ መሠራት ባለባቸው ሥራዎች ዙሪያ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን በአዲሱ የሰው ኃይል ምደባ መሠረት በሥራ አስፈፃሚ መደብ ላይ ተወዳድረው ያለፉ ኃላፊዎችም ተሣታፊ ሆነዋል፡፡

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ


የካቲት 19/2016 ዓ.ም

ማስታወቂያ
በተለያዩ የሃላፊነት ቦታዎች ላይ ያመለከታችሁ የአካዳሚክ ዘርፍ አመልካቾች በሙሉ
ነገ የካቲት 20/2016 ዓ.ም ከሰዓት 8:00 ሰዓት ላይ ሰኔት አዳራሽ እንድትገኙ እናሳስባለን::

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ


የመውጫ ፈተና(Exit Exam) ውጤት በተመለከተ

በ2016 ዓ.ም ዓመት የመውጫ ፈተና የወሰዳችሁ ተማሪዎች ውጤታችሁን ለማየት ከታች ያለውን ሊንክ ተጠቀሙ፦

https://result.ethernet.edu.et/


February 20/2014

Bule Hora University hosts University of Venda delegation

Bule Hora University received a delegation of 20 higher officials and students from the University of Venda in South Africa on February 20, 2024. The visit was part of a Memorandum of Understanding (MOU) signed between the two universities to collaborate on various academic and research issues.

The Bule Hora University president, Dr. Birhanu Lema, the Vice President of Academic, Research, Technology Transfer and Community Service, Dr. Tinsae Tamrat, and other staff members welcomed the Venda team at Hawassa Airport.

The Internationalization Directorate of BHU said that the University Of Venda delegation arrived at a special time, as they would witness the 75th power transfer of the Gujii Oromoo Gadaa Baallii, Indigenous Oromo Democratic governance sytem.
The Directorate also said that they looked forward to exchanging experiences and knowledge with the BHU students and leaders during their stay.

Bule Hora University


05/06/2016 E.C
For Exit Exam Examinees

Bule Hora University


የካቲት 02/2016 ዓ.ም

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የተለያዩ ሰብሎችን ለመዝራት የእርሻ ሥራ ጀምሯል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተሻሻሉ የግብርና የእርሻ መሣሪያዎችን እና ግብዓቶችን በመጠቀም ሥራዎችን አጠናክሮ እየሰራ መሆኑ ይታወሳል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ በ2016 ዓ.ም ይህንኑ በስፋት በመቀጠል ስንዴና ሌሎች ሰብሎችን ለመዝራት የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃኑ ለማ እና የግብርና ልማት ማዕከል ኃላፊ መ/ር ሀሮ አዱላ በተገኙበት የእርሻ ሥራው ተጀምሯል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የልህቀት ማዕከል አድርጎ ከሚሰራባቸው ተግባራት አንዱ ግብርና መሆኑን የጠቀሱት ዶ/ር ብርሃኑ ለማ በአሁኑ ሰዓት የተጀመረው የእርሻ ሥራ ለመማር ማስተማሩ እንደ ምርምር ማዕከል ሆኖ ከማገልገሉም በላይ እየታየ ያለውን የዋጋ ንረት ከመቀነስና በተለይም መንግስት የስንዴ አቅርቦትን በሀገር ዉስጥ አምራቾች ብቻ ለመሸፈን እያደረገ ያለውን ጥረት የሚደግፍ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ

Показано 13 последних публикаций.