#ኮሮና_ቫይረስ😭😭
የመተንፈሻ ማሽን እጥረት
ስለኢትዮጵያ ኮሮና ቫይረስን አስመልክቶ ሳስብ በጣም ያስጨንቀኛል።በሽታው የመተንፈሻ አካልን (ሳንባን) የሚያጠቃ በመሆኑ ተጠቂዎች በሽታውን የመከላከል አቅማቸው ደካማ ከሆነ የመተንፈስ ችግር ይገጥማቸዋል።
ታዲያ በዚህ ጊዜ የመተንፋሻ ስርዓታቸውን ሙሉ በሙሉ ተክቶ የሚሰራ ሰው ሰራሽ መሳሪያ ወይም mehanical ventilator የሚባል ማሽን መጠቀም ግዴታ ይሆንባቸዋል ማለት ነው ።አሁን ችግሩ የሚመጣው የዚህ ማሽን እጥረት መኖሩ ነዉ።
እዚህ አሜሪካ ከባድ የኮሮና ቫይረስ ጥቃት የደረሰባት የኒዮርክ ከተማ ከንቲባ ለፌዴራል መንግስቱ 30,000 mechanical ventilators ቢጠይቅም መንግሥት ማቅረብ የቻለው 4,000 ብቻ ነው ። የፍላጎትና የአቅርቦት (demand and supply) አለመመጣጠኑን ከዚህ መገንዘብ ይቻላል። ይህ እንግዲህ ወደ 19 ሚሊዮን ለሚጠጋ የኒዮርክ ህዝብ ነው።
ታዲያ የኢትዮጵያ ሁኔታ እጅጉን የሚያሳዝን ነው ይኸውም ለመቶ አስር ሚሊዮን ህዝብ አጠቃላይ በአገር አቀፍ ደረጃ ያሉን mechanical ventilators ብዛት ከ200 አይበልጥም መባሉን ከጤና ባለሙያዎች ስሰማ ስጋቴን እጥፍ ድርብ አደረገብኝ።
ኢትዮጵያዬ ፈጣሪ በምህረት ዓይኑ ይይሽ፣ ከዚህ ፈተና ምስኪን አማኝ ህዝብሽን ፈጣሪ ይጠብቅልሽ።
━━━━━━━━━━━━━━━
📢: @Computer_Android_tricks
━━━━━━━━━━━━━━━
☞ሼር በማድረግ ሃላፊነቶን ይወጡ!!!