♥♥
"አንቺ ቆይ የእግዚአብሔር ሚስት ነሽ እንዴ?"♥♥ ♥ #ለቸሮች_የተሰጡ_ተስፋዎች ♥
ከፓ/ር አሸናፊ ከበደ
ዝዋይ አማኑኤል ህብረት ቤተክርስቲያን
በኒዎርክ ውስጥ ከጥቂት አመታት በፊት እንደተፈጸመ ይነገራል...ታሪኩ ፡፡
በጭጋግ በተሸፈነ አንድ ብርዳማ ቀን አንድ ባዶ እግሩን የሆነ የ 10 አመት ልጅ ቆፈኑ እያንዘፈዘፈው በአንድ ጎዳና ላይ ባለ የጫማ ሱቅ መስኮት
ወደ ውስጥ አጮልቆ ይመለከታል፡፡
"አንዲት ሴት ወደ ልጁ ቀረበችና "ልጄ እዚ ቆመህ በመስኮቱ በጥልቅ አጮልቀህ ምታየው ምንድነው?" ብላ ጠየቀችው፡፡"እግዚአብሔርን ጥንድ ጫማ እንዲሰጠኝ እየለመንኩት ነው "ሲል መለሰላት ፡፡ ሴቲቱም ወደ ሱቅ በመዝለቅ ጥንድ ጫማዌችና በዛ ያሉ ካልሲዎች እንዲያመጣላት አዘዘችና የልጁን እጅ ይዛ ወደ ጫማ ሱቁ የጓዳ ክፍል ገባች፡፡በጎድጓዳ ሳህን ውሀ እንዲያመጡላት ጠይቃ የልጁን እግር አጠበችውና በፎጣ አደረቀችው ፡፡ ልጁንም ይዛ ወደ ሱቅ እንደተመለሰች ባለሱቁ ካልሲዎችን አቀረበላት...ልጁ እግር ላይ አጠለቁለት፣የገዛችለትንም ጥንድ ጫማዌች አደረጉለት፡፡ የቀሩትንም ካልሲዎች አሰረችለትና ጀርባውን መታ መታ አድርጋ "አሁን ይመችሀል አልጠራጠርም ! ! ! "አለችው ፡፡
ሴቲቱ ይህንን ቸርነት አድርጋለት ልትሄድ ስትል ልጁ እጇን ያዝ አደረገና በእንባ በተሞሉ አይኖቹ ቀና ብሎ እያያት "አንቺ ቆይ የእግዚአብሔር ሚስት ነሽ እንዴ ?"ብሎ ጠየቃት፡፡
ወዳጆቼ ሆይ ዛሬም ጦርነት እና ረሃብ አለማችንን እያሰጨነቀ ባለበት በዚህ ጊዜ ያለንን ለሌሎች በማካፈል ቸርነት እያደረግን አብረን እየተሳሰብን ብናልፈው መልካም ነው፡፡
♥♥
ለቸሮች የተሰጡ ተስፋዎች ♥♥
1,ቸሮች ፍጹም ተስፋ ይኖራቸዋል ።
"ከመካከል ቀንበርን ብታርቅ ጣትህንም መጥቀስ ብትተው
ባታንጎራጉርም ነብስህንም ለተራበ ብታፈስ የተጨነቀውንም
ነብስ ብታጠግብ ብርሀን በጨለማ ጨለማም እንደ ቀጥር ይሆናል፡፡(ኢሳ 58፡ 10)
2,ቸሮች ከመከራ ይድናሉ ።
"ለችግረኛና ለምስኪን የሚያስብ ምስጉን ነው እግዚአብሔር
ከክፉ ቀን ያድነዋል ፡፡ (መዝ 41፡ 1)
3,
ቸሮች በረከትን ያገኛሉ "እግዚአብሔርን ከሃብት አክብር ከፍሬህም ሁሉ በኩራት ጎተራህም እህል ይሞላል መጥመቂያህም በወይን ጠጅ ሞልታ ትትረፈረፋለች፡፡(ምሳ 3፡ 9-10)
✿ በጎ ፈቃዳችሁ ከሆነ መልዕክቱን share በማድረግ
ለሌሎች ያካፍሉ ። ተባረኩልኝ ! ! !እወዳችኀለው
#
ተሰፋ_አለመልካም ቀን !
CHRIST_TUBE ን ይከታተሉ👍
ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
SHARE |
@CHRIST_TUBESHARE |
@CHRISTFAMILY