🔜ለዘላለም ሕይወት ተጠርታችኀል፡፡
🔵በዚህ ዘመን ያለው አማኝ አብዛኛው ሕይወት በምድር ላለው ብቻ ልቡን እየሰጠ ይገኛል፡፡ ምድራዊ ሕይወት ሁሉ የሚያል የሚጠፋ መሆኑን ዘንግተዋልክርስቶስን ለዚህ ለሚታየው አለም ብቻ ተስፋ አድርገነው ከሆነ ተሳስተናል፡፡ እርሱ እኛን የጠራን ከፍ ላለ ክብር ነው፡፡
🔵ነገር ግን ያንን ክብር እንዳያዩ የዚህ አለም የኑሮ ስርዕት መንፈሳዊ ዐይናቸውን ከድኖባችዋል፡፡ እግዚአብሔር በልጁ የጠራን ለምድራዊ ሕይወት አይደለም፡፡ በዚህ ምድር ሳለን መጻተኞች ነን፡፡ በአለም ሳለን እንግዳ ነን፤ በአለም ሳለን ተጓዦች ነን፡፡
🔵በምድር ሳላችሁ እንግዶች ናችሁ! ሲል አሁን ያላችሁበት ሕይወት ጊዜአዊ ነው፡፡ ሌላ ለእናንተ የሚመጥን የሕይወት አይነት አለ እያለ ነው፡፡ በምድራዊ ሕይወት አትርኩ፤ በክርስቶስ የተገኘ እግዚአብሔር የሚኖረውን የሕይወት አይነት አለ፡፡ ዘላለም መኖር ማለት ዝም ብሎ መኖር መኖር ብቻ ሳይሆን የኑሮ አይነታችን እንደ እግዚአብሔር ነው፡፡
🔵እርሱ ዘላለማዊ ስለሆነ እናንተም ከእርሱ የተነሳ ዘላለማዊ ሁናችሁኀል፡፡ ለዚህ ነው መጽሐፍ እንዲህ የሚለው“ከክፉ ምኞት የተነሣ በዓለም ካለው ምግባረ ብልሹ ሕይወት አምልጣችሁ ከመለኮታዊ ባሕርይ ተካፋዮች እንድትሆኑ በእነዚህ ነገሮች አማካይነት እጅግ ታላቅና ክቡር የሆነውን ተስፋ ሰጥቶናል።”2ኛ ጴጥሮስ 1፥4
ከመለኮት ባህሪይ የተካፈላችሁት አንዱ የእርሱ አይነት ሕይወት ነው፡፡ ዘላለም ከእኛ የመጣ ሳይሆን በክርስቶስ የተገኘ የራሱ የእግዚአብሔር መለኮታዊ ባህሪይ ነው፡፡ ስለዚህ ይሄን ሕይወት ተካፍላችኀል፡፡
🔵አልተገነዘባችሁም እንጂ እግዚአብሔር እኮ ለትልቅ ክብር ነው የጠራችሁ፡፡ ስሙ የስጋ አባቶቻችሁ እንኳን ለእናንተ የበለጠውን ያስባሉ፤ እንዴት የሰማይ አባታችሁ ከእነርሱ አብልጦ አያስብም! የሚገርመው ከስጋ አባቶቻችሁ ንብረት፣ ቤት፣ መሬት፣ ገንዘብ ልትወርሱ ትችላላችሁ፡፡ በፍጹም ግን አባታችሁን ልትወርሱት አትችሉም፡፡ የእርሱ የሆነውን ነገር ልትወርሱ ትችላላችሁ እርሱን ግን አትወርሱትም፡፡
🔵የሰማዩ አባታችሁ ግን እዩት ምን እንዳወረሳችሁ“ልጆች ከሆን ወራሾች ደግሞ ነን፤ የክብሩ ተካፋዮች እንሆን ዘንድ በርግጥ የመከራው ተካፋዮች ብንሆን፣ የእግዚአብሔር ወራሾች፣ ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ነን።”
ሮሜ 8፥17፤ የራሱ የእግዚአብሔር ወራሾች ናችሁ፡፡ ዋው! የሚደንቅ ነው፡፡ ለካ ልጅ በመሆናችሁ ሰማይ፣ የወርቅ መንገድ፣ ጸሐይ፣ ወይም ዳይመድ አይደለም ከእርሱ የምትወርሱት፡፡ እራሱን እግዚአብሔርን ነው የምትወርሱት፡፡
🔵እራሱን መውረስ ማለት፤ እርሱ ማነው ጻዲቅ ነው፡፡ ጽድቅን ደግሞ በክርስቶስ በማመናችሁ ብቻ ወርሳቹኀል፡፡ እርሱ ማነው? ቅዱስ ነው፡፡ እርሱ ማነው? ለዘላለም የሚኖር ነው፡፡ እርሱ ማነው? ፍቅር ነው፡፡ እርሱ ማነው? ቸር ነው፡፡ #ከአምላክነቱ_በቀር! እናንተ የእርሱ ወራሾች ናችሁ፡፡ ማንም በክርስቶስ ኢየሱስ ቢያምን ከክርስቶስ ጋር ሁኖ የእግዚአብሐር ወራሽ ይሆናል፡፡
🔵ይሄ ሕይወት የጀመረው ጌታን የተቀበልን እለት ነው፡፡ ነገር ግን አሁን አብዛኛው ክርስትያን በሚጠፋው አለም የሕይወት ስርዕት ውስጥ ተዘፍቀዋል፡፡ ብዙ ሰዎች የሕይወት ትርጉም አልገባቸውም! ሕይወት ለእነርሱ መብላት፣ መጠጣት፣ መልበስ፣ ከሰው እኩል ሁኖ መገኘት፣ ገንዘብ ማግኘት፣ አሪፍ ትዳር መያዝ፣ መጨረሻ መሞት፡፡ ከሞት በኃላ ሲባሉ! እርሱን ፈጣሪ ያውቃል በማለት እራሳቸውን ያታልላሉ፡፡
🔵አንድ የውጭ ሰው ምስክርነት ሲሰጥ ሰማሁት! እንዲህም አለ፥ በሕይወቴ የሆነ ቦታ ስገባ በጣም ደስተኛ የምሆን ይመስለኝ ነበር፡፡ እናም ሃያ ስኩል ስማር እንዲህ እል ነበር ዩኒቨርስቲ ስገባ ነው የሕይወት ጣዕም የማገኘው፤ ከቤተሰብ ስለይ ትክክለኛውን ሕይወት እኖራለው እል ነበር፥ ወጤትም መጣልኝ ግቢም ገባው ስገባ ግን ከትንሽ ጊዜ በኃላ ያ የጠበቁት ሕይወት በዛ ውስጥ አላገኘሁትም ነበር፡፡ ስለዚህ እንዲህ አልኩ! ልክ ተመርቄ ስወጣ ያ የጎደለውን ሕይወት አገኘዋለው አልኩ! ተመርቄም ወጣው አሁንም ፍጹም ደስታን አላገኘሁም ነበር፡፡
🔵በሕይወቴ የሆነ የጎደለኝ ነገር እንዳለ ይሰማኝ ስለነበር፥ ይሄ ስሜት በምን እንደሚያርፍ መፈለጌን አልተውኩም ነበር፡፡ አሪፍ የፍቅር ጓደኛ ከያዝኩ ሕይወቴ የማረ ይሆናል ብየም አሰብኩ፤ ጓደኛም ያዝኩ! ነገር ግን ፍጹም ደስታውን በዛ ውስጥ አላገኘሁትም ነበር፡፡ ከተጋባን በኃላ ልጅ ስንወልድ ያን ሕይወት አገኘው ይሁን ብየ አሰብኩ! ተጋባን ወለድኩ፡፡ አሁንም ፍጹም ደስታን አላገኘሁም ነበር፡፡
🔵በፍጹም በእነዚህ ውስጥ የሕይወት ትርጉም አላገኘሁም ነበር፡፡ እኔም በጎደሎ የሕይወት አይነት እየኖርኩ ሳለ አንድ ቀን ወንጌል ሰማው ጌታንም አመንኩ፡፡ ከዛን ቀን ጀምሮ ለዘመናት ያላገኘሁትን የሕይወት ትርጉም አገኘሁት፡፡ ፍጹም ደስታን አገኘው፡፡ በማለት እግዚአብሔርን አመሰገነ፡፡
🔵በዚህ ቻናልም ሆነ ይሄን መልእክት የምታነቡ ሁሉ፤ የማረ ህይወት የማ
ሚኖረኝ ተመርቄ ስወጣ፣ ስራ ስቀጠር፣ ጥሩ ትዳር ስይዝ፣ ልጆች ስወልድ፣ ባለሀብት ስሆን ብላችሁ አቅዳችሁ አስባችሁ ከሆነ እመኑኝ በፍጹም ደስተኛ አትሆኑም፡፡ ፍጹም ያማረና ጣፋጭ ሕይወት የሚገኘው በክርስቶስ ኢየሱስ ውስጥ ነው፡፡ ምንም ባይኖራችሁ፤ የሁሉም ባለቤት የሆነው ጌታ ካላችሁ ሌላ ምን ትፈልጋላችሁ!
🔵የምትፈልጉት ሁሉ ያለው፥ በክርስቶስ ውስጥ ነው፡፡ ሰይጣን እንኳን የእርሱ የሆነ ነገር የለም፡፡ ሁሉም የእግዚአብሔር ነው፡፡
©🔰የዘላለም ህይወት🔰[Eternal_Life]
🎸🎸 @CLREthiopia 🎸🎸