CNN News አማርኛ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана



Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


Репост из: Ethiopian Digital Library
የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት

የ28 አመቷ ረድኤት አበበ በኒውዮርክ ከሚገኘው ኮርኔል ዩኒቨርሲቲ በዶክትሬት ዲግሪ በመመረቅ የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት የሚል ታሪክ አስመዘገበች

ረድኤት በዩኒቨርሲቲው በዶክትሬት የተመረቀችው በኮምፒውተር ሳይንስ ነው፡፡ እንደአትላንታ ብላክ ስታር ዘገባ ይህች ወጣት ዶክትሬቷን የሰራችው የኮምፒውተር ቀመርንና ሰው ሰራሽ አስተውሎትን በእኩልነትና በማህበራዊነት እንዴት መጠቀም እንደሚቻል ባተኮረ ምርምር ላይ ነው፡፡

ረድኤት ከዚህም በተጨማሪ በሰው ሰራሽ ክህሎት ላይ የሚሰራው ኤን አይኤች አማካሪ ኮሚቴ ውስጥ አባል ስትሆን ብላክ ኢን ኤአይ የተሰኘ መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም ከመሰረቱት መካከልም ናት፡፡

የመመረቂያ ስራዋን በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እኩልነት ላይ ለመስራት የተነሳሳችው በትውልድ አገሯ ካየችው እውነታ በመነሳት እንደሆነ ተናግራለች፡፡

በአዲስ አበባ ከትልቅ ቪላ አጠገብ የላስቲክ ቤት እንደሚታይና የገቢ እኩልነት እንደሌለ መታዘቧን የገለፀችው ረድኤት ይህ በመላው አለም ያለ መሆኑን ስትረዳ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መስክ እንዳይደገም በማሰብ መመረቂያዋን በዚህ ላይ መስራቷን አስረድታለች፡፡

ረድኤት የመጀመሪያ ዲግሪዋን በማቲማቲክስ ያገኘችው ከሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ሲሆን በካምብሪጅ ዩኒቨርስቲ በዚሁ ትምህርት ማስተርሷን ሰርታለች፡፡ በተጨማሪም ከሀርቫድር ዩኒቨርስቲ በአፕላይድ ማቲማቲክስ ሌላ ማስተርስ አላት፡፡
#MR

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library


Репост из: Ethiopian Digital Library
ታላቅ የምስራች አዳዲስ የስራ ፈጠራ ሀሳብ ላላችሁ በሙሉ!

ታታሪዎቹ/ቀጠሌዋን የሁለተኛ ዙር የአዋሽ ባንክ የስራ ፈጠራ ውድድር ለመሳተፍ የማመልከቻ ጊዜ ከጥቅምት 12 እስከ ህዳር 13 ቀን 2016 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ አዳዲስ እና ችግር ፈቺ የሆኑ የስራ ሀሳቦች ያላችሁና በ Online ማመልከት ለምትፈልጉ 👇👇
https://tatariwochu.awashbank.com እንዲሁም በአካል ማመልከት ለምትፈልጉ በአቅራቢያችሁ ወደሚገኘው የባንካችን ቅርንጫፎች በመቅረብ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን በታላቅ አክብሮት እናሳውቃለን፡፡

Awash Bank

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library


የአዲስ አበባ አንድ ችግር ጫኝ እና አውራጅ መፍትሄ ሊሰጠው ነው
ሰው በንብረቱ የሚዘረፍበት፣የሚደበደብበትና ህይወቱንም የሚያጣበት ተግባር እየሆነ ነበር
   
በከተማዋ የሚገኙ ጫኝና አውራጆች የሚተዳደሩበት ደንብ ማፅቁን የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አከባቢዎች በተለይም በጋራ መኖሪያ አካባቢ ለጫኝና አውራጅ አካላት የሚከፈለው ገንዘብ እንዳማረራቸው ነዋሪዎች በተደጋጋሚ ሲገልፁ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡

ታድያ የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ይህንን ህብረተሰቡን ያማረረ ድርጊት ፈር ለማስያስዝ ደንብ በማውጣት ማፅደቁን አስታውቋል፡፡

በከተማዋ ይሰሩ የነበሩት ጫኝና አውራጆች ከዚህ ቀደም በስራ ዕድል ፈጠራ ስር የነበሩ ሲሆን፣ ከተደራጁበት ዓላማ ውጪ ህብረተሰቡን ከማማረርም ባለፈ ለሰላምና ፀጥታ ስጋት ሆነው መቆየታቸውን የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ ተናግረዋል፡፡

ይህንን ለመቆጣጠርም ጫኝና አውራጆችን ከማደራጀት ጀምሮ፣ የመቆጣጠርና የመከታተል ስራ በሰላምና ፀጥታ ቢሮ ስር እንዲሆን መደረጉን አንስተዋል፡፡

በ11ዱም ክፍለ ከተሞች የሚገኙትን ማህበራት የማፍረስ ስራ በመስራት ጫኝና አውራጆችን መልሶ የማደራጀት ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

የማድራጀቱ ስራ ከተጠናቀቀ በኃላ ደንብ የወጣላቸው መሆኑና በአዲስ አበባበ ፍትህ ቢሮ የፀደቀ መሆኑን የተናገሩት ወይዘሮ ሊዲያ፣ በደንቡ ዙሪያ በተከታታይ ስልጠና እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡

በፍትህ ቢሮ የፀደቀው  ደንብ ላይም የጫኝና አውራጅ ስልጣንና ሀላፊነት እንዲሁም ለእያንዳንዱ ዕቃ ለማውረድም ሆነ ለመጫን ተመን ወጥቶለት ቁርጥ ክፍያ እንዲከፈል እንደሚደረግም ጨምረው ገልፀዋል፡፡

ይህ ደንብ ወደ ተግባር በሚገባበት ወቅት አሁን ላይ በጫኝና አውራጅ ማህበራት እና በማህበረሰቡ መካከል ያለውን ችግር በዘላቂነት ሊያሥቀር የሚችል መሆኑን  ሀላፊዋ ተናግረዋል፡፡


" ... ሕገወጡ የድርጅቱ #ኦንላይን_ሲስተም ሙሉ በሙሉ ተቋርጦ ፕሮፌሽናል በሆኑ የሙያ ተቋማት በአዲስ መልክ መልማት ይኖርበታል " - አምባሳደር ሱሌማን ደደፎ

ከሰሞኑ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ታምሩ ግንበቶ አዋልሶ ጨምሮ 42 የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አመራሮች እና ሠራተኞች ከሙስናና ሕገወጥ ተግባር ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ማዋላቸው ይታወቃል።

ይህንን በተመለከተ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡ ይገኛል።

#የግል አስተያየታቸውን ካጋሩት ውስጥ የቀድሞ በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ (UAE) የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ያገለገሉት ሱሌማን ደደፎ አንዱ ናቸው።

አምባሳደር ሱሌማን ፤ የተወሰደው እርምጃ የዘገየ ቢሆንም የይበል የሚያሰኝ ነው ብለዋል።

ነገር ግን ይህ ብቻውን በቂ እንዳልሆነ ገልጸዋል።

" እነዚህ ሰዎች ዘርግተው የሚጠቀሙበትና በበርካታ ደላሎች የሚሠራበት ሕገወጡ የድርጅቱ #ኦንላይን_ሲስተም ሙሉ በሙሉ ተቋርጦ ፕሮፌሽናል በሆኑ የሙያ ተቋማት በአዲስ መልክ መልማት ይኖርበታል " ብለዋል።

አምባደሩ ፤ " ዛሬም የኢትዮጵያ ፓስፖርት በበርካታ የመካከለኛው ምሥራቅ እና የባሕረ ሰላጤው ሀገራት በደላሎች ሱቆች ውስጥ በይፋ በመቸብቸብ ላይ ይገኛል  " ሲል ገልጸዋል።

" ዜጎቻችን ፓስፖርታቸውን ለማሳደስ እስከ 60,000 ብር የሚጠየቁበት፣ ከቪዛና ከፓስፓርት እድሳት እያንዳንዱ አገልግሎት ጠያቂ $100 ዶላር ላልታወቀ ግለሰብ ወይም ተቋም የሚከፍልበት አሠራር ዛሬም ስላለ በሥራ ላይ ያለው የኦንላይን ሲስተም scrap ተደርጎ በአዲስ መተካት ይኖርበታል። " ብለዋል።

ኦንላይን የቪዛ ጥያቄ አሁንም ሁለት ሦስት ጊዜ ካልተከፈለበት መልስ እንደማይሰጥ ይታወቃል ሲሉም አክለዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ፤ አምባሳደር ሱሌማን ደደፎ ፤ ከክልል እስከ ፌዴራል ያሉት ሁሉም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በጥብቅ መፈተሽ አለባቸው ብለዋል።

" ካሉን ቁልፍ የደህነት ተቋማት መካከል የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ መ/ቤት ምን ዓይነት ውርደት/ውድቀት ውስጥ እንደከተተን አይተናል። " ያሉት አምባሳደሩ " ተቋሙ ብቻውን ለዚህ አልበቃም፤ የባሰም እንዳለ ምንም ጥርጥር የለውም፣ በየዕለቱ የምናየውና የምንሰማው ጉዳይ ስለሆነ። " ሲሉ ገልጸዋል።

" ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ በሕጋዊ መንገድ ለማደስ ሁለት ሚሊዮን ብር ጉቦ የሚጠየቅበት አገር ውስጥ መሆናችንን ስናስብ እጅግ በጣም እንደነግጣለን "ም ብለዋል።

" መንግሥት ብዙ ቅድሚያ የሚሰጣቸው (Priorities) ቢኖሩትም የሥልጣን ብልግናና የአስተዳደር በደሎች፣ በተለይም ሌብነት አሁን ቅድሚያ ከምንሰጣቸው ጉዳዮች መካከል መሆን ይኖርባቸዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

በዚህም ኢሚግሬሽን ብቻውን እንዳልበሰበሰ ታውቆ ከክልል እስከ ፌዴራል ያሉት ሁሉም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በጥብቅ መፈተሽ አለባቸው ሲሉ አስገንዝበዋል።


በእስራኤል እና በፍልስጤም ሃማስ መካከል የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አሳየ

በእስራኤል እና በፍልስጤም ሃማስ መካከል የተቀሰቀሰውን ከፍተኛ ጦርነት ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ መታየቱ እየተዘገበ ይገኛል።

በዚህም እስራኤል በጋዛ ያለው ኹኔታ ከመካከለኛው ምስራቅ የሚነሳውን የነዳጅ አቅርቦት ሊያስተጓጉል ይችላል በሚል ስጋት፤ ዛሬ ሰኞ የአንድ በርሜል ብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ላይ በ 4 በመቶ ጭማሪ መታየቱ ተነግሯል።

ባለፉት ሳምንታት ወደ 96 ዶላር ደርሶ የነበረው የአንድ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ባለፉት ቀናት ጥሩ የሚባል ቅናሽ አሳይቶ የነበረ ሲሆን፤ ነገር ግን ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ በኃላ የነዳጅ ዋጋ ዛሬ በ4 ነጥብ 53 በመቶ ጭማሪ አሳይቶ፤ 88 ነጥብ 41 ዶላር መድረሱን ሲኤንቢሲ ዘግቧል።

የአሜሪካን የነዳጅ ዋጋ ማሳያ ተደርጎ የሚወሰደው ዌስት ቴክሳስ ኢንትርሚዲየት የተሰኘው ተቋም አንድ በርሜል ነዳጅ በ4 ነጥብ 69 በመቶ ጨምሮ ወደ 88 ነጥብ 67 ዶላር ከፍ ማድረጉም ተነግሯል።

በእስራዔልና በፍልስጤሙ ሃማስ መካከል የሚካሄደው ጦርነት ወደ ሙሉ ውጊያ ከተቀየረ ኹለተኛ ቀኑንያያዘ ሲሆን፤ ጦርነቱ በደቡባዊ እስራዔል ሦስት ሥፍራዎች ተፋፍሞ መቀጠሉ ተገልጿል፡፡

ጦርነቱ እስካሁን ቢያንስ የ1 ሺህ 113 ሰዎችን ሕይወት መቅጠፉየተገለጸም ሲሆን፤ ሕይወታቸውን ካጡት መካከል 413ቱ ፍልስጤማውያን ሲሆኑ፤ 700ዎቹ ደግሞ እስራዔላውያን መሆናቸው ተነግሯል፡፡

@cnn_amharic1


ይጠንቀቁ‼

በአዲስ አበባ ሌቦች ሊሰርቋቹ ሲያስቡ ከሚጠቀሙት ዘዴዎች መካከል:—
👇 👇 👇
✔ሞተር እና ሳይክል ወደ እርሶ ሲጠጋ ይጠንቀቁ ስንቱ ስልኩን ተበልቷልና።

✔የማያውቆት ሰው ፀያፍ ስድብ ይሰድቦታል። ለመጣላት ሲጋበዙ ገላጋይ መስለው የተሳዳቢው ተባባሪ ሌቦች ኪሶትን ያጥቦታል።

✔ ታክሲ ውስጥ ሆን ብለው የታመመ ወይም ነፍሰ ጡር የሚመስል ሰው አስቀምጠው መስኮት እንዲከፍቱ በጥድፊያ ይጠይቆታል ። እርሶም መስኮቱን ሲከፍቱ ወይም ቦታ ለመቀየር ሲያስቡ ኪሶት ይገባሉ።

✔ የታክሲ ረዳት በመመስል "የት ኖት " ብለው በሚያልፉበት መንገድ ይጠይቆታል። እርሶ ወደጠሩት ቦታ እንደሚሄዱ በማስመሰል ታክሲ ካስገቦት በኋላ ዘርፈው ደብድበው ያወርዶታል።

✔ አውቀው በታክሲ ትርፍ እንዲጫኑ ካደረጉ በኋላ " ትራፊክ መጣ፣ውረድ ፣ውረጂ " በማለት አዋክበው አውርደው በመሀል ገንዘቦትን ወይም ሞባይል ስልኮትን ይሰርቆታል።

✔ አሁን አሁንማ ማር ፣ቅቤ ተልኮለት ነው በማለት እቤት ሰተት ብለው ገብተው የላከኝን ሰው ልንገረው ስልኮትን አውሱኝ በማለት ያልተሰማቸው በማስመሰል ሹልክ ብለው ያመልጣሉ።

✔ መንገድ ላይ አጣዳፊ ካልሆነ ስልክ ባያወሩ ይመረጣል። መንታፊው በዝቷልና።

✔ ሎተሪ ደረሰኝ ብሎ ወይም የማያውቁት ሰው መንገድ ላይ እያወሮት ሲሄድ ይጠንቀቁ።

@cnn_amharic1
@cnn_amharic1


Do you enjoy reading this channel?
Perhaps you have thought about placing ads on it?
To do this, follow three simple steps:
1) Sign up: https://telega.io/c/cnn_amharic1
2) Top up the balance in a convenient way
3) Create an advertising post
If the topic of your post fits our channel, we will publish it with pleasure.




እንኳን ለ2016 አዲስ ዓመት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

አዲሱ አመት የጤና ፣ የሠላም ፣ የዕድገትና የስኬት ይሁንላችሁ!

መልካም አዲስ አመት!

@cnn_amharic1
@cnn_amharic1


ጥንቃቄ❗️
ከባዕድ ነገሮች ጋር የተቀላቀለ 1 ሺህ 440 ኪሎ ግራም ቅቤ ተያዘ‼️
በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ከባዕድ ነገሮች ጋር የተቀላቀለ 1 ሺህ 440 ኪሎ ግራም ቅቤ መያዙን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

በተጨማሪም ከቅቤ ጋር ሊቀላቀል የነበረ ንጽህናው ያልተጠበቀ 3 ሺህ 360 ኪሎ ግራም የአትክልት ቅቤ እና ፓልም ዘይት መያዙን ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አየርጤና እና ቻይና ካምፕ አካባቢዎች በተደረገ ቁጥጥር እንዲሁም በህብረተሰቡ ጥቆማ ነው ከባዕድ ነገር ጋር የተቀላቀለ 1 ሚሊየን ብር ዋጋ ያለው ቅቤ የተያዘው፡፡

በተጨማሪም ከ650 ሺህ ብር በላይ ዋጋ ያለው ከቅቤ ጋር ለመቀላቀል የተዘጋጀ ንጽህናው ያልተጠበቀ የአትክልት ቅቤ እና የፓልም ዘይት መያዙን የባለስልጣኑ መረጃ ያመላክታል፡፡ከበዓላት ጋር በተያያዘ እንደዚህ አይነት ሕገ ወጥ ድርጊቶች ሊስተወሉ ስለሚችሉ ህብረተሰቡ የምግብ ምርቶችን ሲገዛ ፈቃድ ካላቸው ተቋማት መሆን እንዳለበት ባለስልጣኑ አሳስቧል፡፡እንዲሁም አጠራጣሪ ሁኔታዎችን ሲመለከትም በ8482 ነፃ የስልክ መስመር በመደወል ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርቧል፡፡
@cnn_amharic1
@cnn_amharic1


ልጅ ያሬድ የተባለውን ግለሰብ በህግ
ለመጠየቅ የሚያስችል ሥራ እየተሰራ ነው።
*******
ነሐሴ ፳፮ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም
*******
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
******

ባለፉት ቀናት በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ውስጥ በመግባት ከእምነቷ ውጭ የሆነ መዝሙር የዘመረች ወጣት የፈጸመችው ተግባር ጥፋት መሆኑን አምና በፈጸመችው ጥፋት በመጸጸት በቅድስት ቤተ ክርሰቲያን አውደ ምህረት ተገኝታ ይቅርታ መጠየቋን ተከትሎ ልጅ ያሬድ የተባለ ግለሰብ እንኳን የኃይማኖት ሀገር በሆነችው ኢትዮጵያ ቀርቶ እምነት የለሽ በሚባሉት ሀገራት የማይደረግ የድፍረት ስድብና አጋንታዊ የሆነ ጸያፍ ቃላትን በመጠቀም በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ በማህበራዊ ድህረ ገጹ ላይ በተደጋጋሚ ያስተላለፈውን መልዕክት ተመልክተነዋል።

በዚህ ድፍረት የተሞላበት ድርጊትም በርካታ ኦርቶዶክሳውያን አዝነዋል፣አልቅሰዋል፣ በድርጊቱ ክፉኛ በመበሳጨትም ከፍትህ አደባባይ ፍርድ
እንደሚጠብቁ በተለያየ መልኩ እያሳወቁ ናቸው።

ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስን መስቀል ሁሌ መሸከም የየዕለት ተግባሯ ቢሆንም ከ፷ሚሊዮን በላይ ተከታይ ያላትንና ላለፉት ሁለት ሺህ ዘመናት ሀገርን በፍቅርና በስነምግባር ጥላ ሥር ሰብስባ ያኖረች ቤተ ክርስቲያን መሆንዋ እየታወቀ በእንዲህ አይነት በወረዳና ተሰምቶ በማያውቅ ድፍረት ቤተክርስቲያንን በመስደብ ሕዝበክርስቲያኑን ለማሳዘን መሞከር እጅግ አደገኛ ተግባር ነው።

ቤተክርስቲያንም ይህን ጸያፍ ተግባር የፈጸመና የተሳደበን ግለሰብ በዝምታ ማለፍ ስለማይገባት ጉዳዩን በህግ መምርያ በኩል በመከታተል ተገቢውን ሁሉ የምታደርግ መሆኑን ከወዲሁ እየገለጸች በህግ መምሪያችንና በህግ ባለሙያዎቻችን አማካኝነት አስፈላጊውን ሁሉ እስክታደርግ ድረስ ምዕመናን ከቅድስት ቤተክርስቲያን የተማራችሁትን ትዕግስትና ትህትናን መሰረት ባደረገ አግባብ በፍጹም ክርስቲያናዊ ጨዋነት እንድትጠብቁና በጉዳዩ ዙሪያ ከጸጥታ ከአካላት ጋር በትብብርና በአንድነት በመጠቆም እንድትተባሩ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ጥሪዋን ታስተላልፋለች።

የ/ኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

@cnn_amharic1
@cnn_amharic1


የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደረገ

ማክሰኞ ነሐሴ 23 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ከዛሬ ጀምሮ ለአንድ ወር የሚቆይ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋን ይፋ አድርጓል፡፡

ሚኒስቴሩ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ የዓለም ነዳጅ ዋጋ ከሚያዝያ ወር 2015 ጀምሮ እስከሰኔ ወር መጨረሻ ድረስ አንጻራዊ መረጋጋት እንደታየበት ገልጿል።

በዚህም፤ ላለፉት አራት ወራት በችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ለውጥ ሳይደረግ መቆየቱን አስታውሷል።

ሆኖም ግን የዓለም ነዳጅ ዋጋ ከሐምሌ ጀምሮ የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ እያሳየ በመምጣቱ ዋጋውን ማሻሻያ ማድረግ ማስፈለጉ ተገልጿል፡፡

በዚሁ መሰረት:-

1. ቤንዚን ----------ብር 74.85 በሊትር

2. ነጭ ናፍጣ -----------ብር 76.34 በሊትር

3. ኬሮሲን ብር ------------76.34 በሊትር

4. የአውሮፕላን ነዳጅ ---------ብር 68.58 በሊትር

5. ቀላል ጥቁር ናፍጣ -----------62.22 በሊትር

6. ከባድ ጥቁር ናፍጣ -----------61.07 በሊትር መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

@cnn_amharic1
@cnn_amharic1


በአማራ ክልል በትንሹ 183 ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል


የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ቃል አቀባይ ማርታ ሁርታዶ
ከጄኔቫ

ጋዜጣዊ መግለጫ ስለ ኢትዮጵያ

ጋዜጣዊ መግለጫ ስለ ኢትዮጵያ
በአንዳንድ የኢትዮጵያ ክልሎች ያለው የሰብአዊ መብት ሁኔታ መባባሱ በጣም ያሳስበናል።

በአማራ ክልል በኢትዮጵያ ወታደሮች እና በክልሉ ፋኖ ታጣቂዎች መካከል የተቀሰቀሰውን ግጭት እና በነሃሴ 4 ቀን የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ ሁኔታው በእጅጉ ተባብሷል። ከሀምሌ ወር ጀምሮ በተቀሰቀሰ ግጭት በትንሹ 183 ሰዎች መሞታቸውን የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ቢሮ ያሰባሰበ መረጃ ያሳያል።

ሰፋ ያለዉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለባለሥልጣናቱ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል፣ የሰዓት እላፊ ገደብ እንዲጥል እና ሕዝባዊ ስብሰባዎችን እንዲከለክል ሰፊ ሥልጣን ይሰጣል።

በዚህ ህግ በመላው ኢትዮጵያ ከ1,000 በላይ ሰዎች መታሰራቸውን ዘገባዎች ደርሰውናል። ከታሰሩት መካከል ብዙዎቹ የፋኖ ደጋፊዎች ተብለው የተጠረጠሩ የአማራ ብሄር ተወላጆች ወጣቶች መሆናቸው ታውቋል። ከነሃሴ ወር መጀመሪያ ጀምሮ በጅምላ ከቤት ወደ ቤት ፍተሻ እየተካሄደ ነው የተባለ ሲሆን የአማራ ክልልን ሁኔታ ሲዘግቡ ቢያንስ ሶስት ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ታስረዋል። እስረኞቹ መሰረታዊ ምቾታቸው በሌላቸው የታሰሩ የእስር ማቆያ ማዕከላት ውስጥ እንዲቀመጡ መደረጉ ተነግሯል።

ባለሥልጣናቱ የጅምላ እስራት እንዲያቆሙ፣ ማንኛውም የነፃነት መነፈግ በፍርድ ቤት እንዲታይ እና በዘፈቀደ የታሰሩትን እንዲፈቱ እንጠይቃለን። ባለሥልጣናቱ የእስር ሁኔታዎች ዓለም አቀፍ ደንቦችን እና ደረጃዎችን የሚያከብሩ መሆናቸውን ማረጋገጥ አለባቸው። የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ጽህፈት ቤት እና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽንን ጨምሮ - የሁሉንም የእስር ቦታዎች መደበኛ እና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተቆጣጣሪ አካላት እንዲፈቅዱ እንጠይቃቸዋለን። የታራሚዎች ደህንነት መረጋገጥ እና ፍትሃዊ የፍርድ ሂደት እና የሥርዓት ዋስትናን ጨምሮ ሰብአዊ መብቶቻቸው ሙሉ በሙሉ እንዲጠበቁ ሊደረግላቸው ይገባል።

የፌደራል ሃይሎች በተወሰኑ ከተሞች መኖራቸውን እያረጋገጡ እና የፋኖ ታጣቂዎች ወደ ገጠራማ አካባቢዎች እያፈገፈጉ መሆኑን በመግለጽ ሁሉም ተዋናዮች ግድያ፣ሌሎች ጥሰቶች እና ጥቃቶች እንዲያቆሙ እንጠይቃለን። ቅሬታዎች በውይይት እና በፖለቲካ ሂደት መፍታት አለባቸው።

በምዕራብ ትግራይ አጨቃጫቂው አካባቢ ከ250 የማያንሱ የትግራይ ተወላጆች በአማራ ፖሊስ፣ በአካባቢው ባለስልጣናት እና በአካባቢው ታጣቂዎች የታጠቁ የወልቃይት ተወላጆችን ጨምሮ በጋራ ባደረጉት ዘመቻ መታሰራቸውን ክስ ሰምተናል። ከዚያም የታሰሩት በታጠቁ የወልቃይት ወጣቶች የትግራይ ጊዜያዊ ክልል አስተዳደር ወደሚተዳደረው አካባቢ መወሰዳቸውንና በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል። ከዚያም ኢኤንኤፍ በማጣራት የታሰሩትን ወደ ምዕራብ ትግራይ እንዲመለሱ ወይም በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አካባቢ እንዲቆዩ ምርጫ ሰጥቷቸዋል።

የሰብአዊ መብት ረገጣ እና ወንጀሎች እየቀጠለ ባለበት በአሁኑ ወቅት በኦሮሚያ ያለው ሁኔታ አሳሳቢ ነው።

በኢትዮጵያ የተለያዩ ክልሎች የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እና ጥሰቶች በፍጥነት፣በገለልተኛነት እና በብቃት ተጣርተው ተጠያቂ የሆኑ አካላት በህግ መጠየቅ አለባቸው።


" ኑሮውን አልቻለነውም "

እጅግ በርካታ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት በየአካባቢያቸው የዳቦና የእንጀራ ዋጋ አሁን ላይ የደረሰበትን ጠቁመዋል።

ከአዲስ አበባ ውጭ በክልል ከተሞች አንድ ትንሽ ተብሎ የሚታሰበው ዳቦ ከ5 ብር - 9 ብር ድረስ እንደየአካባቢው የሚሸጥ ሲሆን እንጀራ ከ15-20 ብር ድረስ ይሸጣል ፤ የፀጥታ ችግር ባለባቸው ቀጠናዎች ዋጋው እጅግ ተለዋዋጭ መሆኑን የገለፁት ቤተሰቦቻችን ከጊዜ ወደ ጊዜ ኑሮው እጅግ መክበዱን በመግለፅ መፍትሄ እንዲፈለግ ተማፅነዋል።

ከአዲስ አበባ የተለዩ አካባቢዎች በመጡት መልዕክቶች ምንም እንኳን እንደየአካባቢው ቢለያይም አንድ እንጀራ ያውም ስስ እንጀራ ከ20-25 አንዳዴም ደህና እንጀራ ከሆነ እስከ 27 ብር እንደሚሸጥ ጠቁመዋል።

ዳቦም በተመሳሳይ ዋጋው ቀስበቀስ እየጨመረ አሁን ላይ እስከ 10 ብር (ትንሽ የሚባለው) የሚሸጥበት ደረጃ ላይ ተደርሷል ሲሉ ገልጸዋል።

የዋጋ መጨመር ብቻ ሳይሆን ጣራቱና መጠኑም መቀነሱን ሳይናገሩ አላለፉ።

አንድ በአዲስ አበባ በግል ስራ የምትተዳደር የቲክቫህ ቤተሰብ አባል፤ " ጮኸን ጮኸን ደክሞናል ፤ መፍትሄ የሚሰጠንም አጥተናል። እኔ የማገኘው ገንዘብ ደህና ኑሮ ሊያኖረኝ ቀርቶ በልቶ ለማደርም ስለማይበቃ ከቤተሰቦቼ ጭምር ይላክልኛል " ብላለች።

አንድ በንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ነጋዴ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል፤ " በጣም ከባድ ነው ፤ እኔ ነጋዴ ነኝ እገዛለሁ አትርፌ እሸጣለሁ ነገር ግን ማህበረሰቡ ያሳዝነኛል፤ በተለይ አንዳንድ የመንግስት ሰራተኛ እንዴት ከ3000 ባነሰ ደመወዝ እንደሚኖሩ ሳስብ እገረማለሁ፤ ዱቄት 1200 ብር በላይ ጨምሯል፤ ዳቦ 10 ብር ነው፤ እንጀራም 20 ብር ነው ብቻ ይከብዳል፤ በጣም የማዝነው ደግሞ ጊዜው ላለው በመሆኑ ነው፤ መናገር የምፈልገው ነገር በዚህ የኑሮ ውድነት ላይ ከድሃ ጎሮሮ ላይ ቀምተው ሀብታም ለመባል የሚፈልጉትን ነው ሁሉም ሟች ነው ይህን እወቁት " ሲል ሀሳቡን ገልጿል።

ሌላ ነዋሪ እሱ ባለበት አካባቢ የእንጀራ ዋጋ የቤት የሚባለው 27 ብር እንደሚሸጥ የሱቅ ተብሎ ደግሞ የሚሸጠው 24 ብር መሆኑን ጠቁሞ ገዝቶ መግባት እንደከበደው ጠቁሟል።

አንዲት የቤተሰባችን አባል፤ እኛ ስቃይ ላይ ነን ዋጋውን ብንናገር ከወሬ የዘለለ መፍትሄ የለም ስትል ገልጻለች።

ሌላ ነዋሪ፤ ዛሬ ዳቦ መግዣ የሚባለው ከአንድ አመት በፊት የእንጀራ ዋጋ ነበር፤ በጣም ከባድ ነው ሲጨምርም መጠነኛ ቢሆን ጥሩ ግን ሁሉም ነገር እጥፍ በሚባል ሁኔታ ነው እየጨመረ ያለው ብሏል።

አንድ የቤተሰባችን አባል ደግሞ፤ " ነገሩ በሶሻል ሚዲያ እየተወራ ስለሆነ ነው በሁሉም አካባቢ ዋጋዉ የጨመረው " ብለዋል።

" ለምን ዋጋ ጨመራቹ ሲባሉ ሚዲያ ያለቸው
ናቸው ነገሩ እያባባሱት ያሉት በቀናት ልዩነት
ከ15 ብር ወደ 17 ብር ከዛ ወደ 20 ብር፤ ዛሬ ደግሞ 22 ገባ የሚለው የሶሻል ሚድያ ወሬ ይሰሙና እንጀራ 22 ብር ገባ ማለታቸው የማይቀር ነው " ሲሉ ገልጻዋል።

" መልስ ሊሰጠው ካልተቻለ በሶሻል ሚዲያ ላይ ባይነገር ይሻላል " ብለዋል።

በርከት ያሉ የቤተሰባችን አባላት የሀገሪቱ የሰላም ሁኔታ አስተማማኝ ተደርጎ ፣ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል ግጭት እና ጦርነት በአስቸኳይ ቆሞ በሙሉ ኃይል ወደ ምርት ካልተገባ ፤ ዜጎችም ደህንነታቸው ተጠብቆ በሀገራቸው እንደልብ ቀንና ማታ እየተጓዙ ያለስጋት ካልሰሩ ያለው ሁኔታዎች ከዚህ እንዳይከፋ እንደሚያሳስባቸው ገልጻዋል።

ህዝባችን ያለበት ጫና ይመለከተናል የሚሉ አካላትም ቀስ በቀስ እየጨመረ እና ዜጎችም በማይችለው አቅማቸው እንዲለማመዱት እየተደረገ ያለው በተለይ በምግብ ዋጋ ላይ የሚታየውን ከፍተኛ ጭማሪ እንዲቆጣጠሩ ጥሪ አቅርበዋል።


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


አቶ አረጋ ከበደ የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ

ላለፉት ሁለት ዓመታት ክልሉን በፕሬዝዳንትነት ሲመሩ የቆዩት ይልቃል ከፋለ በራሳቸው ፈቃድ ስልጣን መልቀቃቸውን አሚኮ ዘግቧል።

የአማራ ክልል ምክር ቤት በባህር ዳር እያካሄደ ባለው 6ኛ ዙር፤ 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፤ 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ የቀድሞው ፕሬዜዳንት ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ያቀረቡትን የመልቀቂያ ጥያቄ ተቀብሎ በምትካቸው አቶ አረጋ ከበደን የክልሉ ፕሬዜዳንት በማድረግ ሹሟል፡፡

አቶ አረጋ ከበደ በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ መፈጸማቸው ተገልጿል።

@cnn_amharic1
@cnn_amharic1


Репост из: Ethiopian Lecturers' Voice
“በአደጋ እና በበሽታ የሞቱ እንስሳት ሥጋ በሆቴሎች ለምግብነት እየቀረበ እንደሚገኝ ደርሸበታለሁ” የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን‼️

ባለስልጣን መስሪያቤቱ በ2015 በጀት ዓመት ከህገወጥ የእንስሳት ዝውውርና እርድ ጋር በተያያዘ 2 ሺህ 9 ወንጀሎች ላይ እርምጃ መውሰዱን ለጣቢያችን ገልጿል።

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የደንብ መተላለፍ ቁጥጥር ክትትል እርምጃ አወሳሰድ ዳይሬክተር እዮብ ከበደ ህገወጥ ተግባሩ ያጋጥማል ተብሎ ከሚታሰበው መጠመን በእጥፍ እየተከሰተ ይገኛል ነው ያሉት፡፡

ዳይሬክተሩ ጤናው ያልተረጋገጠ በህመም እና በሌሎች አደጋዎች የሞተ እንስሳት ለምግብ ቤቶች ይቀርባል ብለዋል።

ይህን ለማከናወንም በህገወጥ እርድና እንስሳት ዝውውር ላይ ለተሰማሩ ግለሰቦች በመዲናዋ ቤት ተከራይተው እንደሚሰሩ ተደርሶበታል ነው ያሉት፡፡

በተጠናቀቀው በጀት አመት ከጉዳዩ ጋር የሚገናኙ 2009 ወንጀሎች የተፈጸሙ ሲሆን ደርጊቱን የፈጸሙ ሆቴሎችና ምግብ ቤቶች ተለይተው እርምጃ እንደተወሰደባቸው አራዳ ኤፍ ኤም ዘግቦታል።

ማህበረሰቡ ህገወጥ የእንስሳት ዝውውርና እርድ ሲመለከት በ 9995 ደውሎ እንዲያሳውቅ ዳይሬክተሩ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
ዘገባው የአራዳ ኤፍ ኤም ነው!!

@ethio_lecturers


ኤምፔሳ (M-PESA) አገልግሎት ጀመረ

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሞባይል ፋይናንስ አገልግሎት የሆነው ኤምፔሳ (M-PESA) ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የአገልግሎት ፍቃድ ካገኘ ከሦስት ወራት በኋላ ከዛሬ ነሐሴ 10/2015 ጀምሮ አገልግሎት መጀመሩን አስታውቋል።

ባለፉት ሦስት ወራት አስፈላጊ የሲስተም ፍተሻዎችን እና የቴክኒክ ዝግጅቶችን ሲያደርግ ከቆየ በኋላ ከባንኮች ጋር የሚያስፈልጉትን የአጋርነት ስምምነቶች በመፈራረም እንዲሁም ወኪሎችንም በመመልመል እና በማሰልጠን ወደ ሥራ መግባቱ ተገልጿል።

በዚህም መሠረት ኹሉም የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ደንበኞች የኤምፔሳ አገልግሎትን ለማግኘት እንደሚችሉ የተገለጸ ሲሆን፤ የአንድሮይድ (Android) እና የአይኦኤስ (IOS) ስልክ ተጠቃሚዎች በሳፋሪኮም መስመራቸው *733# ላይ በመደወል የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ ተብሏል።

የኤምፔሳ መተግበሪያ በ5 ቋንቋዎች የተዘጋጀ እና የአንድሮይድ ተጠቃሚዎች ከፕሌይስቶር በማውረድ መጠቀም የሚችሉት ሲሆን፤ የአይኦኤስ (IOS) ተጠቃሚ ደንበኞቻችን በቀጣዩ ሳምንታት በአፕስቶር እንደሚያገኙም ተገልጿል።

የሳፋሪኮም ደንበኞች ኤምፔሳን በመጠቀም በአገር ውስጥ ገንዘብ መላክ፣ ከአገር ውስጥና ውጪ ገንዘብ መቀበል፣ ክፍያዎችን መክፈል፣ የአየር ሰዓት መግዛት፣ ወደ ባንክ ሒሳቦቻቸው ገንዘብ ማስገባት ከባንክ ሂሳባቸው ገንዘብ ወደ ኤምፔሳ መላክ መላክ እንደሚችሉ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አስታውቋል።

@cnn_amharic1
@cnn_amharic1


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
"ወደ ፖለቲካ የገባሁበትን ቀን ረገምኩት"  ያሉት የምክር ቤት አባል።

@cnn_amharic1
@cnn_amharic1


ከምርት ጥራት በታች የሚያመርቱ 32 ፋብሪካዎች ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለጸ

በ2015 በጀት ዓመት አስገዳጅ የኢትዮጵያ ደረጃ ያላቸውን ምርቶች የሚያመርቱ 382 ፋብሪካዎች ላይ ባተደረገ የኢንስፔክሽን ሥራ የ32 ፋብሪካ ምርቶች ጥራት ከደረጃ በታች ሆኖ በመገኘቱ እርምጃ መውሰዱንየንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

እርምጃ የተወሰደባቸው 25 የልብስ ሳሙና፣ ውኃ፣ ሽንሽን ቆርቆሮ፣ ሚስማር፣ አርማታ ብርት፣ non-carbonated fruit juice፣ ሶኬት እና ዋይን ፋብሪካዎች የማምረት ሂደቱን አቁመው የማስተካከያ ሥራዎችን እንዲሰሩ የተደረገ ሲሆን፤ 7 አኩሪ አተር ማከፋፋያ፣ የውኃ እና የሳሙና የፋብሪካዎች ላይ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱ ተነግሯል።

ሸማቹን ህብረተሰብ ጥራታቸውና ደህንነታቸው ካልተረጋገጡ ምርቶች በመከላከል ጤናና ደህንነቱ እንዲጠበቅ ለማድረግ በቀጣይም በየፋብሪካዎቹ ላይ የሚደረገው የምርት ጥራት ቁጥጥር ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ በፋብሪካዎቹ ላይ እርምጃ መውሰዱን ይግለጽ እንጂ፤ በየትኞቹ ፋብሪካዎች ላይ እርምጃው እንደተወሰደ በዝርዝር ይፋ አላደረገም፡፡

@cnn_amharic1
@cnn_amharic1

Показано 20 последних публикаций.

1 717

подписчиков
Статистика канала